Get Mystery Box with random crypto!

ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)

የቴሌግራም ቻናል አርማ mahibere_kidusan — ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)
የቴሌግራም ቻናል አርማ mahibere_kidusan — ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)
የሰርጥ አድራሻ: @mahibere_kidusan
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.91K
የሰርጥ መግለጫ

The channel of mahibere kidusan

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 63

2022-07-14 20:14:49
“የብዙ ትውልድ መሠረት ይታነጻል” ኢሳ58፡12
እንኳን ለማኅበረቅዱሳን አዲስአበባ ማእከል 28ኛው ጠቅላላ ጉባኤ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!ማእከሉ የ2014 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤውን ሐምሌ 16 እና 17 በታላቅ ድምቀት ያካሒዳል።

በዕለቱም በካህናት አባቶች ለቤተክርስቲያንና ለአገር ጸሎት ይደረሳል፣ያሬዳዊ ዝማሬ፣ትምህርት ወንጌልና የመዋቅር ለውጥ ውይይት ይደረጋል።ከዚህ በተጨማሪም በሁለቱም ቀናት የደም ልገሳ መርሐግብር ይኖረናል፡፡ሁላችንም በመገኘት መንፈሳዊ ግዴታችንን እንወጣ!

ቀን፡- ሐምሌ 16 እና 17 2014 ዓ.ም
ቦታ፡-ማኅበረቅዱሳን ሕንፃ 3ኛ ፎቅ
1.9K views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 20:14:49
1.7K views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 20:14:49
በዚህችም ቀን የሮሜ ከተማ ሊቀጳጳሳት ቅዱስ አግናጥዮስ በሰማእትነት ዐረፈ። ይህም በከሀዲው ንጉሥ በጠራብያኖስ ዘመን ሆነ። ንጉሡም አቅርቦ ለአማልክት እንዲሰዋ ጠየቀው ብዙ ቃልኪዳኖችንም በመግባት አባበለው።ባልተቀበለውም ጊዜ ለአንበሶች ሰጠው።

ያን ጊዜም ቅዱስ አግናጥዮስ በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ ሕዝቡን አዘዛቸው።ከዚህም በኋላ አንዱ አንበሳ ቀርቦ አንገቱን ያዘው ያን ጊዜም ክብር ይግባውና በጌታችን እጅ ነፍሱን ሰጠ።ምእመናንም መጥተው ሥጋውን ወስደው በመልካም ቦታ አኖሩት።
በረከቱ ይደርብን!
1.8K views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 19:25:18
On this day took place the martyrdom of the two great apostles,chief of the apostles, Peter and Paul. May their blessings be up on us.
2.8K views16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 19:25:18
ሐምሌ ፭ ቀን በዚህች ቀን የክቡራንና የዐበይት አባቶቻችን ሐዋርያት የጴጥሮስና የጳውሎስ የሰማእትነታቸው መታሰቢያ ነው።
2.7K views16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 11:52:20
3.8K views08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 10:18:53
4.2K views07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 10:18:52 ሐምሌ፪ በዚህች ዕለት ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት የአንዱ ሐዋርያ የቅዱስ ታዴዎች የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። አንድ ባለጸጋ ግመልን ከነባለጸጋው በመርፌ ቀዳዳ ያሳለፈ ነው።

አንድ ገንዘብ የሚወድ ጐልማሳ ባለ ጠጋም ወደ ሐዋርያው ታዴዎስ መጥቶ ሰገደለትና ‹‹የእግዚአብሔር አገልጋይ ሆይ! እድን ዘንድ ምን ላድርግ?›› ሲል ጠየቀው፡፡ ሐዋርያውም ‹‹እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ኀይልህ ውደደው፡፡ አትግደል፤ አትስረቅ፤ አታመንዝር፡፡ በአንተ ሊደረግብህ የማትሻውን በሌላው ላይ አታድርግ፡፡ ደግሞም ገንዘብህን ሸጠህ ለድኆችና ለምስኪኖች ብትሰጥ በሰማያት ለዘለዓለም የሚኖር ድልብ ታገኛለህ›› በማለት ሕገ ወንጌልን አስተማረው፡፡ ጐልማሳውም ትምህርቱን በሰማ ጊዜ ተቈጥቶ ሐዋርያውን አነቀው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ‹‹የክርስቶስን አገልጋይ እንዴት ደፍረህ ታንቃለህ?›› ባለው ጊዜ ጐልማሳው ቅዱስ ታዴዎስን ለቀቀው፡፡ የእግዚአብሔር ኀይል በይረዳው ኖሮ ሐዋርያው ከመታነቁ ጽናት የተነሣ ዓይኖቹ ሊወጡ ነበር፡፡

