Get Mystery Box with random crypto!

Inspire Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia — Inspire Ethiopia I
የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia — Inspire Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @inspire_ethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 162.42K
የሰርጥ መግለጫ

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 53

2022-09-28 08:12:03 ካልቆምህ ስራህ ይመሰክራል!

አንድን ነገር ለማሳካት በጣም እየለፋህ ይሆናል ፤ የሚታይ ውጤትን ግን እስከ አሁን አላገኘህም ፣ የምትሰራበት ቦታ ላይ ከልብህ እየለፋህ ይሆናል ነገር ግን ሰዎች ሁሉ እንዳለህ እየጠቀምካቸው እንደሆነ ተፅዕኖ እንደምትፈጥር አላወቁልህም ፣ ይሄ ስሜት ያስከፋል አይደል? በዚህ ሁኔታ አይደለም ስራህን በድሮ ሞራል ለመቀጠል ይቅር እና ፈፅመህ ለማቆም እስክትመኝ ያደርስሃል አይደል? ግን ማቆም መፍትሄ ሆኖ አያውቅም ከቆምክማ ድሮም የማትጠቅመው ሰው ነህ ድሮም ልፋትህ ዋጋ ያጣው ሰው ነህ !ነገር ግን ስትቀጥል ይባስ ስትበረታ እና ከበፊቱ የበለጠ ስታበረክት ያኔ ታሸንፋለህ ያኔ ሁሉም ያውቅልሀል አንድን ነገር ስታከናውን ያለ እርሱማ ይሄ ስራ አይሆንም እስክትባል ድረስ አከናውነው ! ከዛ ስራ መራቅ ብዙዎችን ለምን የሚያስብል እስኪሆን ድረስ ድርሻህን ተወጣ ያኔ ማንም ሳያረጋግጥል ስራህ ራሱ ይፈርምልሃል!

ውብ ቀን ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
6.4K viewsDaniel W., 05:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 20:57:39 ማደግና መስጠት!

የሰውን ልጅ ደስታ ሙሉ የሚያደርገው ሁለት ነገር ነው። የመጀመሪያው ማደግ ነው፤ ከትላንት የተሻለ ማንነት፣ ዕውቀትና ልምድ እየጨመርክ እያደክ መሄድ ለአይምሮህ ሰላም ይሰጥሀል።

ሁለተኛው ደግሞ መስጠት ነው፤ ካለህ ላይ ጊዜህን፣ ገንዘብህን፣ ዕውቀትህን ወይ ሀሳብህን ስትሰጥ የመንፈስ እርካታ ይኖርሀል። ወዳጄ በየቀኑ ማደግና መስጠት ፀባይህ መሆን አለበት!

ድንቅ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
17.9K viewsSinework Taye, 17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 08:39:35
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችው በዓሉ የሰላም የደስታ የፍቅር እና የጤና ይሁንላችው !

ደስ የሚል ቀን ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
13.8K viewsDaniel W., 05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 20:54:17 ታሪክ የሚቀይር ፈጣሪ ነው!

እስከመቼ ትጨነቃለህ? ልብህ ንፁህ ከሆነ ከባድ የመሰሉህን ነገሮች በቅርቡ ታልፋቸዋለህ፤ አንተ ብቻ የምትችለውን ሁሉ አድርግ፤ እምነትህን ካጠነከርክ አጎንብሰህ አትቀርም! ወዳጄ ታሪክ የሚቀይር ፈጣሪ ነው፤ አንተ ተመልካች ነህ!

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
10.7K viewsSinework Taye, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 08:10:06 ይገኛል !

ሳትታክት ፈልግ ልታገኘው የምትሻውን ነገር ሳታገኘው በፍፁም እንዳትቆም የምትመኘውን ነገር ሳታሳካ ወደኋላ እንዳትል ጥሩ ነገር ሁሌም ያስለፋል ህልም ዋጋ ያስከፍላል አንዳንዴ የማይሳካ የማይሆን ይመስላል ስሜቱ ይከብዳል ግን ካልቆምክ እመነኝ ይገኛል ይሳካል የማይደረስበት የማይሆን ነገር የለም በጥረትህ ውስጥ ግን ሀሌም ፈጣሪን አስቀድም በእርሱ ተመራ ያኔ ሁሉም እውን ይሆናል!

የደስታ ቀን ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
10.5K viewsDaniel W., 05:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 20:30:44
ሰላምታዬ ይድረስ ቤተሰቦች ስልክ እንደ አዲስ ሲስተካከል ምርጥ ሆኖ እንደሚሰራው የኛም አይምሮ በቀላሉ እንደ አዲስ መሆን ይችላል። አይምሮአችንን ከመጥፎ ሀሳብ፣ ጭንቀት፣ ፍርሀት፣ ቁጭት አውጥተን እንደ አዲስ ማሰብ እንጀምራለን፤ የሰኞ ሰው ይበለን!

ነገ ሰኞ ጠዋት 2 ሰዓት በ Inspire Ethiopia ዩቲዩብ ቻናል እንገናኝ

ውብ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
12.1K viewsSinework Taye, 17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 09:25:37 እረፍት !

