Get Mystery Box with random crypto!

ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)

የቴሌግራም ቻናል አርማ mahibere_kidusan — ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)
የቴሌግራም ቻናል አርማ mahibere_kidusan — ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)
የሰርጥ አድራሻ: @mahibere_kidusan
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.91K
የሰርጥ መግለጫ

The channel of mahibere kidusan

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-05-10 12:33:22
2.8K views09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 12:33:22 ይህ ዓቢይ ተልእኮ የሰማይና የምድር መዝሙር ሆኖ ሁሌም በመደበኛ ይዘመራል፤ ጌታችንም ከሞት ከተነሣ በኋላ ያሰማው የመጀመሪያ ድምፅ  “ሰላም ለእናንተ ይሁን”  የሚል ነው፡፡

የጌታ ምርጥ ንዋይ የተባለው ቅዱስ ጳውሎስም ”ሰላም የሚቆምበትን እንከተል” ሲል የሰላምን ተቀዳሚ አስፈላጊነት በአጽንዖት አስተምሮናል፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ ሰላምን በቋሚ ምሰሶ አምሳላዊ ንጽጽር ገልጿታል፡፡
ይህም ማለት ምሰሶ የቤትን ጣራ በቋሚነት ተሸክሞና ቀጥ አድርጎ እንደሚይዝ፣ ሰላምም በተመሳሳይ የሰዎችን መንፈሳዊና አካላዊ ሕይወት ቀጥ አድርጋ የምትይዝና የምትጠብቅ መሆኗን ለመግለፅ እንደሆነ እንገነዘባለን።

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!

እኛ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከኛ በታች ያሉ ውሉደ ክህነት፣ እንዲሁም በእግዚአብሔር የልጅነት ጸጋ የከበሩ ምእመናንና ምእመናት ሁሉ፣ የቤተክርስቲያን መደበኛና ቋሚ ተልእኮ የሆነውን ሰላም የመጠበቅ፣ የማስጠበቅ፣ የማሥረጽና  የማስቀጠል ኃላፊነት እንዳለብን ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም፡፡

በእግዚአብሔርና በሰው፣ በሰውና በሰው መካከል አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም እንዲኖር ጠንክሮ የማስተማር፣ የመምከርና የማስታረቅ ኃላፊነት የእኛ ነው፡፡

ከዚህ አንጻር ዛሬ የተሰበሰብነው የተሰጠን አምላካዊ ተልእኮ ምን ያህል በተግባር አከናውነናል? ምን ሠርተናል? ምንስ ይቀረናል? ተልእኳችንን ለመፈጸም በምናደርገው ጉዞስ ምን ችግር አጋጠመን? ችግሩን ለመፍታትስ ምን እናድርግ? የሚሉትን መሠረታዊ ጥያቄዎች በማንሣት በዝርዝርና በጥልቀት በማየት ተልእኳችንን በአግባቡ ለመወጣት ነው፡፡

የቤተ ክርስቲያናችን ቀኖናም ከበዓለ ትንሣኤ በኋላ በሃያ አምስተኛው ቀን የርክበ ካህናት ዓቢይ ጉባኤ እንዲደረግ ያዘዘበት ዋና ምክንያት ይህንን እንድናደርግ ነው፡፡
ሁላችንም እንደምንገነዘበው በአሁኑ ጊዜ ቤተክርስቲያናችን እንደ ቤተ ክርስቲያን፣ ሕዝባችንም እንደ ሕዝብ በፈተና ውስጥ እያለፉ ያሉበት ጊዜ ነው፡፡

በመሆኑም ከምንም ጊዜ በላይ በአሁኑ ጊዜ በልዩ ትኩረት የምናያቸው ጉዳዮች እንዳሉ መገንዘብ ይኖርብናል፤ የቤተክርስቲያናችንና የሕዝባችን ችግሮች የተራዘሙ እንዳይሆኑ ለቤተክርስቲያናችን ምጧን ሆነን የምንሠራበት ጊዜ አሁን እንደሆነ በውል ማወቅ ይኖርብናል፡፡

ብፁዓን አበው ሊቃነጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!!

