Get Mystery Box with random crypto!

ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)

የቴሌግራም ቻናል አርማ mahibere_kidusan — ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)
የቴሌግራም ቻናል አርማ mahibere_kidusan — ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)
የሰርጥ አድራሻ: @mahibere_kidusan
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.91K
የሰርጥ መግለጫ

The channel of mahibere kidusan

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-05-20 17:39:21
በማኅበረ ቅዱሳን የመዝሙር እና ኪነ ጥበባት አገልግሎት ማስተባበሪያ በኩል የተዘጋጀው የዝክረ ቅዱስ ያሬድ ዐውደ ርእይ ለምእመናን ክፍት ሆኖ በመጎብኘት ላይ ይገኛል።

ዐውደ ርእዩ እስከ ግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ሲሆን ምእመናን በቀሪዎቹ ዕለታት በማኅበሩ ሕንጻ 3ኛ ወለል ላይ በመገኘት መጎብኘት እንደሚችሉ ጥሪ ቀርቧል።
2.8K views14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 17:39:20
"እኔ የሃይማኖት መምህር ነኝ፤ በተከሰስኩበት ወንጀል አልተሳተፍኩም"

መምህር ኃ/ማርያም ዘውዱ ከ4 ጠበቆቻቸው ጋር የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ ይግባኝ ወንጀል ችሎት ዛሬ ረፋድ ቀረቡ።

ግንቦት 4/2015 ዓ᎐ም ባሕር ዳር ከተማ ተይዘው ወደ አዲስ አበባ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ የመጡት መምህር ኃ/ማርያም ግንቦት 7 በነበረ ችሎት ፖሊስ በጠየቀው መሠረት ፍርድ ቤቱ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ መፍቀዱ ይታወሳል።

ሆኖም ትናንት ግንቦት 10/2015 ዓ᎐ም በጠየቁት ይግባኝ መሠረት ዛሬ ግንቦት 11/2015 ዓ᎐ም ረፋድ 4 ሰዓት ላይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ ይግባኝ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል።

በችሎቱ 4 ጠበቆች የቆሙላቸው ሲሆን ክሱ "በማኅበራዊ ሚዲያ ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር ሕገ መንግስቱንና ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ᎐᎐᎐" የሚል ነው። ለዚህም ማስረጃ ለማምጣት የሚያስፈልገው አትሞ ማምጣት ብቻ ነው። ይህንን ለማድረግ 14 ቀናት መቀጠሩ አግባብ አይደለም።" በሚል ክርክራቸውን አቅርበዋል።

መምህር ኃ/ማርያም ዘውዱ በበኩላቸው" እኔ የሃይማኖት መምህር ነኝ፤በተከሰስኩበት ወንጀል አልተሳተፍኩም፤ በአሁኑ ሰዓት ወሎ ዩኑቨርስቲ በሰጠኝ እድል በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ 2ኛ ድግሪ ተማሪ ነኝ።እዚህ በመሆኔ ፈተና እና መሰል ጉዳዮች እያለፉኝ ነው፤ይህም 1 ተጨማሪ ዓመት የሚያስደግመኝ በመሆኑና ብፈለግም የታወቀ አድራሻ ያለኝ በመሆኑ የዋስትና መብት ይሰጠኝ።" ሲሉ ሃሳባቸውን ገልጸዋል።

ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ከሰማ በኋላ ለሰኞ ግንቦት 14/2015 ዓ᎐ም 3 ሰዓት የፖሊስ ምርመራ መዝገብ ለማየት እና በዛው ቀን 5 ሰዓት ከሁለቱ ወገን በቀረበው መከራከሪያ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ሰጥቷል።
3.7K views14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 21:54:16
827 views18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 23:50:27 ቤተ ሰብ

