Get Mystery Box with random crypto!

  ለሙስሊ ደም ተጠያቂ ማን ነው ?    ብዙ ማሰብ አያስፈልግም ወደድንም ጠላንም ለሙስሊሙ ደም | Muslim Students

  ለሙስሊ ደም ተጠያቂ ማን ነው ?

   ብዙ ማሰብ አያስፈልግም ወደድንም ጠላንም ለሙስሊሙ ደም ተጠያቂው ኢኽዋኖች ናቸው ። ብዙዎች ይህ ንግግር እንደሚያበሳጫቸው አውቃለሁ ። ይሁን እንጂ ሊሸሹት የማይቻል እውነታ ሰለሆነ መቀበል የግድ ነው ። ከላይ እስከታች ሁሉም ጣቱን ወደ መንግስት እየቀሰረ ባለበት በዚህ ጊዜ እንዴት እንደዚህ ይላል እንደሚባል ግልፅ ነው ። የሚገርመው ግን ኢኽዋኖች ሰለፍዮችን ነባራዊዉን ሁኔታ የማያውቁ ኋላቀር ብለው እየተቹ ራሳቸው ነባራዊዉን ሁኔታ የማያውቁ መሀይማን መሆናቸው ነው ።
   የመጅሊስ ስልጣን ላይ በወጡ ማግስት ራሳቸውን ከማን ጋር እያወዳደሩ መግለጫ እንደሚሰጡ ለሚያይና የሀገራችንን ታሪክና አሁን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ለሚያውቅ የመጅሊሱ ኮፒ ፔስት ወንበር ላይ የተቀመጡትን ሳይሆን ሙስሊሙን ዋጋ እንደሚያስከፍል ግልፅ ነው ።
     የሙስሊሙ ደም ተጠያቂ መንግስት ነው ወይስ መጅሊሱ ለሚለው መልሱ ከላይ እንዳልኩት መጅሊሱ ነው ። ምክንያቱም አሁን ሀገራችን ያለችበት የፖለቲካ ትኩሳት መንግስት ከውጭም ይሁን ሀገር ውስጥ ስርአቱን ለመናድ እየሰሩ ያሉ አካላት አሉ እነዚህ አካላት ይህን አላማቸውን ህዝብ ውስጥ ገብተው የሚያሳኩበት ቀዳዳ ነው የሚፈልጉት ብሎ በጣም ሴንሴቲቭ ሆኖ እየጠበቀ ባለበት ወቅት ስለሆነ ። ባለፈው ጁሙዓ ነው ሰልፍ የተካሄደው ። ይህ ሰልፍ ከመካሄዱ በፊት ነበር መጅሊሱ መግለጫ የሰጠው ። በሰልፉ ላይ የተፈጠረው ነገር መጅሊሱ አይቷል ። ሙስሊሙን የሚወክል ተቋም እንደመሆኑ የዚህ አይነት ሰልፍ ሸሪዓዊ ብይኑ ምን እንደሆነ በተለይ ደግሞ ሀገራችን ካለችበት ተጨባጭ አንፃር መስላሐና መፍሰዳውን በማስቀመጥ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሌላ ተልእኮ ያላቸው አካላት እንዳይጠቀሙበት በቂ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ አስተምሮ ሰጥቶ ሀላፊነቱን ወስዶ መንግስት ስጋት ውስጥ መግባት እንደሌለበት በማሳመን እርምጃ እንዳይወሰድ ማድረግ ነበረበት ። የሆነው ግን በተቃራኒው ነው ። የተመረጡት ኮሚቴዎች መልስ እሰከሚያመጡ በትእግስት ጠብቁ የሚል ። ይህ መንግስትን የሚያስደስት ነው ወይስ እርምጃ እንዲወስድ የሚያደርግ ? ይህ ማለት የኮሚቴው መልስ ጥሩ ካልሆነ ያኔ መውጣት ትችላላችሁ የሚል ነው ። በሌላ አባባል መንግስትን ስጋት ውስጥ የሚከት ነው ማለት ነው ።  ምክንያቱም ይህን አጋጣሚ መንግስት በአይነ ቁራኛ የሚጠብቃቸው አካላት ላለመጠቀማቸው ምንም ዋስትና ስለሌለ ። ይህ እንዳይሆን መንግስት ስልጣኑን ለመጠበቅ እርምጃ መወሰደ መውሰዱም አይቀርም ። ሙስሊሙ ማህበረሰብ ራሱን ማንነቱ ከማይታወቅ አካል ጥሪ ነፃ እስካላደረገ ።