ጌታችን፡- “እንደ ርግብ የዋሆች፣ እንደ እባብም ብልሆች ሁኑ” ብሎ ያስተማረንን ጥበብ በዚህ ጊዜ በሚገባ መጠቀም ይኖርብናል፡፡በቤተክርስቲያን አጋጥመው ያሉ ችግሮች በዚህ ጥበብ ካልሆነ በቀር በመሳሳብና እልክ በመጋባት የሚፈቱ አይደሉም፡፡

በተለይም በትግራይና በኦሮምያ አካባቢዎች ያጋጠሙን ያሉ ፈተናዎች ከቤተክህነት አልፈው የሕዝብም ጭምር እየሆኑ ስለመጡ የሕዝቡን ጥያቄ በትክክል በማዳመጥ ሃይማኖቱንና ቀኖናውን በጠበቀ መልኩ በጥበብና በፍቅር ጥያቄያቸውን አክብረን መቀበል ያሻል፤ ጉዳታቸውንም መካፈል ይገባናል፡፡በአጠቃላይ አባትና እናት ለልጆቻቸው ሊያደርጉት የሚገባውን በማድረግ ልናቀርባቸውና ልናቅፋቸው ይገባል፡፡
እኛ ያጎደልነው፣ የተሳሳትነውና ያስቀየምነው ካለም ይቅርታ ለመጠየቅም ሆነ ንስሐ ለመግባት ድፍረቱ ሊኖረን ይገባል፡፡ ታረቁ፣ ይቅር በሉ፣ንስሐ ግቡ ብለን የምናስተምር እኛ ይቅርታ ለመጠየቅና ንስሐ ለመግባት ዓቀበቱ ሊከብደን አይገባም፡፡ የተከሠተው ችግር በዚህ ክርስቶሳዊ ጥበብ ሊቃለል እንደሚችል ጥርጥር የለውም፡፡

በሌላ በኩል በሀገራችን ያለው የሰላም ሁኔታ በአንድ ወገን የተረጋጋ ሲመስል በሌላ በኩል ደግሞ የመንገጫገጭ ሁኔታ እየተከሠተ እንደሆነ እያየን ነው፡፡ይህም ሂዶ ሂዶ ቤተክርስቲያንንና ሕዝብን፣ ሀገርን ልማትን መጕዳቱ የማይቀር ነው፡፡

በመሆኑም ቤተክርስቲያን ያለ ሀገርና ያለ ሕዝብ ህልውና የላትምና ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት፣ የሕዝቦቿን አንድነትና ልማት ለማረጋገጥ፣ በሃይማኖታዊ መርሕና መንፈስ፣ በገለልተኛ አቋምና በሁሉም ዓቃፊነት ስልት ለሰላም ጠንክረን መሥራት ይኖርብናል፡፡
ከዚህም ጋር የዛሬው ጉባኤ የቤተክርስቲያናችንን ዓቢይ ተልእኮ ለመፈጸም እንደመሳሪያ ሊያገለግሉ ይችላሉ ተብሎ ታምኖባቸው የተጀመሩትን ወሳኝ ሥራዎች በዝርዝር በማየት ውሳኔ የምናሳልፍበት ጉባኤ ይሆናል፡፡

ከዚህም ሌላ በተፈጠረው አላስፈላጊ ከባድ ጦርነት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የፈራረሱ አብያተ ክርስቲያናትና የተፈናቀሉ ምእመናን ልጆቻችንን በፍጥነት ደርሰን የምናጽናናበትንና የምንደግፍበትን ሁኔታ በዚህ ጉባኤ ማየት ይኖርብናል፡፡

በመጨረሻም
በአሁኑ ጊዜ አላስፈላጊ በሆነ የእርስ በርስ ግጭት እየተሳተፉ ያሉ ወገኖች ግጭቱን አቁመው በሰላማዊ ውይይት ችግሮችን ለመፍታት እንዲጥሩ አባታዊ ጥሪያችንን በአጽንዖት እያስተላለፍን የ፳፻፲፭ ዓ.ም የርክበ ካህናቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በጸሎት የተከፈተ መሆኑን ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምእመናንና ምእመናት እናበስራለን።

እግዚአብሔር ጉባኤያችንን ይባርክልን!
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ !!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር !!!
አሜን፡፡

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ግንቦት ፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓመተ ምሕረት
አዲስአበባ - ኢትዮጵያ
2.7K views09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 12:33:22
''በቤተክርስቲያን አጋጥመው ያሉ ችግሮች በዚህ ጥበብ ካልሆነ በቀር በመሳሳብና እልክ በመጋባት የሚፈቱ አይደሉም፡፡''

የቅዱስ ፓትርያርኩ የግንቦት 2015 ዓ.ም ርክበ ካህናት ጉባኤ መክፈቻ ንግግር።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና በሰሜን አሜሪካ የኒዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣
ብፁዕ አቡነ ሔኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ
አባላት፣

የሰላም አለቃ፣የምሕረት አባት የሆነው ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድስት የሆነችውን በዓለ ትንሣኤውን አክብረን ይህንን የረክበ ካህናት ቀኖናዊና ሲኖዶሳዊ ጉባኤ እንድናካሂድ ስለሰበሰበን ክብርና ምስጋና፣ አምልኮና ውዳሴ ለእሱ በማቅረብ፣እንኳን ደኅና መጣችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡

“ወይእዜኒ ንትልዋ ለሰላም በዘይት ሐነጽ ቢጽነ፡-እንግዲያው ስለሰላም የሚቆምበትን እርስ በርሳችንም የምታነጽበትን እንከተል” (ሮሜ. ፲፬፥፲፱)፤

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!

