የጧት ስንቅ____
ችግርን መጋፈጥ የሚያመጣቸው በጎ ተፅዕኖዎች
ችግር አንድን ሰው በመተናነስ ወደ ጌታው እንዲዞር ያደርገዋል ። « አሏህ ምንኛ የጠራ ጌታ ነው ። በችግር ውስጥ ዱዓ እንድታወስ አደረገ ። አሏህ ባሪያውን በአንዳንድ ነገሮች ይፈትንና ለመላኢኮች ይህን ለምን እንዳደረገ ሲናገር « ድምፁን ለመስማት ነው» ይላል » ። ዱአውንና ልመናውን ማለት ነው ። ችግር በተጠቂው ልብ ውስጥ መተናነስን ያሰርፃል ።
ﻛَﻼَّ ﺇِﻥَّ اﻹِْﻧﺴَﺎﻥَ ﻟَﻴَﻄْﻐَﻰٰ
በእውነቱ ሰው ወሰንን ያልፋል፡፡
(አል_ዐለቅ 6)
ሰዎች የተቸገረን ሰው ያስመቻሉ ። ለተቸገረ ሰው ዱዓ ያደርጋሉ ። ስለዚህ በችግር ወቅት ሙዕሚኖች በወንድማማችነት መንፈስ አንድ ይሆናሉ ።
ችግር አንድን ሰው አመስጋኝ ሊያደርገው ይገባል ። ምክንያቱም ከደረሰበት የባሰ ችግር ቢደርስበት ኖሮስ? በተጨማሪም ችግር ኃጢያትን ያሰርዛል ። የአሏህ ባሪያ እነዚህን እውነታዎች ሲረዳ አመስጋኝ ይሆናል ።
ۗ ﺇِﻧَّﻤَﺎ ﻳُﻮَﻓَّﻰ اﻟﺼَّﺎﺑِﺮُﻭﻥَ ﺃَﺟْﺮَﻫُﻢ ﺑِﻐَﻴْﺮِ ﺣِﺴَﺎﺏٍ
« ታጋሾቹ ምንዳቸውን የሚሰጡት ያለግምት ነው»
(አዝ_ዙመር 10)