Get Mystery Box with random crypto!

ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)

የቴሌግራም ቻናል አርማ mahibere_kidusan — ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)
የቴሌግራም ቻናል አርማ mahibere_kidusan — ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)
የሰርጥ አድራሻ: @mahibere_kidusan
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.97K
የሰርጥ መግለጫ

The channel of mahibere kidusan

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-04-06 21:30:44 “መቅደስም ትይዩ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ጴጥሮስና ያዕቆብ ዮሐንስም እንድርያስም ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? ይህስ ሁሉ ይፈጸም ዘንድ እንዳለው ምልክቱ ምንድር ነው? ብለው ለብቻቸው ጠየቁት። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ ይላቸው ጀመር። ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ። ብዙዎች እኔ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፥ ብዙዎችንም ያስታሉ። ጦርንም የጦርንም ወሬ በሰማችሁ ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና፥ ነገር ግን መጨረሻው ገና ነው። ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፤ በልዩ ልዩ ስፍራ የምድር መናወጥ ይሆናል፤ ራብ ይሆናል፤ እነዚህ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።

እናንተ ግን ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በምኵራብም ትገረፋላችሁ፤ ምስክርም ይሆንባቸው ዘንድ ስለ እኔ በገዥዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ። አስቀድሞም ወንጌል ለአሕዛብ ሁሉ ይሰበክ ዘንድ ይገባል። ሲጐትቱአችሁና አሳልፈው ሲሰጡአችሁም ምን እንድትናገሩ አስቀድማችሁ አትጨነቁ፤ ዳሩ ግን በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ፤ የሚነግረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁምና።

ወንድምም ወንድሙን አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፤ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ። ይገድሉአቸውማል፤ በሁሉም ዘንድ ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። ነገር ግን በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋት ርኵሰት በማይገባው ስፍራ ቆሞ ብታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፤ በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፤ በሰገነትም ያለ ወደ ቤት አይውረድ፤ ከቤቱም አንዳች ይወስድ ዘንድ አይግባ፤ በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመለስ።

በዚያን ወራትም ለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው። ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት እንዳይሆን ጸልዩ፤ በዚያን ወራት እግዚአብሔር ከፈጠረው ከፍጥረት መጀመሪያ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያልሆነ ደግሞም የማይሆን የመከራ ዓይነት ይሆናልና። ጌታስ ወራቶቹን ባያሳጥር፥ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም፤ ነገር ግን ስለ መረጣቸው ምርጦች ወራቶቹን አሳጠረ።

በዚያን ጊዜም ማንም እነሆ፥ ክርስቶስ ከዚህ አለ፥ ወይም እነሆ፥ ከዚያ አለ ቢላችሁ አትመኑ፤ ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳን ያስቱ ዘንድ ምልክትና ድንቅ ያደርጋሉ። እናንተ ግን ተጠንቀቁ፤ እነሆ፥ አስቀድሜ ሁሉን ነገርኋችሁ። በዚያን ወራት ግን ከዚያ መከራ በኋላ ፀሐይ ይጨልማል፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በብዙ ኃይልና ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል። በዚያን ጊዜም መላእክትን ይልካል፤ ከአራቱ ነፋሳትም ከምድር ዳርቻ እስከ ሰማይ ዳርቻ የተመረጡትን ይሰበስባቸዋል። ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤ እንዲሁ ደግሞ እናንተ ይህን ሁሉ መሆኑን ስታዩ ቀርቦ በደጅ እንደ ሆነ እወቁ። እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም።ሰ ማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም።

ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን ከአባት በቀር የሚያውቅ የለም። ጊዜው መቼ እንዲሆን አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ትጉ፤ ጸልዩም። ቤቱን ትቶ ወደ ሌላ አገር እንደ ሄደ ሰው ነው፤ ለባሮቹም ሥልጣን ለእያንዳንዱም ሥራውን ሰጥቶ በረኛውን እንዲተጋ አዘዘ። እንግዲህ በማታ ቢሆን ወይም በእኩለ ሌሊት ወይም ዶሮ ሲጮህ ወይም በማለዳ ቢሆን ባለቤቱ መቼ እንዲመጣ አታውቁምና፤ ድንገት መጥቶ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ ስለዚህ ትጉ። ለእናንተም የምነግራችሁ ለሁሉ እላለሁ፤ ትጉ።”

