Get Mystery Box with random crypto!

Inspire Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia — Inspire Ethiopia I
የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia — Inspire Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @inspire_ethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 162.42K
የሰርጥ መግለጫ

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 54

2022-09-23 08:19:18 በከባድ ፈተና ውስጥ ራስህን መፍጠር እንደምትችል ታውቃለህ ?

የህይወትህ አስቸጋሪ ወቅት ላይ ልትሆን ትችላለህ ምኑን ከምኑ እንደምታቻችል ፣ የትኛውን ማስቀደም እንዳለብህ ፣ የቱን መተው እንደሚጠበቅብህ መላቅጡ ጠፍቶህ ይሆናል ፤ አይዞህ ብዙ ሰው ጋር ይሄ ስሜት አለ ።

ችግሩን መካድ አይጠበቅብህም በጥበብ ማለፍ ግን ትችላለህ !

ኢንስፓየር ኢትዮጵያ ኮሮና በከፍተኛ ደረጃ በተስፋፋበት ፣ ሁሉም በሩን ዘግቶ በተቀመጠበትና ኑሮ ባሻቀበት ወቅት እንደተፈጠረስ ያውቃሉ ?

ህይወትህን ለመቀየር አንድ ውሳኔ በቂ ነው !

ባሉበት ቦታ በምቾት ተቀምጠው ራስ ላይ መስራት ተችሏል !

በዚህ ስልጠና የአመለካከት ለውጥ እንዲያመጡ ፣ የተግባር ሰው እንዲሆኑ ፣ የተሻሉ ውሳኔዎችን መወሰን እንዲችሉ ፣ ትልቅ እንዲያስቡና የይቅርታ ልብ እንዲኖርዎ እናግዞታለን ።

ስልጠናው የሚሰጠው በኦንላይን ( ZOOM App )

በሳምንት ሁለት ቀን ረቡዕ እና ቅዳሜ ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ 5 ሰዓት ራስ ላይ የሚሰራበት ሰዓት ነው !

Silver ( 3ተኛ ደረጃ )

ለስልጠናው የሚያስፈልጉትን ግብአቶች "በሶፍት ኮፒ" ወይም በስልክ ይደርሶታል !

ምንም እንኳን ስልጠናውን ተገኝቶ መካፈል ወሳኝ ቢሆንም በተለያዩ አጋጣሚዎች በስልጠናው ሰዓት ባይገኙ የድምፅ ቅጂ ይደርሶታል !

ለሰልጣኞች ብቻ የሚከፈት የቴሌግራም ግሩፕ አባል በመሆን ከተለያየ የአለም ክፍል የሚሳተፉ ሰዎች ጋር ሀሳብ መለዋወጥ ይችላሉ !

ስልጠናው ሲያልቅ ቀድመው ስልጠናውን ከጨረሱ የኢንስፓየር ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ጋር በመቀላቀል የተለያዩ ስልጠናዎችን በየሳምንቱ ያገኛሉ !

ክፍያ : - 4,999 ብር ብቻ

Gold ( 2ተኛ ደረጃ ) በብዙዎች ተመራጭ

ሁሉንም 3ተኛ ደረጃ ላይ የተጠቀሰውን ያካትታል

በተጨማሪ :

ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ያሉበት ሀገር በ"ሀርድ ኮፒ" እናደርሳለን !

ከመደበኛው ስልጠና ሰዓት ለተጨማሪ 1 ሰዓት ሁሌም የተለያዩ የግል ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ እና ተጨማሪ ስልጠናዎችን ያገኛሉ !

ከስልጠናው በኋላ ለ 1 ዓመት ያክል በወር 1 ቀን ተጨማሪ ስልጠና እና ክትትል ያገኛሉ !

ለ2ተኛ ደረጃ ተመዝጋቢዎች ብቻ የሚከፈት የቴሌግራም ግሩኘ ተሳታፊ ይሆናሉ !

ውስን ሰዎች ብቻ ነው የምንቀበለው !

