Get Mystery Box with random crypto!

የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ 65 ደቀ መዛሙርትን ብፁዓ | ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)

የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ 65 ደቀ መዛሙርትን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በዛሬው ዕለት ሰኔ 18 ቀን 2015 ዓ.ም አስመረቀ፡፡

መንፈሳዊ ኮሌጁ በበጋ ትምህርት በኦሮምኛና በአማርኛ ያስተማራቸውን 33፣ በሥራ አመራር ዘርፍ በዲፕሎማ 22 በሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ 10 በአጠቃላይ 65 ደቀመዛሙርትን አስመርቋል ፡፡

በዕለቱ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ፣ ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆርዮስ የደቡባዊ ትግራይ ማይጨው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ም/ሥራ አስኪያጅ፣ ሊቀ ትጉኅን ቀሲስ ታጋይ የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ተቋማት ሕብረት ጠቅላይ ጸሐፊና ሌሎች የሀገረ ስብከቱ እና የከተማው የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።