ሰው በምድራዊ ሕይወቱ ከመብል፣ ከመጠጥ፣ ከአልባሳት እንዲሁም ከመጠለያ በተጨማሪ እጅጉን ከሚያስፈጉት ነገሮች መካከል ቤተ ሰብ ነው፡፡ አብዛኛዎቻችን ስለ ቃሉም ይሁን ስለ ትርጉሙ በቂ ግንዛቤ ላይኖረን ይችላል፡፡ ምክንያቱም በብዛት ቃሉን የምንሰማውም ሆነ የምንረዳበት መንገድ ከሕፃንነታችን ጀምሮ ወላጆቻችን ወይም ታላላቅ ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን አለበለዚያም ዘመድ ዘመዶቻችን በሚነግሩን ነው፡፡ በዚያም ቤተ ሰብ አባትንና እናትን መሠረት ያደረገ እንዲሁም በወንድ እና በሴት ልጆቻቸው እና በዘመዶቻቸው የተመሠረተ ግንኙነት እንደሆነ እናምናለን፡፡ ወላጆቻቸውንና ታላላቆቻችንን በማክበር እንዲሁም በመታዘዝ ተቻችለን በመተሳሰብ የምንኖረውም ቤተ ሰባዊ ኑሮ ግን ትርጉሙም ይሁን ዓላማው ከዚያ ያለፈ ነው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ቤተ ሰብ ማለት ከዚያ የበለጠ ትርጉም እንዳለው ታስተምረናለች፡፡

በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ቤተ ሰብ አምላካችን እግዚአብሔር በአንድ ልጁ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፍቅር የመሠረተው እንደሆነ እንረዳለን፡፡ በፍቅር ላይ የተመሠረተ ማንኛውም ግንኙነት ቤተ ሰባዊ ነው፡፡ “ሁለት ወይም ሦስት በስሜ ብትሰበሰቡ እኔ በዚያ በመካከላችሁ እኖራለሁ” እንዳለው ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ሰብ የሚመሠረተው ፈጣሪያችን በቸርነቱ በሰጠን በፍቅረ እግዚአብሔር ላይ የተመሠረት ትስስር ስንኖር ነው፡፡ (ማቴ.፲፰፥፳)

በቅዱሳት መጽሐፍት ላይ እንደተለጸው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ሰቦች ተብለው የሚጠሩ ፻፳ ቤተ ሰቦች አሉ፡፡ እነርሱም ፲፪ ቅዱሳን ሐዋርያት፣ ፸፪ አርድእት እና ፴፮ ቅዱሳት አንስት ናቸው፡፡

በእግዚአብሔር የተመረጡት እነዚህ ቅዱሳን በሕይወት ሥጋ የኖሩት በፍቅር ተሳስረው ነበርና ለተልእኮ በሄዱበት ከተማ ሁሉ ሁለትም ይሁን ሦስት ሆነው በተገኙበት ቦታ አምላክ አብሯቸው ስለነበር በፍቅር እንደኖሩና በሰጣቸውም ጸጋና ሥልጣን ጠላታቸውን ድል እንደነሡ ገድላቸው ምስክር ነው፡፡ ስለ ክርስቶስ ፍቅርም መከራና ሥቃይ ተቀብሎው ለፍቅር በመሞት ወደ ፈጣሪያቸው ተጉዘዋል፡፡
 
እኛም የሐዲስ ኪዳን ሰዎች ከክርስቶስ ቤተ ሰብ መከካል እንቆጠር ዘንድ ፍቅረ እግዚአብሔርና ፍቅረ ቢጽ (የባልንጀራ ፍቅር) ሊኖረን እንደሚገባ ከቅዱሳኑ ታሪክ እንመለከታለን፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፡፡ ለአምላካችንና ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በሚኖረን ፍቅር የተነሣ መከራ መስቀሉን ተቀብለን፣ ጠላታችን ድል ነሥተንና መንግሥተ ሰማያትን ወርሰን በፈጣሪያችን ቤት በአንድነት ልንኖር የተገባን ነን፡፡    
 
