Get Mystery Box with random crypto!

Muslim Students

የቴሌግራም ቻናል አርማ muslimstudentsgroup — Muslim Students M
የቴሌግራም ቻናል አርማ muslimstudentsgroup — Muslim Students
የሰርጥ አድራሻ: @muslimstudentsgroup
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.82K
የሰርጥ መግለጫ

እንኳን በደና መጡ!....አስተማሪ ታሪኮች፣ ለትምህርት ጥንካሬ ሊያግዙ የሚችሉ አስተምህሮቶችና መልዕክቶች የሚለቀቁበት ነው።ሀሳብ ወይም አስታየት እንዲሁም እዚህ ቻናል ላይ ምርታቹን መስታወዋቅ ለምትፈልጉ @Remdan333

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-06-05 16:20:04
https://t.me/Dikor_68
360 viewsumu abdul basit ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , 13:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 13:06:02 ከፀጋዎች ሁሉ ትልቁ ፀጋ እስልምና ሲሆን .
ከሁሉም በላጩ ኒእማ ደግሞ
ሙስሊም ሁኖ ኖሮ. . . .ሙስሊም ሁኖ መሞትት ነው ፡፡
507 viewsumu abdul basit ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , 10:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 16:51:05
በስሜታዊ ሳይሆን በምክንያታዊ እንመልከትና መላ እንፍጠር...!!
----------------------------------
አይን ካለህ ተመልከትና ተነጋገር፡
ይህች ነች በቃ ይችች ሀገር፡
ሙስሊሙ በአንድ ቆም በል ተመካከር፡
በእምነትህ እየተደራጀህ ተጠናከር፡
-------------------------------------------
ጉዳዩ በድንገት የተፈጠረ ሳይሆን አማኞች ላይ ያነጣጠረ ሲቀመር የኖረ የግፍ አተላ መሆኑን አስረግጨ እነግርሀለሁ።
«ጉዳያቸው ከአንተ ጋር አይደለም ከአስተሳሰብህ ጋር ነው።»

አላማቸው ጭካኔያቸውን እያሳዩ ሙስሊሙን ማዳከምና እያሸማቀቁ በደማችን ላይ ተረማምደው ግባቸውን እውን ማድረግ ነው።

ተመልከት..ወላሒ....
አሁን እነዚህ ከሰው ልጅ የተፈጠሩ ናቸው ነው የምትሉኝ
ምን አይነት ህሌና ቢኖራቸው ነው
ምን አይነት ጭካኔ ነው!
በዚህ ደረጃ እንደት ሊጠሉን ቻሉ?
ተልዕኳቸው ምንድን ነው!?
እስኪ እየተፈጸመብን ያለውን ግፍ ተመልከቱ!!

አሏህ ሆይ ፦
እንደኛ ወንጀል ሳይሆን እንደ አንተ እዝነት፡
እንደኛ መተኛት ሳይሆን እንደ ኢስላም እንቁነት...ከዚህ በደልና ጭቆና አላቀህ የድል ብስራት አሰማን...!?

~ ኑረዲን አል አረቢ

https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi
1.3K viewsumu abdul basit ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , 13:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 10:15:58
አልጀዚራ የኢትዮጵያ መንግስት ትናንት በአንዋር መስጅድ የሰጋጆችን ደም ማፍሰሱን ዘግቧል።
1.4K viewsհαʍմδ ×͜×, 07:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 07:43:08   ለሙስሊ ደም ተጠያቂ ማን ነው ?