ወንድሞች ሆይ! ጊዜ ዋጋው የላቀ በመሆኑና የጌታችንንም የፍርድ ቀን የሚያውቅ አለመኖሩን በቅዱስ ወንጌል ስለተነገረን በበጎነት፣ በቅንነትና በእምነት ጽናት ሆነን በጸሎት እንዲሁም በጾም፣ በትጋትና በክርስቲያናዊ ምግባር በመታነጽ በሃይማኖት ልንኖር ይገባናል፡፡ ዘወትርም ለሕጉ በመገዛትና ትእዛዙን በመፈጸም እስከ መጨረሻው ጸንተን “ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል። እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና” ልንባል ያስፈልጋል፡፡ (ማቴ.፳፭፥፴፬‐፴፮)

ዕድል ፈንታችን መንግሥተ ሰማያት መውረስ ይሆን ዘንድም በምድራዊ ሕይወታችን መከራ ሥቃይ ተቀብለንና ለነፍሳችን መሥዋዕት መክፈል ይገባል እንጂ “እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘለዓለም እሳት ከእኔ ሂዱ። ተርቤ አላበላችሁኝምና፥ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፥ እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፥ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና” ከመባል ይሠውረን፡፡ (ማቴ. ፳፭፥፵፩‐፵፫)
የአምላካችን ቸርነትና ረድኤት አይለየን፤ አሜን!
12.9K views18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-20 19:59:47
ቅዱስ ፓትርያርኩ ምን አሉ ?

ዛሬ በአዲስ አበባ ' ጃንሜዳ ' ባሕረ ጥምቀት በነበረው የጥምቀት በዓል አከባበር ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መልዕክት አስተላልፈው ነበር።

ከቅዱስነታቸው መልዕክት መካከል የሚከተለው ይገኝበታል ፦

" ... እኛን የላከ እግዚአብሔርም ሆነ፣ ከሱ የተላክን እኛ ለሰው ልጆች ሁሉ የምናስተላልፈው መልእክት “ንስሐ ግቡ” የሚለው ነው፡፡

በእውነት ንስሐ ከገባን ጠቡ፣ ግድያው፣ ዘረፋው፣ መለያየቱ ይቆማል ፤ በምትኩ ደግሞ ፍቅር፣ አንድነትና ወንድማማችነት ይሰፍናል፤ መከባበር፣ መተማመን፣ መስማማትና ይቅር ባይነት የበላይነቱን ያገኛል፤ ውጤቱም ሰላምና ዕድገት ይሆናል፤ የእግዚአብሔርን ቃል የምትሰማ ነፍስ ካለች እኛ የምንነግራት ይኼና ይኼ ብቻ ነው።

ከንስሐና ከፍቅር ውጭ በእግዚአብሔር ስም የሚናገር መልእክተኛ ካለ እሱ የእግዚአብሔር መልእክተኛ አይደለም፤  እባካችሁ የሃይማኖት አባቶችና መሪዎች የእግዚአብሔርን ቃል በሰላምና በሰላም ብቻ ለሕዝቡ እናድርስ፤ ሕዝቡም የእግዚአብሔርን ቃል በትክክል ሰምቶ ለሰላም ይታዘዝ፡፡

ሌላው የጥምቀት በዓል ዋና መልእክት “ያለው ለሌለው ያካፍል” የሚለው ትእዛዘ እግዚአብሔር ነው፡፡ ዛሬ ብዙ ወገኖቻችን ሕፃናት፣ እናቶች፣ እኅቶችና አረጋውያን በረኃብ ተቈራምደው ዕለተ ሞታቸውን ሲጠብቁ እያየን ነው፡፡

ወገኖቻችን በረኃብ እንዲህ እየሞቱ #እንደባዕድ ዝም ብለን የምናይ ከሆነ ክርስቲያንነቱ ጥያቄ ውስጥ አይገባምን ? ስለሆነም ኢትዮጵያውያንም ሆን የዓለም ማኅበረ ሰብ በሙሉ በጽኑ ረኃብ ለተጠቃው ሕዝባችን እጃቸውን እንዲዘረጉ በዚህ አጋጣሚ በእግዚአብሔር ስም ጥያቄያችንን እናስተላልፋለን፡፡

እግዚአብሔር በዚሁ ዕለት እኛን ለመቀበል ሰማያዊ በሩን እንደከፈትልን እኛ ኢትዮጵያውያንም አእምሮአችንን ከፍተን ለመረዳዳት ለሰላም፣ ለፍቅር ለይቅርታ ለአንድነትና ለእኩልነት ተጠቃሚነት በርትተን እንድንሰራ ጥሪያችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላፋለን፡፡ "

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
13.3K views16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-12 12:37:44 ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሥርዓቱ መሠረት የበዓላቱና የአጽዋማቱ መደብ የሚታወቅበትና የዘመናቱ ሂደት ተቀምሮ የሚታወጅበት ዕለት መስከረም አንድ ቀን ርእሰ ዐውደ ዓመትን ታከብራለች፡፡ የኢትዮጵያ የወራት ሁሉ መጀመሪያ መስከረም ነው፡፡ በዚህ ወር የመጀመሪያው ቀን የተለያዩ መጠሪያዎች አሉት፡፡ እነርሱም ዘመን መለወጫ፣ ዕንቁጣጣሽ፣ ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል፡፡

አዲስ ዓመት መስከረም አንድ ቀን ለምን ይከበራል?

