Get Mystery Box with random crypto!

Inspire Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia — Inspire Ethiopia I
የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia — Inspire Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @inspire_ethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 162.42K
የሰርጥ መግለጫ

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 52

2022-10-03 08:04:07 ስኬት ቋሚ አይደለም !

ስኬት በተለያየ አቅጣጫ ይመጣል ይገኛል! ነገር ግን ስኬት የኪራይ ቤት ናት አንዴ ስኬታማ ሆኛለው ከዚህ በኋላ እድሜ ልኬን ባልሰራም ስኬቴ አብሮኝ ይኖራል የሚባል አይደለም ሁሌም ክፍያ ይጠይቃል ክፍያውን ያሳለፍን ቀን ማስጠንቀቂያ ይሰጠናል አልሰማ ብለን ከቆየን ግን ያባርረናል! አለም በሚገርም ፍጥነት እያደገች ነው ! ብዙ ትላልቅ ነገሮች እየተፈጠሩ ነው ብዙዎች የማይጠበቅ ክስተት እየከሰቱ ነው ስለዚህ ባደረግናት ትንሽ ነገር አንገረም ብዙዎች ከእርሱ አልፈዋልና ሁሌም ራሳችንን በየቀኑ ለማሳደግ እና ከአለም እኩል ለመፍጠን እንሩጥ ! ስለዚህ ባደረግነው መኩራራትን አቁመን ለተሻለ እድገት እና ስራ እንነሳ !

ደማቅ ሰኞ ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
22.0K viewsDaniel W., edited  05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 19:40:22
ሰላምታዬ ይድረስ ቤተሰቦች ትልቁ ፍላጎታችንን እንዳናሳካ የያዘን ራስን መጠራጠር ነው፤ ትምህርትና ስራ ላይ ወይ የቤተሰብና የፍቅር ህይወታችን ላይ ውስጣችን የሚያምንበት ነገር ሌላ እኛ የምናደርገው ደግሞ ሌላ ነው።

በዚህ ምክንያት የሰዎችና የሁኔታዎች መጠቀሚያ ሆነናል፤ ምን ማድረግ እንዳለብን በደምብ እንመካከራለን፤ የሰኞ ሰው ይበለን!

ነገ ሰኞ ጠዋት 2 ሰዓት በ Inspire Ethiopia ዩቲዩብ ቻናል እንገናኝ

ውብ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
27.7K viewsSinework Taye, 16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 09:48:52 ራስህን ፈትሽ !

አስኪ ራስህን ፈትሽ የዛሬ አምስት ዓመት ማን ነበርህ? ምን አይነት ሰው ለመሆን ነበር ያቀድከው ? ያኔ ላይ ሆነህ ዛሬ ማን እሆናለው ብለህ ስለህ ስትጠብቅ የነበረው ? ታድያ ዛሬስ ማን ሆነሀል ያ የተመኘኸው ያሰብከው ብሆን ያልከው ሰው ዛሬ አግኝተኸዋል ወይስ ከአምስት አመት የነበረውን ህልም ዛሬም እያለምክ ነው? ዛሬ ራስን የመፈተሻ ቀን ነው ስለዚህ ራስህን ፈትሽ!

መልካም ሰንበት ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
31.2K viewsDaniel W., 06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 21:08:33 አሁን ሞክር!

ዕድሜህ ካለፈ በኋላ ያሳለፍከውን መለስ ብለህ ስታስብ ካደረካቸው ይበልጥ ያላደረካቸው
ይቆጩሀል፣ 'ምናለ ሞክሬው ቢሆን አድርጌው ቢሆን ኖሮ' ትላለህ፤ እንዳትል ግን አሁን የምትቸለውን ሁሉ ሞክር እና ማን እንደሆንክ ለራስ አሳየው! አለዛ ቁጭት ነው ትርፍህ።

የሚገርም ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
34.3K viewsSinework Taye, 18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 08:51:03 ፍርሀትህ ከፈጣሪ አይበልጥም !

ፍርሀት ማለት ፈጣሪን አለማመን ወይ አትችልም ብሎ መቃወም ነው ከእርሱ በላይ አቅም ያለው አለ እንደማለት ነው ከእርሱ ሌላን አግዝፎ እንደማሰብ ነው ፤ ደግሞም እኮ የፈጣሪ ውድ ስጦታ ያለው ከፍርሀታችን በስተጀርባ ነው እርሱን አምነን ከምንፈራው ነገር ስንሻገር ያኔ ሽልማቱን ይሰጠናል ፤ የሁሉ ነገር ባለቤት የሆነን አምላክ ይዘን የትም እንደርሳለን!

ደስ የሚል ቀን ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
37.2K viewsDaniel W., 05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-30 20:38:34 ለመንቃት አታርፍድ!

ሞት ተፈርዶበት አንገቱ ውስጥ ገመድ ገብቶ የመጨረሻ ቃል ተናገር ተባለ፤ ከዛ ኮስተር ብሎ "ይብላኝ ለእናንተ እኔስ ትምህርት ወስጃለው" አለ አሉ።

ስለዚህ ከትናንሽ ስህተቶችህ ቶሎ ካልተማርክ ባለቀ ሰዓት ከነቃህ ትርፉ ቁጭት ነው፤ ከነቃህ አይቀር አታርፍድ ወዳጄ!