አምላካችን እግዚአብሔር የመንግሥቱ ወራሽ ያድርገን!
4.5K views20:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 23:50:27 ቤተ ክርስቲያን ጥንተ ሥርዓቷን አስጠብቃ ዘመኑን የዋጀ መዋቅራዊ አደረጃጀት፣ ብቃት ያለው አስተዳደር እና ሐዋርያዊ አገልግሎቷን የምትመራበት መሪ ዕቅድ ትግበራ እውን እንዲሆን በተደጋገሚ ስንጠይቅ ይሁንታ ባገኘ ጊዜም በዝግጅቱ በመሳተፍ በርካታ ዓመታትን በተስፋ አሳልፈናል:: በያዝነው ዓመትም በቅዱስ ሲኖዶስ ይሁንታ በተሰጠው ዘላቂ መፍትሔ ቋሚ ኮሜቴ ውስጥ በመሳተፍ የሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት ቅድመ ምልመላ መሥፈርት፣ የሀገረ ስብከት አደራጃጀት እና ምደባን አስመልክቶ አስፈላጊና ጠቃሚ የጥናት ሰነዶች እንዲዘጋጅ ተራድተናል። በዚህም ተገቢ ሰነድ ተዘጋጅቶ ቀርቧል።

የሁሉም የሆነችው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተለይ በዚህ አስጨናቂ ወቅት አባቶች የልጆችን ድምፅ በመስማት፣ እርስ በእርስ በመደማመጥና በመናበብ፣ አቃፊ በመሆን፣ በጥበብ መጓዝ ያስፈልጋል ብለን የምናምን ሲሆን እኔ ብቻ አውቅልሀለሁ ብሎ የልጆችን ቀና የአስተዳደር ለውጥ ሐሳብ መግፋትና ከተሳትፎ ማግለል ከባድ ዋጋ እንደሚያስከፍል መረዳትም ያስፈልጋል ብለን እናምናለን:: ቤተ ክርስቲያን በሁሉ ልብ ውስጥ ያለች ናት። በመሆኑም የጥቂት ጳጳሳት ብቻ ሳትሆን የካህናት፣ የምእመናን እና የሰንበት ትምህርት ቤት ድርሻ ተሰናስሎ የሚገለጥባት መንፈሳዊ ተቋም ናት::

በሕገ ቤተ ክርስቲያን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አንድነትና አስተዳደር ለማጠናከር በወጣው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ደንብ (ቃለ ዓዋዲ) መሠረት የቤተ ክርስቲያኗ አስተዳደር መመራት ያለበት ከጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ድረስ ከካህናት፣ ከምእመናን እና ከሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በተውጣጡ መዋቅሮች ነው፡፡ በዚህም አግባብ ይህን ታሳቢ ያደረገ አሳታፊ አሠራርን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን እንገለጻለን።

ሀገራዊ ሰላም ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ቤተ ክርስቲያን የሚኖራት ሱታፌ በትክክል ሊሠራበት ይገባል። ከዚህ በፊት እንደሚደረገው ወሳኝ አስተዋጽኦ ማድረግ በማያስችል ሁኔታ ከአንድ አካል ብቻ ኮሚቴ አቋቁሞ ለዜና ግብአት ከመሆን ባለፈ እውነተኛ ተሳትፎ እንዲኖረን አግባብነት ያላቸውን ሊቃውንት፣ ምሁራን፣ ሰንበት ትምህርት ቤቶች እና ማኅበራትን በማሳተፍ ወደ ሥራ እንዲገባ እንጠይቃለን፡፡