በኢትዮጵያ (ርእሰ ዐውደ ዓመት) ዘመን መለወጫ በመስከረም ወር የሆነበትን ምክንያት ሊቃውንቱ ሲያትቱ ብርሃናት ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ክዋክብት የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜ አጠናቀው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ ነው፡፡ ያን ጊዜ ሌሊቱ ከቀኑ ጋር እኩል ፲፪ ሰዓት ይሆናል፡፡ ዓመቱን ጠንቅቀው ሲቆጥሩ ፫፻፰፬ ቀናት ይሆናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ “ለዘመን መታወቂያው ይሆን ዘንድ ፀሐይና ጨረቃ ከዋክብትንም ፈጠረ” ይላልና (ሄኖክ. ፳፩፥፵፱)፡፡ በሌላ በኩልም በዘመነ ኖኅ ከንፍር ውኃ ምድር የተገለጠችበት ወር ነው፡፡ (ኩፋሌ. ፯፥፩)፡፡ “በመጀመሪያው ወር ምድር ታየች የንፍር ውኃም ከምድር ደረቀ” የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል መሠረት አድርገው የአቡሻኸር ሊቃውንት የዘመን መለወጫን ታሪካዊ አመጣጥን አብራርተው አስቀምጠዋል፡፡

የቤተ ክርስቲያንን ቀኖናዊ ሥርዐት ያጠኑ ሊቃውንት ደግሞ አዲስ ዓመት መስከረም አንድ ቀን መሆኑን አስመልክተው በጽሑፋቸው ዘመኑን በአራቱ ወንጌላውያን ይከፍሉታል፡፡ ምክንያቱም በዘመነ ዮሐንስ ተፀንሶ በዘመነ ማቴዎስ ተወልዶአል፡፡ የጌታን መጠመቅ፣መሰቀልን፣ ዓለምን ከፍዳና ከመርገም ነጻ ማውጣትን አራቱ ወንጌላውያን እያወሱ ዘመናትን ተከትለው ያለ እንቅፋት እንደሚጓዙ ያስረዳሉ፡፡ ወንጌላዊውን ወይም ዘመኑን ለማወቅ ዓመተ ፍዳ(ኩነኔ) አምስት ሺህ አምስት መቶ እና ዓመተ ምሕረት (አሁን ያለንበትን ዓመት) በመደመር ውጤቱ ለአራቱ ወንጌላውያን ማለትም ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስና ዮሐንስ በማካፈል የምናገኘው ነው፡፡ ይህም የአንዱ ወንጌላዊ ድርሻ ማለት ነው፡፡ በዚህም መሠረት ቀሪው አንድ ከሆነ ዘመኑ ማቴዎስ፣ ሁለት ከሆነ ዘመነ ማርቆስ፣ ሦስት ከሆነ ዘመነ ሉቃስ ምንም ቀሪ ባይኖር ደግሞ ዘመነ ዮሐንስ ነው፡፡ ስሌቱም ከዚህ በታች የተቀመጠውን ምሳሌ መነሻ አድርጎ ወንጌላዊውን ማን እንደሆነ ማወቅ ይቻላል፡፡ስለ አዲስ ዓመት በተለያየ ስም የመጠራቱ ታሪካዊ አመጣጥና ስያሜ መነሻ አሳቡ ምን እንደሆነ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡

አዲስ ዓመት ለምን ቅዱስ ዮሐንስ ይባላል...?