ክፍያ : - 9,999 ብር ብቻ

Platinum ( 1ኛ ደረጃ )

ከላይ ያሉትን ሁሉንም ያካትታል !

በተጨማሪ :

መደበኛው ስልጠና ሲያልቅ ለእርሶና ለአሰልጣኛችን የሚመች ሰዓትና ቀን መርጠን በሳምንት 1 ቀን ለሁለት ሰዓት ያክል ለተከታታይ 6 ሳምንታት የግል ስልጠና እና ክትትል ያገኛሉ !

በአንድ ዙር ከ5 ሰው በላይ አንቀበልም !

ክፍያ : - 34,499 ብር ብቻ

ለመመዝገብና ቦታ ለማስያዝ ከታች ባለው ቁጥር በቴሌግራም ወይም በዋትስ አፕ መልዕክት ይላኩ ።

+251944314544

ማሳሰቢያ :- ከላይ ያለውን ስልክ ብቻ ይጠቀሙ

የተባረከ ቀን ተመኘን
Inspire Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
33.3K viewsDaniel W., edited  05:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 08:19:18
29.2K viewsDaniel W., 05:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 20:25:30 ሙሉ ደስታ

ለሰዎች ብለህ ማስመሰሉ እኮ ነው ደስታህን የነሳህ! "ደስታ ማለት የምታስበው ከምትናገረውና ከምታደርገው ጋር አንድ ላይ ሲዋሀዱ ነው" ይለናል ማህተመ ጋንዲ

ብቻህን ደስተኛ ካሎንክ ይመስልሀል እንጂ በሰዎች ብትከበብም ሙሉ ደስታ አይኖርህም፤ ሁልጊዜም ውስጥህ የሚነግርህን ህሊናህ የሚያዝህን አድርግ!

ጣፋጭ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
34.6K viewsSinework Taye, 17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 08:00:34 የነበረውን ይቅር በል !

ቂም መያዝ አቁም በደሉኝ ተገፍቼ ነበር ሰው ለእኔ ክፉ ነው ጥሩ የሚያስብልኝ የለም ብለህ ማሰብህን ተው ሁሉን ነገር ፈተና አታድርገው ሰው ሁሉ ሆን ብሎ አንተን ሊያጠቃህ እና ሊበድልህ የሚተጋ አይደለም ምናልባት አንዲት ሴት ባልጠበቅኸው ሁኔታ አስከፍታህ ይሆናል ያ ማለት ግን ሁሉም ሴት አንተን ሊጎዳ የተዘጋጀ ነው ማለት አይደለም ይጎዱኛል ብለህ ከቀረብህ ግን እመነኝ መጎዳትህ አይቀርም ምክንያቱም አንተ የምታየው ሁሉ መጥፎ ነገሩን ብቻ ስለሆነ ስለዚህ ይቅርታ አድርግ እናም ሁሌም አዲስ ህይወት ጀምር ሁሉም ነገር ባለበት አይቀጥልም !

ደስ የሚል ቀን ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
38.0K viewsDaniel W., 05:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 20:03:14 አሁንም ዕድል አለ!

"ሁሉም ነገር መጨረሻው ላይ ያማረ ነው፤ ካላማረ ግን ገና መጨረሻው ጋር አልደረስክም ማለት ነው" ይለናል ዕውቁ ዘፋኝ ጆን ሌነን ፍፃሜው ካላማረ ማቆም የለም! ምክንያቱም ካቆሞክ መሸነፍህን አረጋግጠሀል፤ ከቀጠልክ ግን አሁንም ዕድል አለ።

የሚያምር ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
39.3K viewsSinework Taye, 17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 08:18:01 እውነተኛውን እንጠብቅ !