በቅዱሳት መጻሕፍት በግልፅ እንደተቀመጠው እኛ የምናገለግላት ቤተክርስቲያን በምድር ያለች የእግዚአብሔር መንግሥት ማእከል ናት፤ የተመሠረተችውም በደመ ክርስቶስ ነው፡፡
የእግዚአብሔር መንግሥት ማእከል የሆነችው ቤተክርስቲያን ልትሰራው፣ልትጠብቀውና ልትፈጽመው የተሰጣት ዓቢይ ተልእኮ አለ፤ እሱም በእግዚአብሔርና በሰው፣ በሰውና በሰው መካከል ፍጹም ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ ነው፤''በቤተክርስቲያን አጋጥመው ያሉ ችግሮች በዚህ ጥበብ ካልሆነ በቀር በመሳሳብና እልክ በመጋባት የሚፈቱ አይደሉም፡፡''
2.0K views09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 12:33:21 “የሕይወት ቀን” በግቢ ጉባኤያት

ወርቃማው የወጣትነት ዘመናችን በተስፋ፣ በመልካም ምኞትና በትጋት የተሞላ፣ ዕውቀትንና አቅምን ያማከለ ማንነታችን የሚታነጽበት፣ መንፈሳዊነታችን የሚገለጽበት የዕድሜ ክልል እንደመሆኑ የሕይወታችን መሠረት ነው፡፡ መንፈሳዊ ፍሬን አፍርተን ርስተ መንግሥተ ሰማያት ለምንወርስብትም የሕይወት ስንቅ የምንሰንቅበት የተጋድሎ ዘመን ስለመሆኑ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከልጅነታችን ጀምሮ አበክራ ታስተምረናለች፡፡ በሰንበት ትምህርት ቤቶቿም ኮትኩታ አሳድጋ መንፈሳዊ ፍሬ ለማፍራት ታበቃናለች፡፡ ለዚህ የመሸጋገሪያ ዕድሜ በደረስንበት ጊዜም የሕይወታችን መርሕ የሆነው ትምህርተ ወንጌል እንዳይጓደልብን በዐውደ ምሕረቷ ላይ ጉባኤ ዘርግታ ሰማያዊ ኅብስትን አዘጋጅታ ትመግበናለች፡፡

በጉባኤያት የሚሰበኩ ትምህርቶች ለክርስቲያናዊ ሕይወት እንድንበቃ የሚረዱንና ለዘለዓለማዊ ሕይወት የሚያበቁን ናቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን የምትመግበን ምግበ ሕይወት ግን በዚህ ብቻ አይወሰንም፡፡ ዘወትር መንፈሳዊ ዝለት አጋጥሞን ከቤቷ እንዳንርቅና በዓለም እንዳንጠፋ ዓለም ባፈራቻቸው የመገናኛ ብዙኀን በየቤታችን፣ በትምህርት ቤታችንና በየአካባቢያችን የሕይወትን ምግብ እየመገበች ታኖረናለች፡፡ ቅዱስ ቃሉን ሰምትንም ለሥጋ ወደሙ እንድንበቃ ምሥጢራቷን ታካፍለናለች፡፡

