Get Mystery Box with random crypto!

* የውሙ ዐረፋ ዒባዳ* የውሙ ዐረፋን (9ኛውን ቀን ) መፆም የ2 ዓመት ወንጀል እንደሚያሰርዝ | Muslim Students

* የውሙ ዐረፋ ዒባዳ*

የውሙ ዐረፋን (9ኛውን ቀን ) መፆም የ2 ዓመት ወንጀል እንደሚያሰርዝ ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ተናግረዋል።

የዐረፋን ቀን ፆም ሙሉ አጅር ለማግነት፣
1/ ስምንተኛው ቀን ምሽት ላይ ጾምን ነይቶ ማደር፣
2/ በዕለቱ ከዐረፋ ፆም ውጪ ሌላ (የቀዳና ወዘተ) ፆም አዳብሎ አለመነየት ይገባናል።

ማስታወሻዎች፥
ቀዳ ያለበትም ሰው ቢሆን የዐረፋን ቀን ጾም መጾም ይችላል።
ማንኛውም ከነጋ በኋላ ምግብና መጠጥ ያልቀመሰ ሰው ከነጋ በኋላም ቢሆን ነይቶ ጾም መጀመር ይችላል።
ነገር ግን ምንዳው የሚጀምረው ከነየተበት ሰዓት ጀምሮ ነው።
ከ9ኛው ቀን በፊት ምንም ላልጾመ ሰውም ቢሆን 9ኛው ቀን ብቻ መፆም ይቻላል/ችግር የለውም።
በዐረፋ (9ኛው ቀን) ላይ ይበልጥ የሚወደዱ 3 ዒባዳዎች፣
1/ ቀኑን መጾም
2/ ዚክር ማብዛት በተለይም ተክቢር
3/ ዱዓእ ማብዛት
ለዐረፋ ቀን ራሱን የቻለ ዱዓእ የለውም ሁሉም የቻለውንና የሚፈልገውን ዱዓእ ማድረግ ይችላል።

ነገን (ጁሙዓ ሰኔ 30/2014) በልባችን የዐረፋን ፆም በማሰብ(በመነየት) እንጾም!
ለወዳጅና ዘመድም እናስታውስ
ለራሳችን፣ለቤተሰባችን፣ ለሀገርና ለኡመታችን ዱዓእም እናብዛ

ሀሙስ / ዙል-ሒጃህ 8)1443 ዓ.ሂ

አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:-
وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ
"ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197