Get Mystery Box with random crypto!

ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)

የቴሌግራም ቻናል አርማ mahibere_kidusan — ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)
የቴሌግራም ቻናል አርማ mahibere_kidusan — ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)
የሰርጥ አድራሻ: @mahibere_kidusan
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.91K
የሰርጥ መግለጫ

The channel of mahibere kidusan

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-06-24 19:04:09
የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በቀንና በማታ መርሐ ግብር ያስተማራቸውን ደቀ መዛሙርት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አስመረቀ ::

መንፈሳዊ ኮሌጁ በብሉይ ኪዳን 7፣ በሐዲስ ኪዳን 23፣ በመጽሐፈ ሊቃውንት 10፣በመጽሐፈ መነኮሳት 1፣ እና በሴሚናሪ 163 በአጠቃላይ 204 ትምህርታቸውን  ያጠናቀቁ ደቀ መዛሙርት ዛሬ ሰኔ 17 ቀን 2015 ዓ,ም በቅዱስነታቸው ዲፕሎማ ተጥቷቸዋል።

ቅዱስነታቸው ለደቀ መዛሙርቱ የምስክር ወረቀት ከሰጡ በኋላ ትምህርተ ወንጌል  ቃለ ምእዳን ቡራኬ ሰጥተዋ::

በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽርሐ ተዋህዶ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ በተካሔደው የደቀ መዛሙርት ምረቃ ላይ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የኮሌጁ  የመምሪያ ኃላፊዎች፣ የተመራቂ ቤተሰቦችና ጥሪ የተደረገላው እንግዶች ተገኝቷል።

 የብፁዕ ወቅዱስነታቸው ቡራኬ ይድረሰን!

ምንጭ:- የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
10.4K views16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 19:30:31 በትግራይ ክልል ከሚገኙ አባቶች ጋር ውይይት
ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተጠናቀቀ።
*****

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በግንቦት ወር ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
ባካሔደው የርክበ ካህናት ጉባኤ በትግራይ ክልል ከሚገኙ አባቶች ጋር የሚደረገው ውይይት ቀደም ሲል በቋሚ ሲኖዶስ በተሰየመው የልዑካን ቡድን አማካኝነት በአስቸኳይ እንዲቀጥል መወሰኑ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ ኮሚቴው ውይይቱን በተሳካ ሁኔታ ለማካሔድ የሚያስችለውን በእቅድ ላይ የተመሰረተ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ሲያከናውን የቆየ ሲሆን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ውይይቱ በተሳካ ሆኔታ መካሔድ የሚችልበትን ሁኔታ እንዲያመቻች በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በተጻፈ ደብዳቤ ጥያቄውን አቅርቧል።የልዑካን ቡድኑ አባላትም ከቅዱስ ፓትርያርኩ የተጻፈውን ደብዳቤ በአካል በመገኘት ለክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት በማቅረብ ከሚመለከታቸው የክልሉ የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር የክልሉ ጊዚያዊ መንግስት ለውይይቱ መሳካት በሚያደርገው ድጋፍ ዙሪያ ውይይት በማድረግ ተመልሷል።

ስለሆነም ለክልሉ መንግስት በቀረበው ጥያቄ መሰረት ሁለቱም አካላት በሚያመቻቹት ጊዜና ቦታ ውይይቱ የሚካሔድ ይሆናል።

በዚህም መሰረት የጠቅላይ ቤተክህነት ልዑካን ቡድን ውይይቱን ውጤታማ ለማድረግ ይቻል ዘንድ እስከ አሁን ያከናወናቸውን ተግባራትና ወደፊት ውይይቱን ስኬታማ በሆነ መንገድ ማካሔድ በሚችልበት ሁኔታ ላይ ሰኞ ሰኔ ፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ይፋዊ መግለጫ ይሰጣል።መግለጫውን ተከትሎም ጉዳዩ በቀኖና ቤተክርስቲያን መሰረት የመጨረሻ እልባት እንዲያገኝ በፍጥነት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በመግባት በሒደቱ የሚመዘገቡ ለውጦችን ሁሉ በመገናኛ ብዙሃን የሚያሳውቅ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሰኔ ፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
4.8K views16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 19:30:31
#አደራ_አለብኝ