ለዚህም ተልእኮ ተደራሽነት በሀገራችን የመንፈሳዊ አገልግሎት ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠው ማኅበረ ቅዱሳን በግቢ ጉባኤ አገልግሎቱ ውስጥ ለኦርቶዶክሳዊያን ወጣት ተማሪዎች ከሚሰጠው ሥርዓተ ትምህርት በተጨማሪ ከምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ይካፈሉ ዘንድ ዘወትር እሑድ የሚቀርበው “የሕይወት ቀን” ተጠቃሽ ነው፡፡ በዓመት በሁለቱ የአጽዋማት ወቅት በነቢያትና በዐቢይ ጾም የሚካሄደው ይህ አገልግሎት በአብዛኛው የከፍተኛ ተቋማት ተማሪዎች የሚሳተፉበት ነው፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎችን መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ከማስተማር ባሻገር በንጽሕና ሕይወት ኖረው ለቅዱስ ቁርባን እንዲበቁ ለማድረግ ባለው ቁርጠኛ ሐሳብ በጀመረው በዚህ መርሐ ግብር በተለይም በአዳማ፣ በሐሮማያ፣ በጎንደር እና በሌሎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገኙ የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎችን የንስሓ አባት ከማስያዝ ጀምሮ ሥጋ ወደሙ እንዲቀበሉ ይረዳቸዋል፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው” በማለት እንደተናገረው እኛ ክርስቲያኖች በንስሓ ሕይወት ተመላልሰን ለሥጋ ወደሙ እንድንበቃ የአምላካችን ቅዱስ ቃል ይገልጻልና የተማርነው ትምህርትም ይሁን የምንኖረው ክርስቲያናዊ ሕይወት ፍጻሜው ቅዱስ ቁርባን በመሆኑ ተማሪዎቹ ይህንን ተረድተው እንዲተገብሩት ማኅበራቸው ማኅበረ ቅዱሳን እገዛ ያደርግላቸዋል፡፡ (ዮሐ. ፮፥፶፫)
ይህን ተልእኮ ለመፈጸም በግቢ ጉባኤያት ለአገልግሎት የተመደቡ መምህራንና ሰባኬ ወንጌላውያን ተማሪዎቹን ለቅዱስ ቁርባን ዝግጁ እንዲሆኑ የእግዚአብሔርን ቃል ከማስተማር ባሻገር አስቀድመው በንስሓ አባቶቻቸው አማካይነት ንስሓን እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡ ከዚህም ቀጥሎ ለአንድ ሳምንት ያህል ሥርዓተ ንስሓን የሚፈጽሙበት “የንስሓ ሳምንት መርሐ ግብር” ይከናወናል፡፡ ተማሪዎች አስፈላጊውን ሥርዓት ተከትለውና በምክረ ካህን ታግዘውም ቅድመ ዝግጅታቸውን ሲያጠናቀቁ ሥራ አስፋጻሚ ቢሮው ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናቱ ጋር በመነጋገር በተለይም በዐበይት የአጽዋማት ወቅቶች ማለትም በዐቢይ ጾመና በጾመ ነቢያት ሥጋ ወደሙ ከሚቀበሉበት ዕለተ እሑድ ዋዜማ የአዳር መርሐ ግብር በማዘጋጀት ትምህርተ ወንጌልና ውይይት ያደርጋል፡፡
በመቀጠልም በቤተ ክርስቲያናቱ ተገኝተው ሥርዓተ ቁርባን እንዲካፈሉ ካደረገ በኋላ ከመምህራኑ ጋር በመተባበር ማኅበሩ የአጋፔ መርሐ ግብር አዘጋጅቶ ያቀርብላቸዋል፡፡ የአጋፔ መርሐ ግብሩንም ተከትሎ የተለያዩ መርሐ ግብራትን በማዘጋጀት የሕይወት ምግብን እንዲመገቡ ያደርጋል፡፡ ቀሪው ዘመናቸውን በሃይማኖት ጸንተው አንዲኖሩና እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ድረስ ለቅዱስ ቁርባን የበቁ እንዲሆኑ ለመርዳት የድኅረ ጉባኤያት መርሐ ግብር አዘጋጅቶም የማያቋርጥ እገዛ ያደርግላቸዋል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን በግቢ ጉባኤያት ያስመረቃቸው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች የቀና መንፈሳዊ ሕይወትም ጉዳዬ ብሎ የያዘው ተልእኮው በመሆኑ ማኅበረ ቅዱሳን በየጊዜው ይህን ሥራውን ለማከናወን የሚረዱ መርሐ ግብራትን ያዘጋጃል፡፡ በተለይም ተልእኮውን ተደራሽ ለማድረግ የሚረዱ የዐቅም ማጎልበቻ ሥራዎችና ለአገልግሎቱ ስኬት እክል የሚሆኑ ችግሮችን የመፍታት ሥራ እየሠራ ይገኛል፡፡ ማኀበሩ ለዚህ እንደ መነሻ ያደረገው በ፳፻፲፫ የተጠናው ጥናት እንደሚያሳየው ከሆነ የመምህራን አቅም ማጎልበቻ ሥልጠናዎች እጥረት፣ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች የመማርያ ግብአቶች አለመሟላት እንዲሁም ሌሎች ውስጣዊ እና ውጫዊ ተግዳሮቶች በመሆናቸው ይህን ችግር ለመቅረፍ የሚያግዙትን ተግባራት በመለየት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

ስለሆነም ይህን ተግዳሮት ለማከናወን ማኅበሩ የበጎ አድራጊ ግለሰቦችም ሆነ ድርጅቶች እገዛ እንደሚያስፈልጉት በማመን በዚህ በያዝነው የግንቦት ወር ባወጣው ዕቅድ መሠረት የ፳፻፲፭ ዓ.ም የግንቦት ልደታ ለማርያምንበዓል “ግንቦት ልደታን ለግቢ ጉባኤ” በሚል ርእስ መርሐ ግብር አዘጋጅቷል፡፡ በዋናው ማእከል ደረጃ ከሚያዝያ ፳፰/ ፳፻፲፭ ዓ.ም እስከ ግንቦት ፮ /፳፻፲፭ ዓ.ም ድረስ ይህ መርሐ ግብር ይከናወናል፡፡ በዋነኛነትም የማኅበሩን የ፴፩ ዓመት አገልግሎት የግቢ ጉባኤ ፍሬዎችን አስተዋጽዖ ለቤተ ክርስቲያን፣ ለምእመናን፣ ለተማሪ ወላጆች፣ ለሀገር እና ለዓለም በማስተዋወቅ ነው፡፡