የቅዱስ ዮሐንስ ተግባር በቕዱስ ዮሐንስ አወርቅ የተጠቀሰ ሲሆን ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ለዘመነ ወንጌል በር ወይም መነሻ እንዲሆን ለኢትዮጵያ ዐውደ ዓመት መስከረም አንድ ቀን እንዲከበር አባቶች ወስነዋል፡፡ (ድርሳነ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ ፩-፫)፡፡ መጽሐፈ ስንክሳር “የመስከረም ወር የተባረከ ነው፡፡ እርሱም የግብጽና የኢትዮጵያ ዓመቶች መጀመሪያ ነው፡፡ የዚህ ወር ቀኑና ሌሊቱ እኩል ፲፪ ሰዓት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ቀኑ እየጎደለ ይሄዳል” እንዲል፡፡ በአጠቃላይ ዘመን መለወጫ ከላይ ባየናቸው የተለያየ ስያሜ ይጠራ እንጂ ዘመኑ አዲስ እየተባለ ቢጠራም አዲስ መሆን ያለበት ወርና ወቅቱ ብቻ ሳይሆን የእኛ የክርስቲያኖች ሥርዓት ነው፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነታችሁን አታርክሱ የእግዚአብሔር ማደሪያ ነውና እያለ በመዋዕለ ሥጋዌው ያስተምር ነበር፡፡ አዲስ ዓመት ሲመጣ በኃጢኣት፣ በተንኮል፣ በክፋት የቆሸሸው ሰውነታችን በንስሓ፣ በቅዱስ ቊርባን፣ በመልካም ተግባር አዲስ ልናደርገው ይገባናል፡፡

ዘመነ ማቴዎስም፣ ዘመነ ማርቆስም፣ ዘመነ ሉቃስም ሆነ ዘመነ ዮሐንስ፤ በአራቱም ዘመናት አስቀድሞ ርእሰ ዐውደ ዓመት ቅዱስ ዮሐንስ ይዘከራል፡፡ ዮሐንስ የስሙ ትርጉም «ጸጋ እግዚአብሔር» ማለት ነው፡፡ ዘመናት ዘመናትን እየወለዱ፣ ሰዓታት ደቂቃን ቅጽበትን (ሰኮንድን) ሳይቀር እየሰፈሩ(እየቆጠሩ) ዕለታት ሳምንታትን፣ ሳምንታት ወራትን፣ ወራት ዓመታትን አሁን ላለንበት ዘመን ደርሰናል፡፡

ዕንቁጣጣሽ

ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚያስረዱት ዕንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜው አመጣጥ ወይም ጥንተ ታሪክ በመጀመሪያ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ አህጉራትን በዕጣ ሲያካፍላቸው አፍሪቃ ለካም ደረሰችው፡፡ በአፍሪቃ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በሀገረ ኢትዮጵያ በወርኀ መስከረም ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኃ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት «ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ» ይህችን ወቅት ዕንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡ በመቀጠል የሀገራችን ንግሥት ንግሥተ ሳባ የንጉሥ ሰሎሞንን ዜና ጥበብ በጆሮዋ የሰማችውን በዓይኗ ዓይታ ለመረዳት ስለፈለገች ወደ ኢየሩሳሌም ገባች፡፡ ንግሥተ ሳባም ከንጉሡ ሰሎሞንም ተገናኝተው ቤተ መንግሥቱንም አስጎበውኝቶ ሲያበቃ «ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንልሽ» ሲል እጅግ በጣም የከበረ ዕንቁ አበረከተላት/ሰጣት/፡፡ ወሩም ወረኃ መስከረም ነበር፡፡

ንግሥቷ ጠቢቡ ሰሎሞንን ለመጎብኘት በሔደችበት ወቅት ፀንሳ ቀዳማዊ ምኒልክን በወለደች ጊዜ ሕዝቡ ንጉሥ ተወለደ እልል እያሉ «አበባ ዕንቁ (አብረቅራቂ ድንጋይ) ጣጣሽ (ገጸ በረከት)» እያለ ገጸ በረከት ለንግሥቲቱ አበረከቱ፡፡ ያ የዘመን መለወጫ በዓልም ልጃገረዶች የአበባ ገጸ በረከት የሚያቀርቡበት ስለሆነ ዕንቁጣጣሽ ተባለ፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው መጥቷል፡፡ አሁን ከሚፈጸመው ሥነ ሥርዓት ደርሶ በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ የሚከበረውም መስከረም አንድ ቀን ነው፡፡ አንድም «ዕንቁ ዕፅ አወጣሸ»ብሎ የአበባውን መፈንዳትን ያስረዳናል፡፡ የዘመን መለወጫ (ርእሰ ዐውደ ዓመት) ዕንቁጣጣሽ ተብሎም እንደሚጠራ ታሪክ ያወሳናል፡፡ ስያሜውም ለበዓሉ የተሰጠው በንግሥተ ሳባ ዘመነ መንግሥት ነበር፡፡

አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የአንድነትና የመተሳሳብ ዘመን እንዲሆንልን የእግዚአብሔር ቸርነት የቅደስት ደንግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁንልን አሜን፡፡
14.1K views09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-12 12:37:44
ርእሰ ዐውደ ዓመት