   ብዙ ማሰብ አያስፈልግም ወደድንም ጠላንም ለሙስሊሙ ደም ተጠያቂው ኢኽዋኖች ናቸው ። ብዙዎች ይህ ንግግር እንደሚያበሳጫቸው አውቃለሁ ። ይሁን እንጂ ሊሸሹት የማይቻል እውነታ ሰለሆነ መቀበል የግድ ነው ። ከላይ እስከታች ሁሉም ጣቱን ወደ መንግስት እየቀሰረ ባለበት በዚህ ጊዜ እንዴት እንደዚህ ይላል እንደሚባል ግልፅ ነው ። የሚገርመው ግን ኢኽዋኖች ሰለፍዮችን ነባራዊዉን ሁኔታ የማያውቁ ኋላቀር ብለው እየተቹ ራሳቸው ነባራዊዉን ሁኔታ የማያውቁ መሀይማን መሆናቸው ነው ።
   የመጅሊስ ስልጣን ላይ በወጡ ማግስት ራሳቸውን ከማን ጋር እያወዳደሩ መግለጫ እንደሚሰጡ ለሚያይና የሀገራችንን ታሪክና አሁን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ለሚያውቅ የመጅሊሱ ኮፒ ፔስት ወንበር ላይ የተቀመጡትን ሳይሆን ሙስሊሙን ዋጋ እንደሚያስከፍል ግልፅ ነው ።
     የሙስሊሙ ደም ተጠያቂ መንግስት ነው ወይስ መጅሊሱ ለሚለው መልሱ ከላይ እንዳልኩት መጅሊሱ ነው ። ምክንያቱም አሁን ሀገራችን ያለችበት የፖለቲካ ትኩሳት መንግስት ከውጭም ይሁን ሀገር ውስጥ ስርአቱን ለመናድ እየሰሩ ያሉ አካላት አሉ እነዚህ አካላት ይህን አላማቸውን ህዝብ ውስጥ ገብተው የሚያሳኩበት ቀዳዳ ነው የሚፈልጉት ብሎ በጣም ሴንሴቲቭ ሆኖ እየጠበቀ ባለበት ወቅት ስለሆነ ። ባለፈው ጁሙዓ ነው ሰልፍ የተካሄደው ። ይህ ሰልፍ ከመካሄዱ በፊት ነበር መጅሊሱ መግለጫ የሰጠው ። በሰልፉ ላይ የተፈጠረው ነገር መጅሊሱ አይቷል ። ሙስሊሙን የሚወክል ተቋም እንደመሆኑ የዚህ አይነት ሰልፍ ሸሪዓዊ ብይኑ ምን እንደሆነ በተለይ ደግሞ ሀገራችን ካለችበት ተጨባጭ አንፃር መስላሐና መፍሰዳውን በማስቀመጥ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሌላ ተልእኮ ያላቸው አካላት እንዳይጠቀሙበት በቂ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ አስተምሮ ሰጥቶ ሀላፊነቱን ወስዶ መንግስት ስጋት ውስጥ መግባት እንደሌለበት በማሳመን እርምጃ እንዳይወሰድ ማድረግ ነበረበት ። የሆነው ግን በተቃራኒው ነው ። የተመረጡት ኮሚቴዎች መልስ እሰከሚያመጡ በትእግስት ጠብቁ የሚል ። ይህ መንግስትን የሚያስደስት ነው ወይስ እርምጃ እንዲወስድ የሚያደርግ ? ይህ ማለት የኮሚቴው መልስ ጥሩ ካልሆነ ያኔ መውጣት ትችላላችሁ የሚል ነው ። በሌላ አባባል መንግስትን ስጋት ውስጥ የሚከት ነው ማለት ነው ።  ምክንያቱም ይህን አጋጣሚ መንግስት በአይነ ቁራኛ የሚጠብቃቸው አካላት ላለመጠቀማቸው ምንም ዋስትና ስለሌለ ። ይህ እንዳይሆን መንግስት ስልጣኑን ለመጠበቅ እርምጃ መወሰደ መውሰዱም አይቀርም ። ሙስሊሙ ማህበረሰብ ራሱን ማንነቱ ከማይታወቅ አካል ጥሪ ነፃ እስካላደረገ ።
    የስልጣን ጉዳይ እንኳን የካፊር መሪዎች የሙስሊም መሪዎችም የሚፈተኑበት ጉዳይ ነው ።  እንዳውም ለሶሓቦች ዘመን ቅርብ የነበሩ በዲናቸውና አላህን በመፍራታቸው የተመሰከረላቸውም ጭምር የተፈተኑበት ጉዳይ ነው ። ለዚህ እንደማሳያ የዐብዱል መሊክ ኢብኑ መርዋንን ታሪክ መውሰድ ይቻላል ።
    በ12 አመቱ ቁርኣን የሐፈዘ ፣ ከመዲና 7 የኢስላም ሊቃውንቶች አንዱ የነበረ ፣ በዒባዳውና አላህን በመፍራቱ ታዋቂው ታብዕይ ስልጣን በያዘ ጊዜ ያ ከበኒ ኡመያዎች እጅ ለመውጣት የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደርሶ የነበረውን ስልጣን ለማረጋገጥና ተቀናቃኞችን ከመሬት በታች ለማድረግ
  – ዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድና ሐጃጅ ኢብኑ ዩሱፍን በመሾም ታሪክ የማይረሳው ጉድ ነው የሰራው ። ከእነዚህ አዛዛኝ ስራዎቹ ውስጥ ከዐብዱራሕማን ኢብኑል አሽዓስ ጋር የነበረውን ሰራዊት ከጨረሰ በኋላ ወደ ሁለት መቶ ሺህ የሚጠጉ ሑፋዞችንና ዑለማዎችን ነው ያስጨረሰው ። ምክንያቱም ነገ እናንተም እንደዚሁ ትሰራላችሁ በሚል ።
– ካዕባ ውስጥ ተጠልሎ የነበረውን የዐብዱላሂ ኢብኑ ዙበይር አንገት ተቆርጦ በሄደለት ጊዜ ሐጃጅ ኢብኑ ዩሱፍ አንገቱን እግሩ ስር አድርጎለት ካየው በኋላ እንዲህ ነበር ያለው : –
ይህ እንዲሆን አልፈልግም ነበር ግን ስልጣን ነው ምን ይደረግ አብዮት ልጇን ትበላለች !!!!!። ይህ ነው የስልጣን ጉዳይ የዚህ አይነቱ ተግባር ለስልጣን ተብሎ በሙስሊም መሪዎች ከተፈፀመ የካፊር መሪ ለስልጣኑ ስጋት የሆኑ አካላት ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ ያላቸውን ሰዎች መግደሉ ምን ይገርማል ? ።
   የሚገርመው ይህን ነባራዊ ሁኔታ ሳያውቁ ሙስሊሙን እንመራለን እያሉ ተነስ ስንለህ ትነሳለህ ብለው የሚያስጨፈጭፉት የኢኽዋን መሪዎች ጅልነት ነው ። ለማንኛውም አሁን ሀገራችን ባለችበት ሁኔታ ከታጠቀ ሀይል ጋር መሳፈጥ በእሳት መጫወት ነው ። ሙስሊሞች ራሳችሁን ጠብቁ ሰላማዊ ሰልፍ መንግስት ቢፈቅድም በሸሪዓ አይቻልም ። እህቴ ሆይ ያለፈው ይበቃል ሸሪዓ ቤትሽ መስገድ ይበልጥልሻል ብሎሻል እቤትሽ ስገጂ ። ለዚህ ነው ባንቺ ላይ ጁሙዓም ጀማዐም ግዴታ ያልሆነው ። መስጂድ ከምትሰግጅው ሶላት ቤትሽ የምትሰግጅው አጅሩ ይበልጣል ።
     አላህ ካለ የሰላማዊ ሰልፍን ብይን በተወሰነ መልኩ በዝርዝር ለማይት እንሞክራለን ።
 