የማኅበረ ቅዱሳንን የግቢ ጉባኤያት መርሐ ግብርን መደገፍ የተማሪዎችን መንፈሳዊ ሕይወት መርዳት ብቻ ሳይሆን ጠቀሜታው ለሀገር፣ ለቤተ ክርስቲያንና ለሁላችንም ጭምር በመሆኑ ተገቢውን እገዛ የማድረግ ኃላፊነት አለብን፡፡ ለዚህም የአምላካችን የልዑል እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ እንዲሆንልን በጸሎት ማሳሰብም ተገቢ ነው፡፡

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!
2.1K views09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 01:16:07
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ የጳጳሳት ሹመትን ጨምሮ የምእመናን ድርሻ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ተሳትፏቸው የጎላ እንዲሆን ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ያነጋገራቸው በአዲስ አበባ የሚኖሩ አገልጋዮችና ምእምናን ጠየቁ።

የመንፈስ ቅዱስ ፍቃድ ሆኖ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊና ሳይፈቱ የቆዩ ጉዳዮች መፍትሔ የሚያገኙበት እንዲሆን ፍላጎታቸው እንደሆነም ተናግረዋል።

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በርካታ ቸግሮችን ብታልፍም በጥር 14/2015 ዓ᎐ም የታየው ሕገ ወጥ ሹመት ግን የችግሮቻችን ውጤት ትልቅ ማሳያ ነው ሲሉም አስተያየት ሰጭዎቹ ገልጸዋል።

አባቶቻችን እግዚአብሔር በሰጣቸው ስልጣንና በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ቤተ ክርስቲያን ወደ ዳግም ጥቁር ታሪክ እንዳትመለስ ማድረግ አለባቸውም ብለዋል።

በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረትም እንደጳጳሳት ሹመት አይነት የምእምናን ድርሻ ያለባቸው ጉዳዮች ላይ ምእመናን እስከአጥቢያ ድረስ እንዲወያዩና ድምጻቸው እንዲሰማ እድል መሰጠት እንዳለበትም አጽንዖት ሰጥተዋል።

የ2015 የግንቦት ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ግንቦት 1 በጸሎት ተከፍቷል።
3.3K views22:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 21:43:27 Waldaan Qulqullootaa buaa baii fi haalota mijatoo dabarse  kauumsa taasisuun Mana Kiristaanaa fi biyyaaf tajaajila fooyyaaa kennuuf ejjennoo cimaa qabu buuureffachuun  yaaiiwwan mooraa jajjabeessuun, rakkoowwan mudatan furuun tajaajila yeroo madaale  akka raawwatamuuf “Caamsaa tokkoo yaaii mooraa keenyaaf” buura jedhuun kabajuuf murteessuu isaa Obbo Abbabaan ibsaniiru.

Obbo Abbaabaan ibsa isaaniitiin “Baroota tajaajilaa darban kanatti jijjiiramootni buaa qabeeyyii mulatan  caalatti tajaajilaaf kan kakaasan waan taaniif; jechuunis barattoota lakkoofsaan hedduu taan sirna barnootaa bocuun barsiisuun, mana barumsaa  Aabinnatii (Abbummaa) baratanii tajaajila Mana Kiristaanatti akka hirmaatan taasisuun, yeroo isaanii seeraan fayyadamuun barnoota idilee  isaanitti cimanii badhaafamtoota geebaa fi warqee horachuu isaatiin, dhaloota namuusa  gaariin ijaaramani Mana Kiristaanaa fi biyya kan tajaajilan horachuun, barsiisota bakka buan horachuun, k.k.f. tajaajila yeroo isaa eeggate kennuuf akka kakaumsa qabaatu taasiseera’ jedhan.

Eebla 28 hanga Caamsaa 6/2015 tti Sagantaalee  jiran  irrattis caalatti jijjiiramoota gaarii yaaii mooraa itti fufsiisuuf, rakkinoota jiran furuu fi tajaajila isaa cimsuuf sagantaan galii sassaabuu akka jiru  himaniiru.

Sagantaa galii sassaabuu kana irratti barattoota yaaii mooraa, maatiwwan barattootaa fi kanneen yaaii mooraa irraa eebbifamanii hojii fi tajaajila garaagaraa irratti bobbaan  irraa sagantaan galii sassaabuu akka karoorfame obbo Abbabaan beeksisaniiru.