ዐውደ ዓመት መነሻው ዖደ ከሚለው የግእዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ዖደ ዞረ፤ዐውድ ዙርያ፣ ማለት ነው፤ ዐውደ ዓመት የፀሐይ ዐውደ ዓመት ፫፻፷፭ ዕለት ከሩብ ይላል፡፡ (ምንጭ፡ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መጽሐፈ ሰዋሰወ ወግስ ወመዘግበ ቃላት ገጽ ፮፻፹፯)፡፡ ወበዐውዱ ለወእቱ መንበር፡፡ ይቀውሙ ዐውዶ፡፡ ዐውደ ጸሓይ፣ ዐውደ ወርኅ፣ ዐውደ ዓመት (ራእ.፬፡፬፤ አቡሻህር ፳፫)

ዐውደ ዓመት በግእዝ ሲሆን በአማርኛ የዘመን መለወጫ ይባላል፡፡ ርእሰ ዐውደ ዓመት ቅዱስ ዮሐንስ መፅምቅን ያወሳናል፤ የቅዱስ ዮሐንስ ዕረፍት (ምትረተ ርእሱ) የሚታሰበው መስከረም ሁለት ቀን ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስን በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ መካከል የነበረ መሸጋገሪያ ነው፡፡ መታሰቢያ በዓሉም የብሉይ ኪዳን ምሳሌ ከሆነው ካለፈው ዓመት የሐዲስ ኪዳን ምሳሌ ወደሚሆነው አዲሱ ዓመት መሸጋገሪያ በሆነው በመስከረም አንድ ቀን ይከበራል፡፡ቅዱስ ዮሐንስ በነቢያት መጨረሻ በሐዋርያት መጀመሪያ ተገኝቶ ዘመነ ሐዲስን እንደሰበከና ከዘመነ ብሉይ ወደ ዘመነ ሐዲስ መሸጋገሪያ ጊዜ ላይ ስለነበረ ያለፈውን ዘመን የምንሸጋገርበት የዘመን መለወጫ ቀን የቅዱስ ዮሐንስ መታሰቢያ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ (ማር.፩፥፪-፭)

የዘመን ቆጠራ ከጌታችን ልደት በፊት የነበረው አገልግሎት የሰው ልጆች ሁሉ በተለይ አበው ነቢያት/ በተስፋ ይጠብቁት የነበረውን የጌታችንን መምጣት የቀረውን ጊዜ እንዲሁም በብሉይ ኪዳን አጽዋማትና በዓላት ለማወቅ ነበር፡፡ ተስፋው ከተፈፀመ በኋላ ደግሞ የዘመን ቆጠራ ዋና አገልግሎቱ በዓላትና አጽዋማት በዓመቱ የሚወሉበትን ዕለት ለማወቅ ነው፡፡ እነዚህ በዓላት እግዚአብሔር በተለያዩ ዘመናት ለሰው ልጆች ያደረጋቸው ድንቅ ነገሮችና ውለታዎች የፈጸመባቸው ስቅለት፣ ትንሣኤ እና ሌሎችም በዓላት የሚታሰቡባቸው ናቸው፡፡
13.2K views09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 17:12:20 በዚሁም መሠረት የተሰየሙት አስመራጭ ብፁዓን አበው ሊቃነጳጳሳት ቋሚ ሲኖዶስ አስቀድሞ ባወጣው የእጩ ኤጲስ ቆጶሳት መመልመያ መስፈርት መሠረት ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በጥቆማ ከቀረቡላቸው 75 ቆሞሳት መካከል በትምህርት ዝግጅታቸው፣ በአሠረ ምንኲስናቸው፣ በቋንቋ ችሎታቸውና መንፈሳዊ አገልግሎታቸው መስፈርቱን አሟልተው የተገኙትን 18 እጩ ቆሞሳትን ከነሕይወት ታሪካቸው የተሟላ ሪፖርት ሰኔ 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ለቋሚ ሲኖዶስ አቅርበዋል፡፡
 
ቋሚ ሲኖዶስም የቀረበውን ሪፖርት መነሻ በማድረግ በጉዳዩ ላይ ከተወያየ በኋላ በቀረቡት እጩ ቆሞሳት ላይ ምርጫ እንዲደረግ ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ባስተላለፈው የስብሰባ ጥሪ መሠረት ከሰኔ 27 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ባደረገው የ2 ቀን ስብሰባ በሁለት ዓበይት አጀንዳዎች ማለትም በእጩ ኤጲስ ቆጶሳት ምርጫና በትግራይ ክልል አህጉረ ስብከት ወቅታዊ ችግር ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡ 