– በቅዱስ ሲኖዶስ ይሁንታ በተሰጠው ዘላቂ መፍትሔ ጠቋሚ ኮሜቴ የሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት ቅድመ ምልመላ መሥፈርትን፣ የሀገረ ስብከት አደራጃጀትን እና ምደባን አስመልክቶ ካህናት፤ ምእመናን እና ሰንበት ትምህርት ቤቶች የተሳተፉበት ጠቃሚ ሰነድ ተዘጋጅቶ ለቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቧል። ይሁንና ለምልዐተ ጉባኤው ገንቢ ግብዓት እንዳይሆን አለመቅረቡ የቀደመ ለውጥ ጠል በሽታ ማሳያ ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ዘመኑን ያልዋጀና የሰነበተ ደዌ በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ቆርጦ እንዲጥል እና የተዘጋጀው ጥናት እና አቅጣጫ ጠቋሚ የመፍትሔ ሐሳብ በመሆኑ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቀኖና፣ ክብር እና አንድነት ቅድሚያ በመስጠት እንዲጠቀምበት፣ ግልፅና መርኀን የተከተለ የምልመላ፣ የምርጫ እና የምደባ ሥርዓት ለመከተል የሚያስችለው የጥናት ሰነድ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አርፎበት ተግባራዊ እንዲሆን በልጅነት መንፈስ እንጠይቃለን።

*በተደራቢነት የተያዙ አኅጉረ ስብከቶች እና በቁጥራቸው ብዙ የሆኑ አድባራትና ገዳማት ያሉባቸው አኅጉረ ስብከቶችን ተገቢ እና ውጤታማ አገልግሎት መስጠት በሚያስችል መልኩ ተጨማሪ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት በቀረበው መሥፈርት መሠረት በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እና ሕግ መሠረት እንዲከናወን እናሳስባለን፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ በውጪያዊ እና በውስጣዊ ግፊት፣ ከሲሞናዊነት እኩይ ተግባር፣ ለውጥ ጠልና ጎታች በሆኑ አመለካከቶች እንዳይያዝ በመጠንቀቅ ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅ መንፈሳዊ ግዴታውን እንዲወጣ እንጠይቃለን። እንዲሁም ጥር ፲፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም. በግልጽ ደብዳቤ ለቅዱስ ሲኖዶስ ያቀረብነውን የመፍትሔ ሐሳብ በአግባቡ በመመልከት በግብዓትነት እንድትጠቀሙበት በፍጹም ትሕትና እና በልጅነት መንፈስ እንጠይቃለን።

የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
3.9K views20:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 23:50:27
ቤተ ክርስቲያን የአንድ አካል ብቻ አይደለችም፤ የካህናት፣ የምእመናን እና የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ጭምር እንጂ!

ከሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የተላለፈ ወቅታዊ መልእክት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ዋና ተግባሩ የሆነውን ሐዋርያዊ ተልእኮ በትጋት እና በስፋት ከማስፈጸም ይልቅ በሥጋ ሐሳብ ተቀፍድዶ ጥንታዊቷን እና አማናዊቷን ቤተ ክርስቲያን በማይመጥን ደረጃ ላይ መገኘቱን የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ተገንዝቧል። በተለይ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን፣ አደረጃጀቱን ለማዘመን እና የሥራ አፈጻጸም ስልትን ከዘመኑ ጋር ለማጣጣም እንዲያስችል በተለየዩ ጊዜያት በባለሙያዎች ተጠንተው የተዘጋጁ መፍትሔ አመላካች ሰነዶች ልዩ ልዩ ምክንያት እየተለጠፈባቸው ተገፍተው መወገዳቸውን ታዝበናል። ስለሆነም አስተዳደራዊ ክፍተቱ በከፍተኛ ደረጃ የወለደው ችግር የአደባባይ ምሥጢር ሆኖ ተገልጧል::

ከቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ድክመት ጋር ተያይዞ እየተስተዋሉ ያሉ ዘርፈ ብዙ የውስጥ ችግሮች እና የሥነ ምግባር ጥሰቶች መንፈሳዊ አገልግሎቱን ያቀጨጩ፣ በመንፈሳዊነት ዐውድ አንገታችን ያስደፉ፣ በሌሎች ዘንድ ለስላቅ መንገድ የከፈቱ፣ ለትችት የዳረጉን የትውልዱ ስብራቶች እንደ ሆኑ ተገንዝበናል።
3.9K views20:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 23:35:35  
ከ፳፻፲፩ ዓ.ም ባሉት ዓመታት የምረቃ መጽሔትን ከወረቀት ኀትመት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ወደሚታገዝ (Digital) አሠራር እንዲቀየር ስምምነት መደረሱን እና ከ፳፻፲፪ ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ወደሚታገዝ (Digital) አሠራር ተቀየረ፡፡
 
ማኅበሩ በ፲፱፻፺፩ ዓ.ም በክረምቱ ወራት ለተተኪ መምህራን በአማርኛ ሥልጠና መስጠት ሲጀምር፣ ከ፲፱፻፺፯ ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በአፋን ኦሮሞ መስጠት ቀጠለ፡፡ በአሁኑ ወቅት በአፋን ኦሮሞ ማስተማር የሚችሉ መምህራንን ማፍራት ችሏል፡፡
 
ማኅበረ ቅዱሳን ከየካቲት ፳፻ ዓ.ም ጀምሮ በተለይ ለግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች “ጉባኤ ቃና” የተሰኘ መጽሔት በየ፫ ወሩ በአማርኛ እንዲሁም በአማርኛ የተዘጋጀው መጽሔት ወደ አፋን ኦሮሞ በመተርጎም አዘጋጅቶ ማሠራጨት ጀመረ፡፡
 
ማኅበሩ ምንም እንኳን የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተምሮ በአባቶች ቡራኬ የሚያስመርቃቸው ኦርቶዶክሳውያን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ፣ ከ፹ በላይ የሚሆኑ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ቢሆኑም ከኦሮምያ ክልል የሚመጡት በሃይማኖታቸው እንዲጸኑና ከተለያዩ አካላት የሚደረግባቸውን ጫና መቋቋም እንዲችሉ በማሰብ ለሁሉም የሚታተመው የምረቃ መጽሔት በልዩ ሁኔታ በአፋን ኦሮሞ ጭምር ተተርጉሞ እንዲታተም እየተደረገ መሆኑን ያውቃሉ?
82 views20:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 23:35:35
ይህን ያውቁ ኖሯል?

የመጀመሪያው የግቢ ጉባኤያት ተወካዮች ሀገር አቀፍ ሴሚናር ከየካቲት ፲፫-፲፬ ቀን በ፲፱፺፩ ዓ.ም ተከናወነ፡፡
    
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት  ቤት ሲማሩ የቆዩ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመጀመሪዋ  የደረቅ ቅጅ /Hard copy/ የምረቃ መጽሔት በ፲፱፻፹፮  ዓ.ም ተዘጋጀ፡፡
 
የመጀመሪያዋ ጉባኤ ቃና ጋዜጣ ቁጥር ፩ የካቲት ፳፻ ዓ.ም መታተሟና  ዋጋዋም  ፩ ብር ከ፳፭ ሣንቲም የነበረ ሲሆን የገጽ ብዛቱም ፰  ነበር፡፡
  
በሀገር ወስጥ ፪፻፹፮፣ በውጭ ሀገራት ፲፯ የጸደቁ ግቢ ጉባኤያት እና  በሀገር ውስጥ ፻፵፭ በክትትል ላይ  ያሉ፣  በውጭ  ሀገራት ደግሞ ፮ ግቢ ጉባኤያት ይገኛሉ፡፡
  
ማኀበረ ቅዱሳን በአጠቃላይ ፬፻፶፬ (፬፻፴፩ በሀገር ውስጥ እና ፳፫ በውጭ ሀገራት) ግቢ ጉባኤያትን  እያስተማረ መሆኑን ያውቃሉ?
 
