Get Mystery Box with random crypto!

Inspire Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia — Inspire Ethiopia I
የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia — Inspire Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @inspire_ethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 162.68K
የሰርጥ መግለጫ

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 61

2022-07-07 07:34:44 ፈጣሪ መቼም አይተወንም!


ብዙ ሰዎች ቃል ሊገቡልን ይችላሉ ! አንተ ብቻ ተመረቅ እንጂ በበነጋታው ነው ስራ የማስገባህ ከሚለው አንስቶ እስከ ትልልቅ ነገሮች እኔ አደርግልሀለው፣ አሳካልሀለው፣ አስተካክልካለው እያሉ ብዙ ተስፋ ይሰጡሀል ከዚያ ግን በጣም በፈለግካቸውና ቃል የገቡልህ ሰዐት በደረሰ ግዜ ከጎንህ የሉም ያኔ ምን ይሰማሀል? አምነትህን ሙሉ ለሙሉ የጣልክባቸውን ሰዎች ምንም ሊያረጉልህ እንደማይችሉ ስታውቅ ተስፋ ትቆርጣለህ? ሁሉን ነገር ታቆማለህ? በፍፁም እንዳታደርገው ! የሰው ልጅ ትልቁ ተስፋ ፈጣሪው ብቻ ነው ስለዚህ ቃል የገቡልህ ያመንካቸው እነሱን ተንተርሰህ መንገድ የጀመርክባቸው ድንገት ቢሸሹህ የሚያስጨርስህ እና የሚያሳካልህ የሚያግዝህ ፈጣሪ እንዳለህ አስታውስ !


የተባረከ ሀሙስ ተመኘን
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
53.5K viewsDaniel W., 04:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 20:40:09 በፍቅር ማሸነፍ!

ሰዎችን ሁሉ አሳምናለው ካልክ ከድካም ውጪ ምንም አታተርፍም፤ ዝቅ ማለት ካለብህ ዝቅ ትላለህ፣ ያንን ጊዜ አጎንብሰህ ማለፍ ካለብህ አጎንብሰህ ታልፋለህ።

አንዳንዴ ታሪክ የምትሰራው በማሸነፍ ብቻ አይደለም፤ ለፍቅር ስትል ዋጋ በመክፈልና በመሸነፍም ነው። ይሄን የምታደርገው ለጊዜው ተሸንፈህ ለዘላለም ለማሸነፍ ነው!

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
53.6K viewsSinework Taye, 17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 07:05:59 ሁሌም በመልካም መልስ!

አሸናፊ ሰው የሰዎችን ከባድ ስሜት መቆጣጠር የሚችል ነው ! ሰዎች በህይወት አጋጣሚ ብዙ ነገሮችን ሊያሳልፋ ይችላሉ ይከፋሉ፣ ይናደዳሉ፣ ይጨነቃሉ ከዛም በምንሰራበት ቦታ ወይ ደግሞ ያለንበት አካባቢ በዚያ ስሜት ውስጥ ሆነው ይገኙ እና የሚያስቀይም ንግግርን ሊናገሩን ይችላሉ ያኔ ታድያ እኛም ከእነርሱ በላይ የሚያስቀይም ንግግርን ከአንደበታችን ካወጣን ሊፈጠር የሚችለውን የማያልቅ ጭቅጭቅ እና አለመግባባት በዛ ላይ እርስ በራስ ከሚፈጠርብን ጥላቻ ባለፈ የዛን የተረበሸ ሰው ስሜት የባሰ መጉዳት ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍልስ እናስበዋለን? ሁሌም ባለን እና በተቻለን አቅም ሁሉ ለሰዎች መልካም እንሁን ከልባችን እናግዛቸው ምንም አይነት ምላሽ ይስጡን ጥሩነታችንን እናጋራቸው ያኔ እነርሱ በነበራቸው መጥፎ ስሜት ያፍሩበታል መልካምነታችን ይጋባባቸዋል አሸነፍን ማለት ይሄ አይደለ!

ደስ የሚል ረቡዕ ተመኘን
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
55.5K viewsDaniel W., 04:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 20:44:57 ደስተኛ መሆን አለብህ!

አንዳንዴ በጣም ከባድ ችግር የመሰለህ ነገር አስቂኝ ሆኖ ቁጭ ይላል፤ በዚህ ምድር ለመኖር የቀረህ 1 ሳምንት ብቻ ነው ቢባል የትኛው ሰው ነው የኑሮ ውድነት የሚያሳስበው? የትኛው ሰው ነው የፍቅረኛው ስልክ አለማንሳት የሚያበሳጨው? ያለህን አጭር ጊዜ እንዴት አጣጥመህ እንደምታልፈው ታስባለህ እንጂ በፍፁም አተክዝም።

አየህ ወዳጄ አሁንም የቀረህ እድሜ ስንት እንደሆነ አታውቀውም፤ ተኝተህ ማደርህን እንኳን እርግጠኛ አይደለህም! ስለዚህ ለማን ብለህ ነው የምታዝነው? በፈጣሪህ እመን ከዛ የምትችለውን ሞክር የቀረውን ለነገ ተወው!

ገራሚ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
55.0K viewsSinework Taye, 17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 07:43:45 ብቻህን ተደብቀህ አትታገል !

ምንም አይነት ስሜት ለይ ብትሆን ቢከፋህ ቢደብርህ ያለመቻል የመሸነፍ ስሜት ቢሰማህ በርህን ዘግተህ አትተኛ ፣ አትደበቅ ፣ ብቻህን ቁጭ ብለህ አትከፋ! ተነሳ ፣ ተታጠብ ፣ ልብስህን ቀይር ራስህን አስተካክል ከዛም ውጣ አካባቢህን በዙሪያህ ያሉትን ሁሉ ተመልከት እንቅስቃሴ አድርግ ሮጥ ሮጥ በል ከሠዎች ጋር ተወያይ ከዚያ ያ የነበረክ ስሜት ሁሉ ከላይህ ላይ እርግፍ ብሎ ሲለቅህ ታየዋለህ በአዲስ ሀሳብ በተሻለ ማንነት ትሞላለህ!

የተባረከ ቀን ተመኘን
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
56.1K viewsDaniel W., edited  04:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 20:29:30 የተለየ ጥረት ያስፈልግሀል!

ታሪክ መስራት ከፈለክ አብዛኛው ሰው የማያደርገውን ማድረግ አለብህ፤ ሌላው ሲተኛ አንተ ትነሳለህ፣ ሌላው ጊዜውን በከንቱ ነገር ሲያጠፋ አንተ ራስህ ላይ እና ስራህ ላይ ታጠፋለህ፣ ሌላው ገንዘብ ሲያጠፋ አንተ ታስቀምጣለህ፣ ሌላው ወደ ፈጣሪው ለመቅረብና ፀሎት ለማድረስ ጊዜ ሲያጣ አንተ ይበልጥ በመንፈሳዊነትህ ትጠነክራለህ!

ወዳጄ የተለየ ነገር ከፈለክ የተለየ ጥረት ያስፈልግሀል፤ ደስ የሚለው ምን ማድረግ እንዳለብህ አውቀህ መንገዱን ጀምረሀል፤ ማን እንደሆንክ ለራስህ ሳታሳየው ማቆም የለም!

አስደናቂ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
55.8K viewsSinework Taye, 17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