የእረፍት ቀናት ደስ ይላሉ ለመዝናናት ዘመድ ለመጠየቅ ለመተኛት ፊልም ለማየት በስራ ቀናቶቻችን በሙሉ ማድረግ ፈልገን ያልቻልናቸውን ነገራቶቻችንን የምንፈፅምባቸው ቀናቶች ናቸው ነገር ግን ከዛም ያለፈ ድንቅ ስጦታ አላቸው ይሄ ስጦታ ራስን መፈተሽ ራስን መገምገም እና ለቀጣይ እርምጃ ደሞ ራስን ማዘጋጀት ይባላሉ ስለዚህ ካለችን ቀን ቢያንስ 1ሰዓት ወስደን በዚህ ሳምንት ምን ሰራው ቀጣይስ ምን ላድርግ የሚለውን ነገር እናስተካክልበት!

መልካም ዕለተ ሰንበት
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
16.1K viewsDaniel W., 06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 19:56:48 አሁን ጀምር!

ምንም ነገር ቁጭ ባልክበት ሊሳካ አይችልም! ይህ ምድር ያንተን ላብ ይፈልጋል፤ ያንተን ጥረት ይፈልጋል፤ ለነገ መድረሻህ አሁን መዘጋጀት፣ ማቀድ እና ወደ ድርጊት መግባት አለብህ! ወዳጄ ለመጀመር ታላቅ መሆን አይጠበቅብህም፤ ታላቅ ለመሆን ግን አሁኑኑ መጀመር አለብህ!

የሚገርም ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
እናንተው ምርጥ ጓደኛ!
13.8K viewsSinework Taye, 16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 08:09:50 እስቲ ወደ ልጅነትህ ተመለስ!

ልጅ እያለህ መዳህ ማን አስተማረህ ? መንቀሳቀስ እንዳለብህ ከቦታ ቦታ መሄድ እንደምትችል ማነው ያሳወቀህ? እናትህ ፣ አባትህ ፣ ወንድምህ ወይስ አህት ወይስ ሌላ ሰው? በፍፁም ይሄንን የነገረህ የለም ግን ደግሞ አሳይተውኋል አይደል? ሲንቀሳቀሱ አይተህ አንተም መሄድ መቻል እንዳለብህ ተሰማህ ግን እግርህ ለመራመድ ስላልጠነከረ ጉልበትህን እና እጅህን አጣምረህ የምትፈልገውን አሳካህ ምናልባት መሬቱ ይዋጋ ነበር ጉልበትህ ቅዝቃዜው ኮሮኮንቹ ብቻ ብዙ ምቾት ሲነሳው የነበረን ነገር ተቋቁሞ ያለማንም እርዳታ ህልምህን ስታሳካ ነበር አይደል ለመቆም ስትጠነክርስ ማን አሳወቀህ? አሁንም ማንም አደል? ግን ብዙ አልወደቅህም? ብዙ አላባሀሉህም? ታድያ እንደዛ ስትወድቅ ስትነሳ ስትታመም ተስፋ ቆርጠህ መራመድ ይቅርብኝ ብለህ ትተኸዋል እንዴ በፍፁም አይደል ድክ ድክ ስትል ውበትህ ይበልጥ የሚያሳሳ የማትጠገብ ሆንክ አይደል አቤት መራመድ የጀመርክ ቀን እማ ማን ይቻልህ እዚም እዛም ስጥሮጥ ስትፈነጭ እንደ አንተ የሚታይ ማን ነበረ! አየህ የህይወትህን የመጀመሪያ ትግል ድል ያደረግኸውና ራስህን ችለህ መቆም የቻልከው እኮ ገና ያኔ ነው እንደዛ ቀን ከዛ በፊት ተደስተህ አታውቅም ያ ቀን ግን ደስታን አስተማረህ የሰው ልጅ የመቀየር የማደግ ለውጥ የመፍጠር የማሸነፍ ፍላጎት አብሮት ተፀንሶ አብሮት የተወለደ ነገር ነው መቼም ቢሆን መቆም አይፈልግም ታድያ ያኔ የነበረህ የልጅነት ጥንካሬ በህመም ውስጥ ማሸነፍ ብቻ ቆሞ ድል የማድረግ ማንነት በላይ ትምህርት ቤት እና እንደምትችል ማሳያ ምን አለ!

የድል ቀን ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
24.4K viewsDaniel W., 05:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 20:07:11 ሁለቱ ሸክሞች

የመጀመሪያው ጠንክሮ የመስራት ሸክም ነው፤ ሁለተኛው የፀፀት ሸክም ነው። ጠንክሮ መስራት ምናልባት 1 ኪሎ ግራም ቢመዝን ነው፤ ፀፀት ግን 100 ኪሎ ግራም ተሸክሞ እንደመዞር ነው። የቱ እንደሚሻልህ አንተው ምረጥ!

ሁላችንም አሁን ካለንበት የተሻለ ነገር እንፈልጋለን፤ በከንቱ ቀንህ ያለፈ ጊዜ "በቃ አይኔ እያየ ምንም ሳልሰራበት ቀኑ አለፈ?" እያልክ ራስህን የወቀስክበትን ጊዜ አስብ፤ አየህ ወዳጄ ጠንክረህ የምትሰራው ከፍ እንድትል ብቻ አይደለም ሁሌም ከራስህ ጋር እንድትስማማ ነው። ዳይ ወደ ስራ!

ግሩም ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
28.3K viewsSinework Taye, 17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