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
38.6K viewsSinework Taye, 17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-30 08:36:41 ሚስጥር ልንገራችዉ!

በቀላሉ ስኬታማ መሆን ያሰበውን ማሳካት የሚፈልግ ማነው? ይሄን ለማሳካት ብዙ ነገሮች ሊጠይቅ ይችላል ጥረት ፣ የሚጠየቅብንን መስጠት መገኘት ያሉብንን ቦታዎች ማወቅ የመሳሰሉት ግን ከነዚህ በላይ ዋናው እና ትልቁ ምስጢር ትህትና ነው ስኬታማ ሰው ዋናው ምልክቱ ትሁትነቱ ነው! በማንኛውም ሁኔታ እውነተኛ ደስታን የምናገኘው እኛ ከምንቀበለው ሳይሆን ከምንሰጠው ነገር ነው ! ስለዚህ ትህትና መለያህ ይሁን!

መልካም ጁምዓ ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንው ምርጥ ጓደኛ
42.0K viewsDaniel W., 05:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 20:59:16 ታልፈዋለህ!

"ፈጣሪ ስጦታ ሊሰጥህ ሲል የስጦታው መሸፈኛ ችግር ነው፤ ትልቁ የፈጣሪ ስጦታ ሊሰጥህ ሲል በትልቅ ችግር ተጠቅልሎ ይደርስሀል" ይለናል ደራሲ ኖርማል ቪንሰንት ፔል።

አሁን የገጠመህ ችግር የማይታለፍ ቢመስልም ብዙ ስጦታዎች ይዞ እንደሚመጣ አትጠራጠር!

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
11.1K viewsSinework Taye, 17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 08:04:01
በከባድ ፈተና ውስጥ ራስህን መፍጠር እንደምትችል ታውቃለህ ?

የህይወትህ አስቸጋሪ ወቅት ላይ ልትሆን ትችላለህ ምኑን ከምኑ እንደምታቻችል ፣ የትኛውን ማስቀደም እንዳለብህ ፣ የቱን መተው እንደሚጠበቅብህ መላቅጡ ጠፍቶህ ይሆናል ፤ አይዞህ ብዙ ሰው ጋር ይሄ ስሜት አለ ።

ችግሩን መካድ አይጠበቅብህም 'በስታይል' ማለፍ ግን ትችላለህ !

ኢንስፓየር ኢትዮጵያ ኮሮና በከፍተኛ ደረጃ በተስፋፋበት ፣ ሁሉም በሩን ዘግቶ በተቀመጠበትና ኑሮ ባሻቀበት ወቅት እንደተፈጠረስ ያውቃሉ ?

ህይወትህን ለመቀየር አንድ ውሳኔ በቂ ነው !

ባሉበት ቦታ በምቾት ተቀምጠው ራስ ላይ መስራት ተችሏል !

በዚህ ስልጠና የአመለካከት ለውጥ እንዲያመጡ ፣ የተግባር ሰው እንዲሆኑ ፣ የተሻሉ ውሳኔዎችን መወሰን እንዲችሉ ፣ ትልቅ እንዲያስቡና የይቅርታ ልብ እንዲኖርዎ እናግዞታለን ።

ስልጠናው በኦንላይን ' Zoom App ' ነው !

የፊታችን ረቡዕ መስከረም 25 16ተኛ ዙር ስልጠናችን ይጀመራል ፤ በሳምንት ሁለት ቀን ረቡዕ እና ቅዳሜ ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ 5 ሰዓት ራስ ላይ የሚሰራበት ሰዓት ነው !

    ▸ Silver           ▸ Gold          ▸ Platinum

ስልጠናው በሶስት አማራጮች ቀርቧል ያሻዎትን መርጠው አሁኑኑ ይመዝገቡ !

ለመመዝገብና ቦታ ለማስያዝ ከታች ባለው ቁጥር በቴሌግራም ወይም በዋትስ አፕ መልዕክት ይላኩ ።

+251944314544

የተባረከ ቀን ተመኘን
Inspire Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
12.2K viewsDaniel W., 05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 20:46:24 መጀመሪያ አንተ ተቀየር!

ለሰዎች መምከርማ እንችልበታለን! ምን ቢያደርጉ እንደሚሻል ከነሱ በላይ እኛ እናውቃለን፤ ችግሩ እሱ አይደለም "ለራሴስ እንዴት ልወቅበት?" ነው ጨዋታው።

አንድ የማከብረው ሰው "አገሬን እቀይራለው ብዬ ተነሳው ብዙም ሳልቆይ እንደማይሆን ገባኝ፣ አይ መቀየር ያለብኝ ከተማዬን ነው አልኩ እሱም እንደማይሳካ ሲገባኝ ሰፈሬን አልኩ፣ ከዛ ቤተሰቦቼን አልኩ....በመጨረሻ የገባኝ ነገር መጀመሪያ ራሴን መቀየር እንዳለብኝ ነው" ይለናል።

ጣፋጭ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
20.9K viewsSinework Taye, 17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