  https://t.me/bahruteka

https://t.me/Ethio_Suna_Media
https://t.me/Ethio_Suna_Media
1.4K viewsumu abdul basit ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , 04:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 07:40:41 ➝ድራማው ሌላ ነው እንንቃ..!?

#አጥፍቶ__ጠፊ..!?

#ፕሮቴስታንት በአውሮፓ የተሸመነበት ድርና ማግ እንደሆነ ሁሉ የተዋረደበት ማቅ፣ የተገነዘበት በፍታ፣ የተከፈነበት ግምዣ ነው።

ይህ አስተሳሰብ ከተፈበረከበት ዘመን አንስቶ እስከ አሁን ድረስ #በደም የጨቀዬ ፍትህን የማያውቅ አጋንንታዊና ሰይጣናዊ አስተሳሰቦች የሚሾፍሩት አደገኛ እና ታሪኩ በደም ጎርፍ የታጠበ የጠባብ ሰወች ክምችት ከመሆኑም ባሻገር በዚህ ድርጊቱ ነገም መቀጠልን የሚቋምጥ ከታሪክ የማይማር ህቡዕ ድርጂት ነው።

አውሮፓ #የካቶሊክ አገር በነበረበት ሰዓት ፕሮቴስታንት በሚሽነሪነት እና በጦርነት ተስፋፍቶ ካቶሊክን አዳክሞ ሃይማኖታዊ መንግሥት ሆኖ ነበር።
ዳሩ ግን እራሱ ፕሮቴስታንት ውስጥ የኢአማኒነት ዝገት ተፈጥሮ ዛሬ አውሮፓ ከመቶ 65% በፈጣሪ የማያምን ሕዝብ ሆኗል።

ፕሮቴስታንት አጥፍቶ ጠፊ ነው።
ፕሮቴስታንት በአገራችንም በኢኮኖሚ እና በፓለቲካ በልጽጎ ኦርቶዶክስን እና ሙሥሊሙን እየቦረቦረ ያለ የኢሉሚናቲ ሕዋስ ነው።

ሥልጣን ላይ ያለው የፕሮቴስታንት መንግሥት ጉልበተኛ ሆኖ በሙሥሊሙ እና በኦርቶዶክሱ የውስጥ ጉዳይ እየገባ እና ቤተ እምነትን እያፈራረሰ ሲለውም ምእመናንን እየገደለ ሕዝቡን እያስለቀሰ ነው።
የተበዳይ ጸሎት ደግሞ መሬት ጠብ አይልም፦

ሡነን ኢብኑ ማጃህ 34, ሐዲስ 36
አቢ ሁረይራህ እንደተናገሩት፦
"የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦

"ሦስት ልመናዎች ያለጥርጥር ተቀባነት አላቸው፥ እነርሱም፦ የተበዳይ ልመና፣ የመንገደኛ ልመና እና ወላጅ ለልጁ የሚያደርገው ልመና ናቸው"።