Waldaan Qulqullootaa biyya keessatti wiirtuuwwan 48, biyyaa alaa wirtuuwwan 4 yoo qabaatu walumaagalatti yaaiiwwaan moora 452 (biyya keessa 435, biyya alaa 23) akka qabu ragaaleen ni mul’isu.
3.1K views18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 21:43:27
አንገብጋቢ ሁኔታዎች ባሉበት ኹኔታ የአባቶቻችን ስለሢመትና ሽልማት መነጋገርም ሆነ በተግባር መፈጸም ጊዜውን ያልዋጀ ሀገርና ሕዝብ ለደረሰባቸውና ለተጋረጠባቸው አደጋ ቤተ ክርስቲያን ትኩረት እንዳልሰጠች የሚያስቆጥር ነው ብለን እናምናለን።

ያ ሳይሆን ቀርቶ አባቶቻችን በየትኛውም ኃይል ሊደረግባቸው ለሚችል ተጽዕኖ እጅ ሰጥተው ሕገ ወጦችንም ሆነ ሌሎችን ለመሾም ውይይት ቢያደርጉና በተግባርም ቢፈጽሙ ቤተ ክርስቲያን አሁን ባላት ችግር ላይ ሌላ መጨመርና በቁስሏ ላይ ጨው እንደመነስነስ ሆኖ ይሰማናል።

አባቶቻችን ይህንን ቢፈጽሙ በታሪክ ተጠያቂ ይሆናሉ።

የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ማኅበረ ካህናትና ምእመናን
2.5K views18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 21:43:26 በጥሪቃም ለሚስቱ ሔዶ የሕልሙን ፍቺ ነገራት፡፡ በዚያም ወር የመጀመሪያዋ ሴት ልጅ ተፀነሰች፡፡ በተወለደች በ፰ኛው ቀን ሄኤሜን አሏት፤ ወላጆቿም በሥርዓት አሳደጓት፡፡ እርሷም ለአቅመ ሔዋን ስትደርስ ባል አግብታ ሴት ልጅ ወለደች፤ የሄኤሜን ልጅም ዴርዴን ትባል ነበር፡፡ ዴርዴንም እንዲሁ አድጋ ቶና የምትባል ሴት ልጅ ወለደች፡፡ ቶና ደግሞ ሲካርን ወለደች፤ሲካርም ሔርሜላን ወለደች፤ ሔርሜላም በሥርዓት አድጋ ባል ካገባች በኋላ ሐና የተባለች ልጅ ወለደች፤ሐና ማለትም በሃይማኖትና በምግባር የጸናች፤ በንጽሕና በቅድስና የኖረች ቡሩክት ክብርት ልዕልት ማለት ነው፡፡ የሐና ወላጆች ልጃቸውን በሥርዓት አሳደጓት፡፡ ለአካለ መጠን ስትደርስም ኢያቄም የተባለውን ጻድቅ ሰው አጋቧት፡፡ ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑም ኖረዋለወ። በዚያ ወራት የመካኖች መብዓ ካህናቱ አይቀበሉም ነበርና፡፡ እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኅዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር፡፡ እናም ባልና ሚስቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ፤ ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ሐሳባቸውን ተመለከተ፡፡ ክቡር ኢያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኅነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው፡፡

በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ፤ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት። ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች። ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገነች። የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርገው ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች፡፡

ከዚህም በኋላ ሐምሌ ፴ ኢያቄም ለሐና ራእይ አየ፤ ነጭ ርግብ ፯ቱን ሰማያት ሰንጥቃ ወርዳ በራሷ ስታርፍ በቀኝ ጆሮዋ ገብታ በማኅፀኗ ስታድር አየ፤ ሐናም ለኢያቄም ፀምራ ሲያስታጥቀህ መቋሚያህ አብባ አፍርታ ፍጥረት ሁሉ ሲመገባት አየሁ ብላ» ነገረቸው፡፡

ነሐሴ በባተ በሰባተኛው ቀን በዕለተ እሑድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተፀነሰች፡፡ በ፶፻፬፻፹፭ ዓመተ ዓለም በግንቦት ፩ ቀንም እመቤታችን ድንግል ማርያም ከሐና እና ከኢያቄም፡፡ በ፰ኛው ቀንም ስሟን ‹ማርያም› ብለው ሰየሟት፤ በዚህ ዓለም ካሉት ምግቦች ሁሉ ጣፋጭ «ማር» በመሆኑ እንዲሁም በገነት ካሉት ምግቦች ደግሞ «ያም»ን የሚያህል ጣፋጭ ባለመኖሩ «ማርያም» አሏት፡፡ ትርጓሜውም ‹እመቤት› ነው። ‹ደግሞም ሀብታና ስጦታ› ማለት ነው፡፡ በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነትን ያገኘንባት ናትና።

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን፤ አምላካችን እግዚአብሔር ከበዓሉ ረድኤትና በረከት ይክፈለን!

ከመጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ግንቦት
2.3K views18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 21:43:26
ልደታ ለማርያም

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል አደረሰን!!!


ንጽሕተ ንጹሐን፣ ቅድስተ ቅዱሳን፣ ከተለዩ የተለየች፣ ከተመረጡ የተመረጠች ክብርት እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በከበረች ቀን ግንቦት አንድ ቀን ተወለደች፡፡ የመወለዷም ነገር እንዲህ ነው፡፡ በጥሪቃና ቴክታ የተባሉ የእግዚአብሔር ሰዎች ነበሩ፤ ባለጸጎች ቢሆንም ልጅ ግን አልነበራቸውም፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ቴክታ ሕልም አለመች፡፡ ለባሏም እንዲህ ስትል ነገረችው «በራእይ ነጭ ዕንቦሳ ከማሕፀኔ ስትወጣ፤ ያችም ዕንቦሳን እየወለደች እስከ ፮ ትውልድ ስትደርስ ፮ኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃ ደግሞ ፀሐይን ስትወልድ አየሁ» አለችው፡፡ (ውዳሴ ማርያምና ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ)

ባሏ በጥሪቃም «ራእዩስ ደግ ነው፤ የሚፈታልን የለም እንጂ» አላት፡፡ በማግሥቱ ለሕልም ፈቺ ሔዶ ነገረው፡፡ ሕልም ፈቺውም «እግዚአብሔር በምሕረቱ አይቷችኋል፤ በሣህሉ መግቧችኋል» ብሎ ፮ቱ እንስት ጥጆች መውለዳቸው ፯ ሴቶች ልጆች እንደሚወልዱ፤ ፯ኛይቱ በጨረቃ መመሰሏ ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ደግ ፍጥረት እንደሚወለዱ፤ የፀሐይ ነገር ግን እንደንጉሥ ያለ ይሆናል አልተገለጸልኝም ብሎ ነገረው፡፡ (ነገረ ማርያም)
2.1K views18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 21:43:26 በዚህም ተማሪዎች ተመርቀው ሲወጡ በሥነ ምግባር የታነጸ ትውልድ በመፍጠር የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አደራ ተቀብለው እንዲወጡ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ በሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችና በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የአንገት ማተብና መስቀል ይደረግላቸዋል፡፡

ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በከፍተኛ ውጤት የሚመረቁ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችም “ለውጤታማነታችን ትልቁን ድርሻ የሚወስደው ማኅበረ ቅዱሳን ነው” በማለት የተሸለሙትን ሜዳልያ እና ዋንጫቸውን ለማኅበረ ቅዱሳን በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜም የተሸለሙትን ሜዳልያ ለማኅበረ ቅዱሳን በመስጠት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የኩላሊት ንቅለ ተከላ ሒኪም የሆኑት ፕሮፌሰር እንግዳ አበበ ይጠቀሳሉ፡፡ ወደ ሥራ ሲሠማሩም ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው ጸጋ መልሰው ቤተ ክርስቲያንን እንዲያገለግሉ፣ በሚሠማሩበት የሥራ መስክም በታማኝነትና በቅንነት እንዲያገለግሉ አስችሏቸዋል፡፡ በቅድስት ቤተ ክርሰቲያን መዋቅር ውስጥ በመግባትም በሰ/ት/ቤቶች እና በሰበካ ጉባኤያት እንዲሁም በአብነት ትምህርት ገፍተው ዲቁና ተቀብለው የሚወጡትም በቤተ ክርስቲያን በውስጥ አገልግሎት እንዲሳተፉ ማድረግ ተችሏል፡፡

የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች ከተከታታይ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት በተጨማሪ በግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ አማካይነት “ጉባኤ ቃና” የተሰኘ ተማሪ ተኮር መረጃዎችን የያዘ መጽሔት ከ፳፻ ዓ.ም ጀምሮ በማሳተምና መልሶ ለተማሪዎች በማሠራጨት፣ በምረቃ መጽሔት፣ በድረ ገጽ፣ በፌስቡክ፣ በቴሌግራም ሃይማኖታቸውን ጠንቅቀው እንዲረዱ እገዛ ሲደረግላቸው ቆይቷል፡፡