የመጀመሪያው የግቢ ጉባኤያት የተከታታይ ትምህርት /course/ ማስተማሪያ መጻሕፍት ዝግጀት የተጀመረው በ፲፱፻፺፮ ዓ.ም ነበር፡፡ በተቀረጸው ሥርዓተ ትምህርት /carricullum/ ውስጥ ፳፪ የተከታታይ ትምህርት መጻሕፍትን በማዘጋጀት የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ነገረ ሃይማኖት ማስተማሩን ቀጠለ፡፡
    
በ፳፻፭ ዓ.ም የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ በማድረግ የትምህርት ዓይነቶቹን ወደ ፲፩ ዝቅ በማድረግ  እስከ አሁን  በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለሚማሩ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች  በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡
70 views20:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 23:35:35 2ኛ. ቤተ ክርስቲያናችን በ2009 ዓ.ም  ኤጲስ ቆጶሳትን ከሾመች በኋላ በልዩ ልዩ ምክንያቶች በተፈጠሩ ክፍተቶች የተነሣ በብፁዓን አባቶች ተደርበው የተያዙ ሀገረ ስብከቶች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ለዚህም ባደረጋችሁት ውይይትና ሰምምነት አንቀጽ 4 ላይ #… በቀጣይ የግንቦት ርክበ ካህናት ተወስኖ እንዲሾም በማለት መስማማታችሁ ይታዋሳል፡፡ በዚሁ መሠረት ተደርበው ለተያዙ ሀገረ ስብከቶች የኤጲስ ቆጶሳትን መሾም አስፈላጊነትን በመወሰን አፈጻጸሙ በቤተ ክርሰቲያን ቀኖና መሠረት በጥንቃቄ ለማከናወን በዐቢይ ኮሚቴው ተጠንቶ የቀረበውን  ወቅቱ የሚጠይቀውን የእጩ ኤጲስ ቆጶሳት የምርጫና የመመዘኛ ሥርዓት ላይ ተወያይቶ በማጽደቅ እና ሁሉን አካታች የሆነ ግልጽና ተጠያቂነት ባለው አሠራር የሚመራ አስመራጭ ኮሚቴ በመሰየም፣ የሢመቱ ሂደትም ግልጽ፣ ምእመናንና ካህናት በንቃት ተሳታፊ የሚሆኑበት ለማድረግ በጥንቃቄ እንዲታይና በሚጸድቀው መሥፈርትና ስምምነት መሠረት ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን በአባትነት በሙሉ ልባቸው የሚቀበሏቸው ኤጲስ ቆጶሳት ለመሾም የምርጫ ሂደቱ ቢጀምር፡፡

3ኛ. ባለፉት ሁለት ዓመታት በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በትግራይ ክልል የሚገኙ ሀገረ ስብከቶች ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጋር ያላቸው አስተዳደራዊ ግንኙነት ተቋርጦ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ በዚህ ሁኔታ የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ቢከናወን በቀጣይ የቤተ ክርስቲያን ጎዞ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል፡፡ በመሆኑም ይህ ችግር ተወግዶ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ አንድነት እንዲጠናከር ቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳዩን በትኩረት ተመልክቶ አስፈላጊውን ውሳኔና አቅጣጫ ቢሰጥ፡፡

4ኛ. ቤተ ክርሰቲያን ያጋጠማትን ወቅታዊ ችግር ምክንያት በማድረግና እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም አብያተ ክርሰቲያናትን በኃይል ሰብሮ በመግባት፣ ታሪካዊ ቅርሶችን በመዝረፍና በማውደም፣ ምእመናን ላይ የአካልና የሕይወት ጉዳት በማድረስ ላይ የሚገኙ ሕገወጥ አካላትን መንግሥት ሕግ የማስከበር ኃላፊነቱን እንዲወጣ ቅዱስ ሲኖዶስ ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገርና በመመካከር የቤተ ክርስቲያን መብትና ሕልውና እንደያስከብር ቢያደርግ፡፡