በዚሁም መሠረት፡- 1ኛ. የእጩ ኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ በተመለከተ፡- 
 
1. ቆሞስ አባ ሣህለማርያም ቶላ ………….. ለምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት
2. ቆሞስ አባ ወ/ገብርኤል አበበ……………. ለምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት  
3. ቆሞስ አባ ጥላሁን ወርቁ………………. ለምሥራቅ ሐረርጌሀገረ ስብከት
4. ቆሞስ አባ አምደሚካኤል ኃይሌ……….. ለሆሮ ጉድሩሀገረ ስብከት     
5. ቆሞስ አባ ኃይለማርያም ጌታቸው……… ለድሬዳዋ ሀገረ ስብከት
6. ቆሞስ አባ ዘተ/ሃይማኖት ገብሬ………… ለምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት
7. ቆሞስ አባ አስጢፋኖስ ገብሬ…………… ለቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት
8. ቆሞስ አባ ክንፈገብርኤል ተ/ማርያም….. ለጌዴኦ አማሮና ቡርጂ ሀገረ ስብከት
9. ቆሞስ አባ ስብሐት ለአብ ኃይለማርያም… ለዳውሮ ኮንታ ሀገረ ስብከት
በኤጲስ ቆጶስነት እንዲሾሙ የተመረጡ ሲሆን በዓለ ሢመቱንም በተመለከተ ሐምሌ 9 ቀን 2015 ዓ.ም. እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ 

2ኛ. በክልል ትግራይ በተካሄደው ጦርነት ወቅት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊትና ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን እንደመሆኗ መጠን ጦርነቱ እንዲቆም በወቅቱ መግለጫ ባለመስጠቷ፣ በጦርነቱ መካከል ወደ ትግራይ ክልል መግባትና መውጣት በሚቻልበት ወቅትም በክልሉ የሚገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንንና መላው ሕዝበ ትግራይን በአካል በቦታው ተገኝታ ባለመጠየቋና ባለማጽናናቷ፣ ጦርነቱ ቁሞ በአገር አቀፍ ደረጃ እርቀ ሰላም ከወረደበት ጊዜ ጀምሮ ለደረሰው ጉዳት በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነውን ሰብአዊ ድጋፍ በውሳኔው መሠረት በወቅቱ ማድረስ ባለመቻሏ፣ በዚሁም የተነሣ በቤተ ክርስቲያኗና በመላው ሕዝበ ትግራይ መካከል ለተፈጠረው ቅሬታና አለመግባባት ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታ ጠይቋል፡፡  

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ
 
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ሰኔ ፳፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም 
አዲስ አበባ   
ኢትዮጵያ
3.6K views14:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 17:12:20
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን በክርስቶስ ደም ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ  ከቅዱሳን ሐዋርያት የወረሰችውን ምዕመናንን የመጠበቅና ወንጌለ መንግሥቱን ለዓለም የማዳረስ እንዲሁም ዶግማዋ እና ቀኖናዋ ሳይፋለስ ጠብቃ በማስጠበቅ የተቀደሰውን ሥርዓተ አምልኮ ከትውልድ ወደ ትውልድ በማሻገር የማይተካ ሚና በመጫወት እስካሁን የደረሰች በቀጣይም ይህንን ሐዋርያዊ ተልዕኮዋንና የክህነት አገልግሎትዋን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ እንዲቻል ከሐዋርያት ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ኤጲስ ቆጶሳትን እየሾመች መንፈሳዊ አገልግሎቷን ስታከናውን ኖራለች፤ ወደፊትም ትኖራለች፡፡ ይህም በመሆኑ ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም. በኦሮምያ ክልል በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጭ በተፈጸመው ሢመት በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የደረሰውን መከራና ፈተና ለማሳለፍ ሲባል ዶግማዋን፣ ቀኖናዋንና ትውፊቷን ባስጠበቀ ሁኔታ ችግሩ በውይይት እንዲፈታ ባደረገችው ያላሰለሰ የሰላም ጥሪ መነሻነት የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም. ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በተደረሰው ስምምነት መሠረት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ቀኖናዋን ከስምምነቱ፣ ስምምነቱን ከቀኖናዋ ጋር በማዛመድ በኦሮምያና በደቡብ ክልል ባሉ ክፍት አህጉረ ስብከት ተመድበው የሚያገለግሉ 9ኝ ኤጲስ ቆጶሳት በቀኖና ቤተ ክርስቲያን እንዲሾሙ በወሰነው መሠረት ተሿሚ እጩ ኤጲስ ቆጶሳትን መልምለው የሚያቀርቡ ሰባት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን መሰየሙ ይታወሳል፡፡
3.3K views14:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 17:12:19
የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ

ምንጭ: EOTC TV
3.2K views14:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 22:49:23
በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ የልዑካን ቡድን ሐምሌ ፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም ወደትግራይ ርዕሰ ከተማ መቐለ ይጓዛል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ባስ ተላለፈው ውሳኔ መሰረት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሚመራ የልዑካን ቡድን ሐምሌ ፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ .ም ወደ ክልል ትግራይ ርዕሰ ከተማ መቐለ ይጓዛል።

ልዑካን ቡድኑ ወደ መቐለ የሚጓዘው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ መሰረት ለትግራይ ክልል እንዲሰጥ የተወሰነውን ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስና በትግራይ ከሚገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በሰላም ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር መሆኑ ታውቋል።ይህንን በተመለከተም ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት የተላከው ደብዳቤ ለፕሬዝዳንቱ ጽሕፈት ቤት ዛሬ ማለዳ እንዲደርስ ተደርጓል።

ምንጭ: EOTC Public relations
5.1K views19:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 02:34:11 ሕንጸተ ቤተ ክርስቲያን

እንኳን አደረሰን!

በኬልቄዶን አውራጃ በቂሣርያ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ያለ እንጨት፣ ያለ ጭቃና ያለ ውኃ በሰኔ ፳ ቀን ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሦስት ድንጋዮች ቤተ ክርስቲያን ያነጸበት ዕለት የከበረ በዓል ነው፡፡ ይህም የሆነው ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ በርናባስ ወደ ፊልጵስዩስ ገብተው በክርስቶስ ስም አሳምነው ብዙ አሕዛብን ካጠመቁ በኋላ ቤተ ክርስቲያን ሊሠሩላቸው ፈልገው በተነሡበት ጊዜ ነበር፡፡ ቤተ ክርስቲያኗንም ለመሥራትም ለርእሰ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ መልእክት ላኩበት፡፡ ከቅዱስ ጳውሎስ እና ቅዱስ በርናባስ ጋር በኢየሩሳሌም ተገናኙ፤ ቅዱስ ዮሐንስም ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር አብሮ መጥቶ ነበር፡፡

በዚያም በአንድነት ሱባዔ ይዘው በለመኑት ጊዜ ጌታችን የሞቱትን አስነሥቶ፣ ያሉትንም ጠርቶና ቅዱሳን ሐዋርያትን በፊልጵስዩስ ሀገር ሰብስቦ ‹‹በእናቴ በድንግል ማርያም ስም ከጽንፍ እስከ ጽንፍ
የሚሠራውን የአብያተክርስቲያናት ሥራ ላሳያችሁ፤ ሥርዓቱንም ላስተምራችሁ ሰብስቢያችኋለሁ›› ብሎ ወደ ምሥራቅ ይዟቸው ወጣ፡፡ (መጽሐፈ ሥንክሳር ሰኔ ፳ ቀን)

በዚያ ሥፍራ የነበሩትን ሦስት ድንጋዮችንም የተራራቁትን አቀራርቦ፣ ጥቃቅኑን ታላላቅ አድርጎ ቁመቱን በ፳፬፣ ወርዱን በ፲፪ ክንድ ለክቶ ለቅዱሳን ሐዋርያት ሰጣቸው፡፡ ከዚህ በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያት ድንጋዩ በእጃቸው ላይ እየተሳለ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑን ሠርተው ፈጽመውታል፡፡ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ የተሠራውም ጌታችን በዐረገ በ፲፱ኛው፣ እመቤታችን በዐረገች በ፬ኛው ዓመት ሰኔ ፳ ቀን ሲሆን በማግሥቱ በ፳፩ኛው ቀን ኅብስት ሰማያዊ፣ ጽዋዕ ሰማያዊ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ወረደ፡፡ ጌታችንም ከእመቤታችን ጋር ከሰማየ ሰማያት መጥቶ እመቤታችንን ታቦት፣ ሐዋርያትን ልዑካን አድርጎ፣ እርሱ ሠራዒ ካህን ሆኖ ቀድሶ አቆረባቸው፡፡

