Get Mystery Box with random crypto!

Inspire Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia — Inspire Ethiopia I
የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia — Inspire Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @inspire_ethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 162.42K
የሰርጥ መግለጫ

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 56

2022-09-09 20:27:40 ያንተ ጥንካሬ!

"ሁሉም ሰው ጂኒየስ ነው፤ ግን አሳ ከዛፍ ዛፍ በመዝለል ችሎታው ከተመዘነ እድሜ ልኩን የማይረባ እንደሆነ ያምናል" ይለናል አልበርት አንስታይን

ድክመታችንን ከሌሎች ጥንካሬ ጋር ካወዳደርነውማ ሁሌም የበታችነት ይሰማናል፤ ከሌሎች ዝቅ ያልን ይመስለናል። እኛን የሚዳኘን የራሳችን መስፈርት ነው፤ የሌሎች መንገድማ የሌሎች ነው!

በደስታ የተሞላ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
35.2K viewsSinework Taye, 17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-09 10:59:02
አዲስ ዓመትን ከመቀበላችው ይሄን ቪዲዮ ተጋበዙልኝ እጅግ ጠቃሚ ነው። ኢንስፖየር ኢትዮጲያ ቻናል ላይ አሁን ተለቋል!

መልካም አዲስ ዓመት
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
37.4K viewsDaniel W., 07:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-09 08:07:43 ሳትሰስት ቀና ሁን!

ሁሌም መልካም ሁን ምንም ሳትጠብቅ ስጥ የሚገባህን የሚጠበቅብህን ሳትሰስት አድርግ ቅንነት ከውስጥህ አይጥፋ ያኔ አንተ ሳትሆን ፈጣሪ ባንተ ላይ ሲሰራ ታየዋለህ ባንተ የማይቻለው እና እደርስበታለው ብለህ የማታስበውን ሁሉ ስትደርስበት እና ታሪክህ ሲቀየር ታያለህ ከአቅም በላይ ናቸው ያልሀቸው ነገሮች በሙሉ ከአቅምህ በታች ሲገኙ ታያለህ ስለዚህ ወዳጄ ለጥያቄዎችህ መልስ ለማግኘት ስትሻ ውስጥህን ከልብህ አንፃ እመነኝ ያኔ የማይመለስ ጥያቄ አይኖርህም!

መልካም ቀን ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
37.2K viewsDaniel W., 05:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 20:49:52 ከፍታው ላይ እንገናኝ!

ውስጥህ የሚናገር አንበሳ የሆነ ድምፅ አለ፤ ምንም ነገር እንደማያቅትህ፣ እንደምትችል፣ ጀግና እንደሆንክ አጥብቆ የሚነግርህ፤ በደምብ አርገህ ስማው! እመነው! እስከዛሬ ሰው ጫን አርጎ የሚነግርህን ድክመት አምነሀል እኮ፤ ከዚህ በኋላ ግን ጆሮህ የሚከፈተው ለሚለውጥህ ወይ ለሚያሳድግህ ነው እንጂ ወደ ኋላ ለሚጎትትህ አይደለም!

"የነብርን ጭራ አይዙም ከያዙም አይለቁም" ነው አባባሉ፤ አሁን ራስህን ለመለወጥ ልብህ ተነስቷል ማፈግፈግ የለም! ከፍታው ላይ እንገናኝ ወዳጄ

ደማቅ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
38.9K viewsSinework Taye, 17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 20:30:21 ደስ ይበልህ!

እውነተኛ ለውጥ በፈተናና በችግር የተሞላ ነው፤ ከንብ ማር መውሰድ የሚፈልግ ሰው ንድፊያዋን መታገስ አለበት። ወዳጄ ነገሮች ከባድ ሲሆኑ ብታዝን፣ ብታማርር ወይ ራስህን ብትጎዳ ምንም አትፈጥርም! በፈተና ደስ ይበልህ ምክንያቱም ጠንካሮች ናቸው የሚፈተኑት!

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
13.9K viewsSinework Taye, 17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 08:11:08 ያለህን በበቂ አመስግነሀል?