#ዓለም_ዓቀፍ_የግቢ_ጉባኤ_ምሩቃን_ኅብረት_ጉባኤ

#4ኛ_ዙር

• ቀን፡ ሰኔ 04/2015 ዓ.ም
• ሰዓት፡ ከ 7፡30 ጀምሮ
• ቦታ፡ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ

ማኅበረ ቅዱሳን
4.4K views16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 13:14:36
#አደራ_አለብኝ

#ዓለም_ዓቀፍ_የግቢ_ጉባኤ_ምሩቃን_ኅብረት_ጉባኤ

#4ኛ_ዙር

• ቀን፡ ሰኔ 04/2015 ዓ.ም
• ሰዓት፡ ከ 7፡30 ጀምሮ
• ቦታ፡ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ

ማኅበረ ቅዱሳን
2.5K views10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 13:14:36
2.5K views10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 13:14:36
2.4K views10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 00:01:39
መልካም ዜና

መምህር ኃይለ ማርያም ዘውዱ ከእስር ተፈተዋል።


ግንቦት 5 ቀን 2015 ዓ.ም ባሕር ዳር ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ተይዘው በአዲስ አበባ የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ ውስጥ በእስር ላይ የነበሩት መምህር ኃይለ ማርያም ዘውዱ ከእስር መለቀቃቸውን ቤተሰቦቻቸው ለዝግጅት ክፍላችን አሳውቀዋል።
5.3K views21:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 22:15:00
#አደራ_አለብኝ

#ዓለም_ዓቀፍ_የግቢ_ጉባኤ_ምሩቃን_ኅብረት_ጉባኤ

#4ኛ_ዙር

• ቀን፡ ሰኔ 04/2015 ዓ.ም
• ሰዓት፡ ከ 7፡30 ጀምሮ
• ቦታ፡ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ

ማኅበረ ቅዱሳን
6.3K views19:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 22:14:59 በኢ/ኦ/ተ/ቤ የሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ የዓለም አቀፍ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ፲፪ኛው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ከግንቦት 26-27 ቀን 2015 ዓ.ም አከናውኗል።

ጉባኤው የሀገረ ስብከቶች የሰ/ት/ቤት ተወካዮችን በማካተት የተከናወነ ሲሆን በጉባኤው ላይ ከቀረቡ ሪፖርቶች ፣ ጥናታዊ ሰነዶች እና ከተከናወኑ ውይይቶች በመነሳት ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