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ ثَلاَثُ دَعَوَاتٍ يُسْتَجَابُ لَهُنَّ لاَ شَكَّ فِيهِنَّ دَعْوَةُ الْمَظْلُومِ وَدَعْوَةُ الْمُسَافِرِ وَدَعْوَةُ الْوَالِدِ لِوَلَدِهِ ‏"‏

ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ 48, ሐዲስ 229

አቢ ሁረይራህ እንደተናገሩት፦
"የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሦስት ሰዎች ልመናቸው ተመላሽ አሆንም፥ እነርሱም፦ "እስኪያፈጥር ድረስ ያለ ፆመኛ፣ ፍትሐዊ መሪ እና የተበዳይ ልመና ናቸው"።

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ ثَلاَثَةٌ لاَ تُرَدُّ دَعْوَتُهُمُ الصَّائِمُ حَتَّى يُفْطِرَ وَالإِمَامُ الْعَادِلُ وَدَعْوَةُ الْمَظْلُومِ "‏

ይህ ፈሣድን በኢትዮጵያ ምድር የሚያስፋፋው የኢሉሚናቲ ሕዋስ በዘረኝነት እና በኢኮኖሚ ምእመናንን አዳክሞ ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳ ነው። ነቃ እንበል!

ሙሥሊሙስ በደልን እና ጭቆናን የሚሸከምበት ጫንቃ የለውም።
ከታሪክ እንደተማርነው ኢንሻላህ ይህ ሥርዓት ጉልበተኛ ሆኖ አይቀጥልም።
አሏህ የተበዳዮችን እንባ የሚታበስበትን ዘመን ያምጣልን! አሚን።

#EthioMuslims
#Islamophobia
1.1K viewsumu abdul basit ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , 04:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 19:23:25
የጧት ስንቅ____

ችግርን  መጋፈጥ የሚያመጣቸው በጎ ተፅዕኖዎች

ችግር  አንድን ሰው በመተናነስ  ወደ ጌታው እንዲዞር ያደርገዋል ።  «  አሏህ ምንኛ የጠራ ጌታ ነው ። በችግር ውስጥ ዱዓ እንድታወስ  አደረገ ። አሏህ ባሪያውን  በአንዳንድ ነገሮች ይፈትንና  ለመላኢኮች ይህን ለምን እንዳደረገ ሲናገር  « ድምፁን ለመስማት ነው»  ይላል » ።  ዱአውንና ልመናውን ማለት ነው ። ችግር በተጠቂው ልብ ውስጥ መተናነስን ያሰርፃል ።

ﻛَﻼَّ ﺇِﻥَّ اﻹِْﻧﺴَﺎﻥَ ﻟَﻴَﻄْﻐَﻰٰ

በእውነቱ ሰው ወሰንን ያልፋል፡፡
(አል_ዐለቅ 6)

ሰዎች የተቸገረን ሰው ያስመቻሉ ። ለተቸገረ ሰው ዱዓ ያደርጋሉ ። ስለዚህ በችግር ወቅት ሙዕሚኖች  በወንድማማችነት መንፈስ አንድ ይሆናሉ ።

ችግር አንድን ሰው አመስጋኝ ሊያደርገው ይገባል ።  ምክንያቱም ከደረሰበት የባሰ ችግር ቢደርስበት ኖሮስ?  በተጨማሪም ችግር ኃጢያትን ያሰርዛል ።  የአሏህ ባሪያ እነዚህን እውነታዎች ሲረዳ አመስጋኝ ይሆናል ። 

ۗ ﺇِﻧَّﻤَﺎ ﻳُﻮَﻓَّﻰ اﻟﺼَّﺎﺑِﺮُﻭﻥَ ﺃَﺟْﺮَﻫُﻢ ﺑِﻐَﻴْﺮِ ﺣِﺴَﺎﺏٍ

« ታጋሾቹ ምንዳቸውን የሚሰጡት ያለግምት ነው»
(አዝ_ዙመር  10)
1.2K viewsumu abdul basit ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , 16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 07:37:25 @Muslimstudentsgroup
سورة الكهف
ሱረቱል አል ካህፍ
1.2K viewsumu abdul basit ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , edited  04:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 07:37:25
سورة الكهف

ሙሉውን ጁም0 ቀን በ naqaa studio

@Muslimstudentsgroup
1.1K viewsumu abdul basit ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , edited  04:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 07:35:03
"عِزَّةُ المَرْأَةِ فِي دِينِهَا، وَمَا غَيْرُ ذَلِكَ وَهْمٌ..".

الشَّيْخُ: صَالِحْ آلْ الشِّيخْ -حَفِظَهُ اللَّهُ-.
1.3K viewsumu abdul basit ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , 04:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