    የስልጣን ጉዳይ እንኳን የካፊር መሪዎች የሙስሊም መሪዎችም የሚፈተኑበት ጉዳይ ነው ።  እንዳውም ለሶሓቦች ዘመን ቅርብ የነበሩ በዲናቸውና አላህን በመፍራታቸው የተመሰከረላቸውም ጭምር የተፈተኑበት ጉዳይ ነው ። ለዚህ እንደማሳያ የዐብዱል መሊክ ኢብኑ መርዋንን ታሪክ መውሰድ ይቻላል ።
    በ12 አመቱ ቁርኣን የሐፈዘ ፣ ከመዲና 7 የኢስላም ሊቃውንቶች አንዱ የነበረ ፣ በዒባዳውና አላህን በመፍራቱ ታዋቂው ታብዕይ ስልጣን በያዘ ጊዜ ያ ከበኒ ኡመያዎች እጅ ለመውጣት የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደርሶ የነበረውን ስልጣን ለማረጋገጥና ተቀናቃኞችን ከመሬት በታች ለማድረግ
  – ዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድና ሐጃጅ ኢብኑ ዩሱፍን በመሾም ታሪክ የማይረሳው ጉድ ነው የሰራው ። ከእነዚህ አዛዛኝ ስራዎቹ ውስጥ ከዐብዱራሕማን ኢብኑል አሽዓስ ጋር የነበረውን ሰራዊት ከጨረሰ በኋላ ወደ ሁለት መቶ ሺህ የሚጠጉ ሑፋዞችንና ዑለማዎችን ነው ያስጨረሰው ። ምክንያቱም ነገ እናንተም እንደዚሁ ትሰራላችሁ በሚል ።
– ካዕባ ውስጥ ተጠልሎ የነበረውን የዐብዱላሂ ኢብኑ ዙበይር አንገት ተቆርጦ በሄደለት ጊዜ ሐጃጅ ኢብኑ ዩሱፍ አንገቱን እግሩ ስር አድርጎለት ካየው በኋላ እንዲህ ነበር ያለው : –
ይህ እንዲሆን አልፈልግም ነበር ግን ስልጣን ነው ምን ይደረግ አብዮት ልጇን ትበላለች !!!!!። ይህ ነው የስልጣን ጉዳይ የዚህ አይነቱ ተግባር ለስልጣን ተብሎ በሙስሊም መሪዎች ከተፈፀመ የካፊር መሪ ለስልጣኑ ስጋት የሆኑ አካላት ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ ያላቸውን ሰዎች መግደሉ ምን ይገርማል ? ።
   የሚገርመው ይህን ነባራዊ ሁኔታ ሳያውቁ ሙስሊሙን እንመራለን እያሉ ተነስ ስንለህ ትነሳለህ ብለው የሚያስጨፈጭፉት የኢኽዋን መሪዎች ጅልነት ነው ። ለማንኛውም አሁን ሀገራችን ባለችበት ሁኔታ ከታጠቀ ሀይል ጋር መሳፈጥ በእሳት መጫወት ነው ። ሙስሊሞች ራሳችሁን ጠብቁ ሰላማዊ ሰልፍ መንግስት ቢፈቅድም በሸሪዓ አይቻልም ። እህቴ ሆይ ያለፈው ይበቃል ሸሪዓ ቤትሽ መስገድ ይበልጥልሻል ብሎሻል እቤትሽ ስገጂ ። ለዚህ ነው ባንቺ ላይ ጁሙዓም ጀማዐም ግዴታ ያልሆነው ። መስጂድ ከምትሰግጅው ሶላት ቤትሽ የምትሰግጅው አጅሩ ይበልጣል ።
     አላህ ካለ የሰላማዊ ሰልፍን ብይን በተወሰነ መልኩ በዝርዝር ለማይት እንሞክራለን ።
 
  https://t.me/bahruteka

https://t.me/Ethio_Suna_Media
https://t.me/Ethio_Suna_Media