ከዚያም በኋላ ‹‹እምይእዜሰ አንትሙኒ ከመዝ ግበሩ፤ ከዛሬ ጀምሮ እናንተም እንደዚህ አድርጉ›› ብሎ አዟቸው በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡ የሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ ቁመት የ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ አምሳል ነው፤ ወርዱ ደግሞ የ፲፪ቱ ሐዋርያት ምሳሌ ነው፡፡ አንድም ሦስቱ ድንጋዮች የሥላሴ አምሳል ምሳሌ ናቸው፤ ከታች አቀማመጣቸው ሦስት፣ ከላይ ሕንጻቸው አንድ መሆኑ የሥላሴን ሦስትነትና አንድነት ያስረዳል፡፡ የሠሩትም ሦስት ክፍልም የመጀመሪያው ክፍል የታቦተ አዳም፣ ሁለተኛው የታቦተ ሙሴ፣ ሦስተኛው የታቦተ ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡ አንድም የሦስቱ ዓለማት ማለትም የጽርሐ አርያም፣ የኢዮር፣ የጠፈር ምሳሌ ነው፡፡ አንድም አንደኛው የኤረር፣ ሁለተኛው የራማ፣ ሦስተኛው የኢዮር አምሳል ነው፡፡ በኤረር፡- መላእክት፣ መኳንንት፣ ሊቃናት፤ በራማ፡- ሥልጣናት፣ መናብርት፣ አርባብ፤ በኢዮር፡- ኃይላት፣ ኪሩቤል፣ ሱራፌል ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ዘጠኙ ነገደ መላእክት የዘጠኙ መዓርጋተ ቤተ ክርስቲያን (መዓርጋተ ክህነት) አምሳል ሲሆኑ ይኸውም መላእክት የመዘምራን፣ የመኳንንት የአናጕንስጢሳውያን፣ ሊቃናት የንፍቀ ዲያቆናት፣ ሥልጣናት የዲያቆናት፣ መናብርት የቀሳውስት፣ አርባብ፣ የቆሞሳት፣ ኃይላት፣ የኤጲስ ቆጶሳት፣ የሱራፌል፣ የጳጳሳት፣ የኪሩቤል እንዲሁም የሊቃነ ጳጳሳት ምሳሌዎች ናቸው፡፡

ይህም በምድር የሚኖሩ ደቂቀ አዳም ከቅዱሳን በቀር ወደ ሰማይ መውጣት እንደማይቻላቸውና ከመዘምራን እስከ ጳጳሳት ድረስ ያሉ ካህናትም ከእነርሱ በላይ ያሉትን መዓርግ መሥራት እንደማይቻላቸው ያስረዳል፡፡ እንደዚሁም መላእክት ወደ ምድር መውረድ እንደሚቻላቸውና ሊቃነ ጳጳሳትም ከእነርሱ በታች ያሉ ካህናትን ተልእኮ መፈጸም እንደሚቻላቸው ያስረዳል፡፡ በጽርሐ አርያም መንበረ ብርሃን፣ ታቦተ ብርሃን፣ መንጦላዕተ ብርሃን እንደዚሁም ፬ ፀወርተ መንበር፣ ፳፬ አጠንተ መንበር (መንበሩን የሚያጥኑ) መላእክት አሉ፡፡ ጽርሐ አርያም የመቅደስ፣ መንበረ ብርሃን የመንበር፣ መንጦላዕተ ብርሃን የቤተ መቅደሱ መጋረጃ፣ ፬ቱ ፀወርተ መንበር የ፬ቱ ሊቃነ ጳጳሳት ወይም የመንበሩ እግሮች፣ ፳፬ቱ አጠንተ መንበር የጳጳሳት (የኤጲስ ቆጶሳት) ምሳሌዎች ናቸው፡፡

ምንጭ፡-መጽሐፈ ስንክሳር፣ ሰኔ ፳ ቀን እንዲሁም መጽሐፈ ታሪክ ወግስ፣ገጽ ፫፻፵፱-፫፻፶፩

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
12.9K views23:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-26 22:59:14
የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ 65 ደቀ መዛሙርትን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በዛሬው ዕለት ሰኔ 18 ቀን 2015 ዓ.ም አስመረቀ፡፡

መንፈሳዊ ኮሌጁ በበጋ ትምህርት በኦሮምኛና በአማርኛ ያስተማራቸውን 33፣ በሥራ አመራር ዘርፍ በዲፕሎማ 22 በሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ 10 በአጠቃላይ 65 ደቀመዛሙርትን አስመርቋል ፡፡

በዕለቱ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ፣ ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆርዮስ የደቡባዊ ትግራይ ማይጨው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ም/ሥራ አስኪያጅ፣ ሊቀ ትጉኅን ቀሲስ ታጋይ የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ተቋማት ሕብረት ጠቅላይ ጸሐፊና ሌሎች የሀገረ ስብከቱ እና የከተማው የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
9.5K views19:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