ዓመቱ እያለቀ ነው በቀናት የሚቆጠር እድሜ ቀርቶታል ፤ ሁላችንም በተለያየ የእድሜ ክልል ላይ ነን ዛሬ ያለንበት እድሜ ድረስ ስንኖር ፈጣሪ ብዙ ይገቡናል ብለን ያላሰብናቸውን ስጦታዎችን ሰጥቶናል ፤ ከነዚህ ድንቅ ስጦታዎች አንዱ እና ዋናው እየቆጠርነው ያለነው እድሜ እና ዓመት ነው ስለዚህ ወደ አዲስ ዓመት ለመሸጋገር ሲያበቃን በምን ያህል ስጦታዎች ባርኮ እና አንበሽብሾን ነው? ለፈጣሪስ የሚገባውን ክብር እና ስጦታ ሰጥተነዋል? ከምንጠይቀው በላይ ያለንን ብዛት አይተን ተደስተናል? አዲሱን ዓመት በምስጋና እና በተሰጠን በመርካት እንጀምረው!

የደስታ ጊዜያት ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
12.5K viewsDaniel W., 05:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 20:40:48
የከበረ ሰላምታዬ ይድረስ ቤተሰቦች ኢንስፓየር ኢትዮጵያ ለዛሬ የደረሰው መጀመሪያ በፈጣሪ ክንድ ከዛ በእናንተ ድጋፍና ፍቅር ነው። አሁንም በአዲሱ አመት ወደ እናንተ ይበልጥ ለመቅረብ ከዩቲዩብ ቻናላችን በተጨማሪ በአርትስ ቴሌቪዥን ዘወትር እሁድ ከቀኑ 11 ሰዓት እንገናኛለን።

ለውጥ በአዲስ አመት ያስፈልገኛል ብለን ለምናስብ ሁሉ በጣም ደስ የሚሉ ሀሳቦችን እሁድ መስከረም 1 ከቀኑ 11 ጀምሮ በአርትስ ቲቪ እና በዩቲዩብ ቻናላችን ይዘን እንመጣለን! ብቻ ፈጣሪ የአዲስ አመት ሰው ይበለን!

የሚገርም አዲስ አመት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia 
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
22.0K viewsSinework Taye, edited  17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 20:48:11 ላልተመለሰው ፀሎትህ አመስግን!

ለዛሬ መድረስ ቀላል አይደለም! ሀብታም ወይ ደሀ ስለሆንክ አይደለም ይሄ ቀን የተጨመረልህ፤ ጎበዝ ወይ ሰነፍ ስለሆንክ አይደለም፤ ዕድለኛ ስለሆንክ ብቻ ነው ለዛሬ የደረስከው!

ዛሬ ያንተ ቀን ነው፤ ያንተ ባይሆንማ ትንፋሽህ ተቋርጦ ይሄን ፅሁፍ እንኳን ማንበብ አትችልም ነበር። ለማመስገን የምትፈልገው ሁሉ እስኪሟላ አጠብቅ፤ ወዳጄ እንደውም ላልተመለሰው ፀሎትህ ሳይቀር አመስግን! እስትንፋስ ያለው ሁሉ ፈጣሪውን ያመስግን!

የምስጋና ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
15.8K viewsSinework Taye, 17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 10:03:43 ሁሉም ሰው የራሱ ነገር አለው !

እኛ በአንድ መንገድ ተሳካልን ደስተኛ ሆንን ማለት ሌሎች ሰዎችም ሁሉ በዛ መንገድ ነው የሚያልፍላቸው የሚያሳኩት የሚደሰቱት ማለት አይደለም ፤ እኛ የፈለግነውን መውደድ እንችላለን ነገር ግን ሌሎችን እኛ የወደድነውን እንዲወዱ የመረጥነውን እንዲመርጡ ማስገደድ አለብን ማለት አይደለም ሁሌም ቢሆን መሆን እና ማየት ያለብን የእኛ የሆነውን ለእኛ የተሰጠውን ብቻ ነው እንደ እከሌ ለምን አልሆነልኝም ወይም አልሆንኩም ብለን ልንከፋ አይገባም ፤ የተሰራነው እንደሌላው እንድንሆን ሳይሆን እንደራሳችን ሆነን እንድንኖር ነው! ስለዚህ ደስታን ከራሳችን እንፈልገው !

የደስታ ቀን ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
25.7K viewsDaniel W., 07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 20:30:32 ሁለት ዜና አለኝ!

ከባድ ዜና: ጊዜው በፍጥነት ይነጉዳል
መልካም ዜና : አንተ የምትችለውን ሁሉ እያረክ ነው

ወዳጄ ማንም የማይሰጥህ ማንም የማይነጥቅህ ሀብት ቢኖር ጊዜ ነው፤ ካልተጠቀምክበት ይጥልሀል! ከተጠቀምክበት ደግሞ ከፍ ያደርግሀል!

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
16.7K viewsSinework Taye, 17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