Get Mystery Box with random crypto!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን  ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስ | ማኅበረ ቅዱሳን ( Mahibere Kidusan)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን በክርስቶስ ደም ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ  ከቅዱሳን ሐዋርያት የወረሰችውን ምዕመናንን የመጠበቅና ወንጌለ መንግሥቱን ለዓለም የማዳረስ እንዲሁም ዶግማዋ እና ቀኖናዋ ሳይፋለስ ጠብቃ በማስጠበቅ የተቀደሰውን ሥርዓተ አምልኮ ከትውልድ ወደ ትውልድ በማሻገር የማይተካ ሚና በመጫወት እስካሁን የደረሰች በቀጣይም ይህንን ሐዋርያዊ ተልዕኮዋንና የክህነት አገልግሎትዋን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ እንዲቻል ከሐዋርያት ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ኤጲስ ቆጶሳትን እየሾመች መንፈሳዊ አገልግሎቷን ስታከናውን ኖራለች፤ ወደፊትም ትኖራለች፡፡ ይህም በመሆኑ ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም. በኦሮምያ ክልል በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጭ በተፈጸመው ሢመት በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የደረሰውን መከራና ፈተና ለማሳለፍ ሲባል ዶግማዋን፣ ቀኖናዋንና ትውፊቷን ባስጠበቀ ሁኔታ ችግሩ በውይይት እንዲፈታ ባደረገችው ያላሰለሰ የሰላም ጥሪ መነሻነት የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም. ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በተደረሰው ስምምነት መሠረት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ቀኖናዋን ከስምምነቱ፣ ስምምነቱን ከቀኖናዋ ጋር በማዛመድ በኦሮምያና በደቡብ ክልል ባሉ ክፍት አህጉረ ስብከት ተመድበው የሚያገለግሉ 9ኝ ኤጲስ ቆጶሳት በቀኖና ቤተ ክርስቲያን እንዲሾሙ በወሰነው መሠረት ተሿሚ እጩ ኤጲስ ቆጶሳትን መልምለው የሚያቀርቡ ሰባት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን መሰየሙ ይታወሳል፡፡