Get Mystery Box with random crypto!

በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ የልዑካን ቡድን ሐምሌ ፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም ወደትግራይ ርዕ | ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)

በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ የልዑካን ቡድን ሐምሌ ፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም ወደትግራይ ርዕሰ ከተማ መቐለ ይጓዛል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ባስ ተላለፈው ውሳኔ መሰረት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሚመራ የልዑካን ቡድን ሐምሌ ፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ .ም ወደ ክልል ትግራይ ርዕሰ ከተማ መቐለ ይጓዛል።

ልዑካን ቡድኑ ወደ መቐለ የሚጓዘው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ መሰረት ለትግራይ ክልል እንዲሰጥ የተወሰነውን ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስና በትግራይ ከሚገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በሰላም ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር መሆኑ ታውቋል።ይህንን በተመለከተም ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት የተላከው ደብዳቤ ለፕሬዝዳንቱ ጽሕፈት ቤት ዛሬ ማለዳ እንዲደርስ ተደርጓል።

ምንጭ: EOTC Public relations