በመጨረሻም ወደ ፊት ቤተ ክርስቲያን ፈተና እንዳይገጥማት ማድረግ ባትችልም እንኳ ለትውልድ መሻገር የምትችለው የውስጥ አስተዳደራዊ አቅሟን ማሳደግ ስትችል ነው፡፡ ይህንን አስተዳደራዊ ጥንካሬ እና ተቋማዊ ልዕልና መፍጠር የሚቻለው ደግሞ በቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትና በየዘርፉ ባሉ ባለሙያዎች የሚቀርቡ ጥናቶችንና ምክረ ሐሳቦችን በበጎ ሕሊናና በሠለጠነ አስተሳሰብ በመቀበል ጥናቶቹ በውይይት እንዲበለጽጉ አድርጎ ለታለመው ዓላማ መጠቀም ሲቻል ነው፡፡

በመሆኑም ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያንን ሊቃውንትና የየዘርፉ ባለሙያዎች የሆኑ የቤተ  ክርስቲያንን ልጆች በተናጠልና በጋራ በበጎ ፈቃድ የሚያቀርቡትን አስተዳደራዊ ማሻሻያዎች ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮ መሳካትና ተቋማዊ ልዕልና ጥቅም ላይ የሚውሉበትን መንገድ አቅጣጫ እንዲሰጥበት እየጠየቅን ማኅበረ ቅዱሳንም ቅዱስ ሲኖዶስ በሚወስነው ውሳኔ መሠረት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ለመወጣትና በልጅነት ለመታዘዝ ዝግጁ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
61 views20:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 23:35:35
ማኅበረ ቅዱሳን ለቅዱስ ፓትርያርኩና ለብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ደብዳቤ አስገባ።

በጻፈው ደብዳቤም ቤተ ክርስቲያን አስቀድማ የጀመረችውን ስልታዊ እቅድ፣ የመዋቅር እና የአስተዳደራዊ ማሻሻያ ሰነዶችን ተመልክቶ ውሳኔ እንዲሰጥ ጠይቋል።

ከማንኛውም ሹመት በፊት የእጩ ኤጲስ ቆጶሳት የምርጫና የመመዘኛ ሥርዓት ሁሉን በአሳተፈ መንገድ ለውይይት ቀርቦ እንዲጸድቅም ሃሳብ ሰጥቷል ።

ቅዱስ ሲኖዶስ ጊዜ የማይሠጡ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች በጥልቀት ተመልክቶ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች እንደሚሰጥ ተስፋ አለን ያለው ማኅበሩ በ4 ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንዲወያይ እንደልጅነታችን እንጠይቃለን ብሏል።

1ኛ. ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ቤተ ክርስቲያን የሚያጋጥሟት ፈተናዎች ዋነኛ ምክንያት የቤተ ክህነት አስተዳደር ዘመኑን የዋጀ አለመሆን ነው፡፡ ይህንንም ብፁዓን አባቶቻችን ከፍተኛ የመንግሥት ባላሥልጣናት እና የሚመለከታቸው አካላት ባሉበት ባደረጋችሁት ስምምነት አንቀጽ 8 እና 9 ላይ በግልጽ የተቀመጠ ሲሆን “ለትውልድ አርአያ የሚሆን ቤተ ክህነት እንዲኖር ለማድረግ አሠራራችንን በጥናት አሻሽለን ቤተ ክርስቲያንን ለትውልድ እናሻግራለን፡፡” በማለት ስምምነት ላይ መድረሱ ይታወሳል፡፡ በዚሁ መሠረት ቤተ ክርስቲያን አስቀድማ የጀመረችውን የመሪ እቅድ እና የዘላቂ አስተዳደራዊ መፍትሔ ጥናቶች ውጤት መሠረት የተዘጋጁትን ስልታዊ እቅድ፣ የመዋቅር እና የአስተዳደራዊ ማሻሻያ ሰነዶችን ተመልክቶ ውሳኔ ቢሰጥ፡፡
63 views20:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