በበጎ አድራጎት ተግባራትም የመንፈሳዊ ጉዞ መርሐ ግብር፣ ነዳያንን መመገብ፣ አረጋውያንን መንከባከብ፣ ለሕፃናት የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት፣ አብያተ ክርስቲያናት እና የስብከተ ወንጌል አዳራሾችን በማነጽ፣ … ወዘተ ተግባራትን በማከናወን ረገድ ግቢ ጉባኤያት አርአያ የሚሆኑ ሥራዎችን ሠርተዋል ወደፊትም በተጠናከረ ሁኔታ ይቀጥላሉ፡፡

ግቢ ጉባኤያትን ለማስተማርና ብቁ ዜጋ አድርጎ ለመቅረጽ የማኅበረ ቅዱሳን ድርሻ ከፍተኛውን ቦታ የሚይዝ ሲሆን እንዚህን ሥራዎች ለመሥራት በሚደረገው ጥረት ውስጥ በርካታ ችግሮችም በእግዚአብሔር ቸርነት ታልፈው ዛሬ ላይ መድረስ ተችሏል፡፡ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህልም፡-
ውጫዊ ችግሮች ከምንላቸው ውስጥ፡- ዓለማዊነትና ሉላዊነት/Globalization/ አስተሳሰብ መስፋፋት፣ የመገናኛ ብዙኀንና ማኅበራዊ ሚዲያዎች መስፋፋት፣ የምዕራባዊ የባሕል ወረራ፣ የተማሪዎች ከኢትዮጵያዊነት እሴት ማፈንገጥ/ ውርጃ፣ ሱሰኝነት፣ ግብረ ሰዶም፣ ዝሙት፣ ሌሎችም መስፋፋት/፣ የአጽራረ ቤተ ክርስቲያን እንቅስቃሴ እና የጎሣ ፖለቲካ አስተሳሰብ መስፋፋት ይጠቀሳሉ፡፡ ውስጣዊ ችግሮችን ስንመለከት ደግሞ፡- የግብረ ገብነት መቀነስ፣ የሙስና መስፋፋት፣ ለሱስ ተጋላጭ የሆኑ ወጣቶች መበራከት፣ ዓለም አቀፋዊና ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የቤተ ክርስቲያን ተሳትፎ አናሳ መሆን፣ ለግቢ ጉባኤያት አገልግሎት በብዛትና በጥራት በተለያዩ ቋንቋዎች የሚያገለግሉ አገልጋዮች እና መምህራን ያለመኖር እንደ ችግር የሚታዩ ናቸው፡፡

ግቢ ጉባኤያት ማኅበረ ቅዱሳን ወደፊት አገልግሎቱን በማጠናከር ተቋማዊ ለውጥን በመተግበር የሚታዩ ችግሮችን በመፍታት ልዩ ትኩረት ሠጥቷቸው ከሚሠራባቸው ዘርፎች አንዱ ነው፡፡ በዚህም መሠረት የጉባኤ ቤት ደቀ መዛሙርትን ለግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማሠልጠን፣ ኢ-መደበኛ መምህራንን በማእከላት ማፍራት፣ መደበኛ መምህራንን እና የአብነት መምህራንን መቅጠር፣ ከአንድ በላይ ተጨማሪ ቋንቋ ለሚያስተምሩ እና ለሚያሠለጥኑ መምህራን የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና መስጠትና ማሠማራት፣ ተተኪ መምህራንን በደረጃ ፫ በልዩ ሁኔታ ማሠልጠን፣ ግቢ ጉባኤያት ተኮር የአንድ ሰዓት የብሮድ ካስት መርሐ ግብር ሥርጭት መጀመር እና የመሳሰሉት አገልግሎቶች ተግባራዊ ይደረጋሉ፡ ፡ በዚህም የወደፊት ተስፋችን በቅንነትና በታማኝነት ሀገርንና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የሚረከቡ እንዲሁም ሊያገለግሉ የሚችሉ በሁለት ወገን ማለትም በዓለማዊውም ሆነ በመንፈሳዊው ዘርፍ የተሣለ ሰይፍ ሆነው የሚወጡ ወጣቶችን ማፍራት ነው፡፡

በዚህም መሠረት የግቢ ጉባኤያትን አገልግሎት ለማጠናከር “ግንቦት ልደታን ለግቢ ጉባኤያት” በሚል መሪ ቃል ከሚያዚያ ፳፰ እስከ ግንቦት ፮ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ልዩ ልዩ መርሐ ግብራትን በማዘጋጀት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ በተለይም በግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ውስጥ የሚያጋጥመው የፋናንስ እጥረት ለመቅረፍ ከበጎ አድራጊ ምእመናን፣ ከግቢ ጉባኤያት ተመርቀው በልዩ ልዩ ሥራ ላይ የሚገኙ ወንድሞችና እኅቶች፣ ሌሎችም ተባባሪ አካላት ድጋፍ ለማሰባበሰብ እየሠራ ይገኛል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
2.1K views18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