ያን ጊዜም ቅዱስ ታዴዎስ ‹‹ጌታችን ‹ሀብታም መንግሥተ ሰማያት ከሚገባ ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል› ሲል በእውነት የተናገረው እንዳንተ ላለው ሀብታም ነው›› አለው፡፡ ጐልማሳውም ‹‹ይህ ሊኾን አይችልም!›› ባለ ጊዜ ሐዋርያው ታዴዎስ በመንገድ ሲያልፍ ያገኘውን ባለ ግመል አስቁሞ መርፌ ገዝቶ ሊያሳየው ወደደ፡፡ መርፌ ሻጩ ሐዋርያውን ለመርዳት ፈልጎ ቀዳዳው ሰፊ የኾነ መርፌ አመጣለት፡፡ ቅዱስ ታዴዎስም ‹‹እግዚአብሔር ዋጋህን ይክፈልህ፤ ነገር ግን በዚህች አገር የእግዚአብሔር ክብር ይገለጥ ዘንድ ቀዳዳው ጠባብ የኾነ መርፌ አምጣልን›› አለው፡፡ ቀዳዳው ጠባብ የኾነውን መርፌ ቅዱስ ታዴዎስ ተቀብሎ ‹‹ኀይልህን ግለጥ›› ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፡፡ እጁንም ዘርግቶ ባለ ግመሉን ‹‹በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከግመልህ ጋር በመርፌ ቀዳዳው ውስጥ እለፍ›› አለው፡፡ ሰውየውም እስከ ግመሉ ድረስ በመርፌ ቀዳዳው አለፈ፡፡

የሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስ በረከቱ ይደርብን!
4.5K views07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 14:53:56
3.9K views11:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 14:53:56 ሰኔ ፴ ልደቱ ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
በንጉሥ ሄሮድስ ዘመን ዘካርያስ የሚባል ካህን ነበር፤ ሚስቱም ኤልሣቤጥ መካን ስለነበረች ልጅ አልነበራቸውም፤ እርሷም የመውለጇ ዘመን አልፎ ነበር፡፡ ሆኖም ሁለቱም በእግዚአብሔር የታመኑ ጻድቃን ነበሩ፡፡ 
ከዕለታት በአንድ ቀንም ካህኑ ዘካርያስ ወደ ቤተ መቅደስ ለአገልግሎት በገባበት ሰዓት በዕጣን መሠውያው በቀኝ በኩል የእግዚአብሔር መልአክ ቆሞ ታየው፤  እንዲህም አለው ‹‹ዘካርያስ ሆይ፥ አትፍራ፤ ጸሎትህ በእግዚአብሔር ፊት ተሰምቷልና፤ ሚስትህ ኤልሣቤጥም ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ፡፡ ደስታና ሐሤትም ይሆንልሃል፤ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል፡፡ እርሱ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ይሆናልና የወይን ጠጅና የሚያሰክርም መጠጥ ሁሉ አይጠጣም፤ ከእናቱ ማሕፀን ጅምሮም መንፈስ ቅዱስ ይመላበታል፡፡ ከእስራኤልም ልጆች ብዙዎቹን ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር ይመልሳቸዋል፡፡ እርሱም የአባቶቻችን ልብ ወደ ልጆች፥ የከሓዲያንንም ዐሳብንም ለእግዚአብሔር የተዘጋጀ ያደርግ ዘንድ በኤልያስ መንፈስ ቅዱስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል፡፡›› ዘካርያስም መልአኩን እንዲህ አለው፤ ‹‹ይህ እንደሚሆን በምን አውቃለሁ? እነሆ፥ እኔ አርጅቻአለሁ፤ የሚስቴም ዘመንዋ አልፏል፡፡›› መልአኩም እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ ይህንም እነግርህና አበሥርህ ዘንድ ወደ አንተ ተልኬአለሁ፡፡ አሁንም በጊዜው የሚሆነውንና የሚፈጸመውን ነገሬን አላመንኽኝምና ይህ እስኪሆን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ፤ መናገርም ይሳንሃል፡፡›› (ሉቃ.፩፥፲፫-፳)
ከዚህም በኋላ ሚስቱ ኤልሣቤጥ ፀነሰች፤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ፀንሳ እናቱ ኤልሣቤጥን ለመጠየቅ በሄደችበት ወቅት በማሕፀኗ ውስጥ ሳለ ሕፃኑ ለእግዚአብሔር ልጅ ሰገደ፡፡ (ሉቃ.፩፥፴፱-፵፩)
ኤልሣቤጥ የመውለጃዋ ጊዜ በደረሰ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች፡፡ መውለዷን የሰሙ ዘመዶቿና ጎረቤቶቿም ደስ ተሰኙ፤ ልጁንም ስምንት ቀን በሞላው ጊዜ ሊገረዙት መጡ፤ ስሙንም በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ሊሰይሙት ወደዱ፤ ነገር ግን እናቱ ዮሐንስ ተብሎ መጠራት እንዳለበት ተናገረች፡፡ ሆኖም ግን ከዘመዶቿ መካከል ስሙ ዮሐንስ የሚባል ባለመኖሩ አባቱ እንዲወስን ካህኑ ዘካርያስን በጠየቁት ጊዜ መናገር የተሣነው ዲዳ ነበርና ብራና ለምኖ ስሙ ዮሐንስ ይባል ብሎ ሲጽፍ ሁሉም ተደነቁ፤ በዚያን ጊዜም የዘካርያስ አንደበት ተፈታ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነ፡፡
ካህኑ ዘካርያስም መንፈስ ቅዱስ በመላበት ጊዜ እንዲህ ብሎ ትንቢት መናገር ጀመረ፤  ‹‹ይቅር ያለን፥ ለወገኖቹም ድኅነትን ያደረገ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ ከባርያው ከዳዊት ቤት የምንድንበትን ቀንድ አስነሣልን፤ ከጥንት ጀምሮ በነበሩ በቅዱሳን በነቢያት አፍ እንደ ተናገረ፡፡ ከጠላቶቻችን እጅ፥ ከሚጠሉንም ሁሉ እጅ ያድነን ዘንድ፤ ቸርነቱን  ከአባቶቻችን ጋር ያደርግ ዘንድ፤ ቅዱስ ኪዳኑንም ያስብ ዘንድ፤ ለአባታችን ለአብርሃም የማለውን መሐላ ያስብ ዘንድ፤ ከጠላቶቻችን እጅ ያድነን ዘንድ ያለ ፍርሃት፥ በቅድስናና በጽድቅ በፊቱ በዘመናችን ሁሉ እንድናመልከው ይሰጠን ዘንድ፤ አንተም ሕፃን፥ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፡፡ መንገዱንም ትጠርግ ዘንድ በፊቱ ትሄዳለህና፡፡ ኃጢአታቸው ይሰረይላቸው ዘንድ መድኃኒታቸውን እንዲያውቁ ለአሕዛብ ትሰጣቸው ዘንድ፤ ከአርያም በጎበኘን በአምላካችን በይቅርታውና በቸርነቱ፤ በጨለማና በሞት ጥላ ለነበሩት ብርሃኑን ያሳያቸው ዘንድ፥ እግሮቻቸውንም ወደ ሰላም ጎዳና ያቀና ዘንድ ወጣ፡፡›› ሉቃ.፩፥፷፰-፸፱
የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ አማላጅነት እና ተራዳኢነት አይለየን፤ ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን!
4.5K views11:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