የአቋም መግለጫ ፦

1. በ12ኛው ጠቅላላ ጉባኤ የቀረበውን ሪፖርትና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተቀብለን አጽድቀናል ለትግበራው በጋራ እንሰራለን፡፡
2. ከጠቅላይ ቤተክህነት ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሀገር አቀፍ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት እስከ አጥቢያ ሰ/ት/ቤት የቀረበውን የአደረጃጀት መዋቅር በጥልቀት ገምግመናል፡፡ በጉባኤው የተሰጡ ማስተካከያዎችን በማካተት ወደ ስራ እንዲገባ ወስነናል፡፡
3. የሥርዓተ ትምህርት መጻሕፍትን ለማሳተም የበጀት እጥረት እንዳለ ተገንዝበናል፡፡ ይህንን ከቅዱስ ሲኖዶስ እስከ ሀገረ ስብከት ያሉ የቤተክርስቲያን መሪዎች በመገንዘብ ለሕትመቱ ተዘዋዋሪ በጀት /Revolving budget/ እንዲፈቀድና የተዘጋጁ መጻሕፍት ወደ ሕትመት እንዲገቡ በየደረጃው ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄ እንዲቀርብና ክትትል እንዲደረግ በአጽንዖት እንጠይቃለን፡፡
4. ሀገሪቱ ላይ በሚከሰቱ የተለያዩ አለመግባባቶች ምክንያት ያለ እዳዋ እዳ የተሸከመችው ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን በአቢያተ ክርስቲያኗ ላይ የሚደርሰው መቃጠልና መዘረፍ ፤ በምእመናን እንዲሁም በሰንበት ት/ቤት ወጣቶቻችን ላይ የሚደርስ የህይወት መጥፋት ፤ የአካል መጉደልና መሳደድ እንዲቆም የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ እንጠይቃለን፡፡
5. በተለያየ ምክንያት የቤተ ክርስቲያንን መምህራን እና አገልጋዮችን ማሰር እንዲቆም የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ እንጠይቃለን፡፡
6. የቤተክርስቲያናችን አንድነት ተጠብቆ ምዕመናን ከመደናገር ወጥተው ሥርዓተ አምልኮ በነጻነት መፈጸም ይችሉ ዘንድ ይቅርታና ሰላምን ሲያስተምሩ የኖሩ የትግራይ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳትና የአስተዳደር አካላት ለቤተክርስቲያን አንድነትና ለምዕመናን ሲሉ ወደ ውይይትና ይቅርታ እንዲመለሱና ቅዱስ ሲኖዶስ ያቀረበውን የሰላም ጥሪ እንዲቀበሉ በልጅነት መንፈስ እየጠየቅን ቅዱስ ሲኖዶስና በአንጻራዊ ሰላም ውስጥ ያለው የቤተ ክርስቲያን መዋቅር በትግራይ በተፈጠረው ጦርነት ለተፈጠረው ችግር ተገቢውን ድጋፍ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ እንጠይቃለን፡፡
7. በቃለ አዋዲ የተደነገገው የሰበካ አስተዳደር መንፈሳዊ ጉባኤ አደረጃጀት ከአጥቢያ ቤተክርስቲያን በቀር እየተተገበረ አለመሆኑ በቤተክርስቲያን አስተዳደራዊ ሂደት ላይ ክፍተት እንደፈጠረ በጉባኤው በጥልቀት ተነስቷል፡፡ስለሆነም ከወረዳ ቤተክህነት እስከ ጠቅላይ ቤተክህነት ድረስ በቃለ አዋዲው መሰረት የካህናት ፣ የምዕመናን እና የሰንበት ት/ቤት አባላት ተሳትፎ እንዲከበር በታላቅ አጽንዖት እንጠይቃለን፡፡
8. ሥርዓተ አምልኮ ለመፈጸም ፤ ልጆች ወልዶ ለማሳደግ እና ተተኪ ትውልድ ለማፍራት ሀገር ያስፈልጋል፡፡ በሀገር ውስጥም ሰላም ከሌለ ምንም ማከናወን አይቻልምና በመላው ሀገሪቱ በተቃርኖ የሚገኙ አካላት በሚያርጉት ጦርነትና የእርስ በእርስ ግጭት ምክንያት ንጹሐን ዜጎች ሕጻናት ፣ ሴቶችና ካህናት ላይ የሚደርስ እንግልትና ጉዳት እየከፋ መምጣቱን በመገንዘብ ልዩነታቸውን በውይይት እና በድርድር ብቻ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡
9. ከሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ችግሮች በፍጹም ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን የሚመጥኑ ሆነው አላገኘናቸውም፡፡ በመሆኑም ሲመቱ ሕገ ቤተክርስቲያንን ፣ ፍትሐነገሥትን እና ቃለ አዋዲን ባከበረና ባከበረ መልኩ #ብቻ እንዲደረግ በልጅነት መንፈስ እንጠይቃለን፡፡
10. በቤተክርስቲያናችን የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በተለያዩ የቤተ ክርስቲያን አካላት ተጠንተው የሚቀርቡ የመፍትሔ ሀሳቦችን ቅዱስ ሲኖዶስ በምክረ ሃሳብነት እንዲቀበላቸውና ፤ በማዳበር እንዲተገበሩ አቅጣጫ እንዲሰጥ ከጠቅላይ ቤተክህነት ጀምሮ ያሉ የቤተ ክርስቲያን መዋቅር አካላት የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ያለምንም መሸራረፍ ተግባራዊ እንዲያደርግ በአጽንዖት እናሳስባለን፡፡
11. በቤተክርስቲያናችን ውስጥ የሚስተዋሉ የአስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ በሚያስችሉ ሥራዎች ላይ ሁሉ በመሳተፍና እንደ ቤተክርስቲያን ተተኪ ልጅነታችን የበኩላችንን ኃላፊነት በባለቤትነት መንፈስ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ አጥቢያ ባለዉ መዋቅር ትኩረት ሰጥተን የምንሠራ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ምንጭ
የሰንበት_ትምህርት_ቤቶች_አንድነት
5.8K views19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 22:14:57
5.1K views19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