በፍቅር ግንኙነት ላይ ሁሉም ነገር እንደምናስበው እና እንደሳልነው "ፐርፌክት" ይሆናል ብለን ከጠበቅን ከማንም ሰው ጋር አብረን ልንሆን አንችልም ምክንያቱም ሰዎች ነን እና የራሳችን አስተሳሰብ፣ ማንነት ፣ ጠንካራ እና ደካማ ጎን ይኖረናል ሰዎች የጠበቁብንን ሳይሆን እኛ የሆንነውን ማንነት ነው የምንሰጣቸው ስለዚህ ሙሉ ሰው ሳይሆን እውነተኛ ሰው መሆኑን ብቻ እንየው ሌላው ቀስ በቀስ ልክ ይመጣል !

የተባረከ ቀን ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
43.2K viewsDaniel W., 05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 21:12:29 ትላንት አልፏል!

ፈጣሪ ጊዜን ከፈጠረበት አንዱ ምክንያት 'ድሮ' የሚባል ላጠፋሀቸው ጥፋቶች ሁሉ መቀበሪያ ጉድጓድ ለማዘጋጀት ነው። ታዲያ እዛ የመቃብር ስፍራ ምን ታረጋለህ ወዳጄ? ለምን ስለትላንት እያሰብክ ራስህን ታስጨንቃለህ?! ወዳጄ አሁንን መኖር ጀምር! አጠገብህ ያለውን በረከት እይና ተመስገን በል፤ ተደሰት!

ውብ ምሽት ይሁንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
43.7K viewsSinework Taye, 18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 08:03:09
ሰላም ለእናንተ ይሁን ቤተሰቦች  ሰው ስታከብረው ይንቅሃል ቦታ ስትሰጠው ከአቅምህ በላይ ይሆንብሀል ስለዚህ ናቅ ማድረግ ነው ፤ ኮራ በልበት ይባላል ግን ማነው እየተናቀ ክብር የሚሰጠው? እየተሰደበ ለሚሰድበው ሰው ትልቅ ቦታ የሚሰጠው? ይፈራው ይሆናል ፣ ይሸሸዋል ወይ እንከኑን ፈልጎ ሊያዋርደው ይመኛል እንጂ።

" ሰው ሁሉ የዘራውን ነው የሚያጭደው "

ስለዚህ ምን እናድርግ ? በዚህ ቪድዮ በጥሩ ሁኔታ መልስ ተሰጥቶበታል ፤ ከአሁን ጀምሮ በኢንስፓየር ኢትዮጵያ ዩቲዩብ ቻናል ላይ ታገኙታላችሁ !

የተባረከ ቀን ተመኘን
Inspire Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
47.4K viewsDaniel W., edited  05:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 08:53:10 ይሉኝታ !

ሰው ምን ይለኛል ካልክ ብዙ ነገር ይልሀል እልሀለው ! በእያንዳንዱ ድርጊትህ ስም ሊያወጣልህ ከፈለገ እመነኝ ጥሩ ሰራህ ወይ ለእርሱ ስትል የማትፈልገውን ነገር አደረግህለት ስም ይሰጥሀል ጥሩነትህን እንደሞኝነት እሺ ማለትህን እንዳለማወቅ መቁጠሩ አይቀርም ታድያ ሰው ምን ይለኛል ብለህ የማትፈልገውን ነገር ለእርሱ ስትል አድርገህ ከሁሉ ያጣህ መሆን ይሻላል ወይስ የምትፈልገውን በማግኘት መበርታት?

ደስ የሚል ሰኞ ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
49.9K viewsDaniel W., edited  05:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-18 20:30:43 መስጠት!

አንዳንዴ የምትወደውን ነገር ስትሰራ ይበልጥ ማተኮር ያለብህ አንተ የምትሰጠው ላይ ነው፤ የምትወደውንም ሰው ስትንከባከብ የምትቀበለውን ሳይሆን የምትሰጠው ፍቅር ላይ አተኩር፤ የፈጣሪ ቀመር ደስ የሚለው አንተ ቀንሰህ ስታካፍል እሱ በተቃራኒ ደምሮ እያባዛ መስጠቱ ነው።

የመስጠት ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
49.7K viewsSinework Taye, 17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