Get Mystery Box with random crypto!

Inspire Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia — Inspire Ethiopia I
የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia — Inspire Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @inspire_ethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 162.42K
የሰርጥ መግለጫ

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 58

2022-08-29 19:57:56 ራስ ላይ ማተኮር!

የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል፤ ራስህን ከሰዎች ጋር የምታወዳድር ከሆነ መቼም አትደሰትም፤ ደስ ቢልህ እንኳን ደስታህ ብዙ አይቆይም! ከራሱ ጋር የሚወዳደር ሰውን ግን ማንም አያቆመውም።

በራስህ ለውጥ ደስ ይበልህ፤ ዛፎች ሁሉ እኩል አያድጉም ግን ማደግ እስከሚችሉት ከፍ ይላሉ። ወዳጄ አይንህን ከሌሎች ላይ ነቅለህ ወደ ራስህ ባየህ ቁጥር እድገትህ ፈጣን ነው፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ የአይምሮ ሰላም አለህ!

ሰላማዊ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
31.2K viewsSinework Taye, 16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 08:02:30 ይቅርታ !

ይቅርታ ለራስ የሚሰጥ ድንቅ ስጦታ ነው ሰው ይቅር ማለት ሲጀምር ህይወት ይጀምራል ፤ ሰው ሰውን የሚበድለው ስለማያውቅ ነው ! ቢያውቅማ ራሱን አይጎዳም ነበር ቢገባውማ በዳይ መሆንን አይመርጥም ነበር ግን አልገባውም ታድያ እሱ ሳያውቅ አጠፋ እኛስ ለምን እያውቅን እንሸከመዋለን? ራሳችንንስ ሌሎች በደሉን ከምንለው በላይ ለምን እንበድለዋለን? ይቅርታ ለነሱ በነፈግን ቁጥር ለራሳችንም ሰላም እየነፈግን ነው ! ስለዚህ ይቅር ከኛ ይውጣ እንበል !

የሰላም ሰንበት ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
35.4K viewsDaniel W., 05:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:47:00
ሰዎች እንዲሁ ሊፈልጉህ አይችሉም! አንተን ለመፈለግ ወይ አንቺን ለመውደድ ምክንያት ይፈልጋሉ፤ ታዲያ ምን ይሻላል? ስለዚህ ወዳጄ ከሰው መጠበቁን አቁምና ራስህ ላይ አተኩር! ጠንካራ ጎንህ ላይ ጠንክረህ ስራ፣ ህልምህን አሳድ፣ ማንነትህን በስራህ ወይ በትምህርትህ አሳይ! በዚህ ሀሳብ እንጨዋወታለን፤ ብቻ ፈጣሪ የነገ ሰው ይበለን!

ነገ ሰኞ ጠዋት 2 ሰዓት በ Inspire Ethiopia ዩቲዩብ ቻናል እንገናኝ

ጣፋጭ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
36.8K viewsSinework Taye, edited  17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 08:47:10 እኔ እችላለሁ

ለራስህ እንዲህ ብለህ ንገረው አይምሮህ መሬት ነው የዘራህበትን ነው የሚያበቅለው።
1. እኔ ልዩ ነኝ! እኔ ድንቅ ነኝ!
2. እኔ እችላለሁ!
3. በጎ አሳቢ አይምሮ አለኝ!
4. የጀመርኩትን የህይወትና ጉዞ በድል እጨርሳለሁ!
5. ስኬታማም፤ ደስተኛም፤ መንፈሳዊም ነኝ!

ይሄኝ ለራስህ መንገር ወይ ድምፅ አውጥተህ ማንበብ ብቻ ስሜትህን ይቀይረዋል፤ ቀንህን ስለ ድክመትህ፣ ስለ ጭንቀትህ፣ ስለ ችግርህ በማሰብ አትጀምር! ምክንያቱም ጭንቀትና ችገር ከዘራህ ጭንቀትና ችግር ነው ምታጭደው፤ አይምሮህ ውስጥ አሪፍ ነገር ዝራ ወዳጄ!

ደማቅ ሰንበት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
38.2K viewsSinework Taye, 05:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:48:32 አሁን ሞክር!

ዕድሜህ ካለፈ በኋላ ያሳለፍከውን መለስ ብለህ ስታስብ ካደረካቸው ይበልጥ ያላደረካቸው
ይቆጩሀል፣ 'ምናለ ሞክሬው ቢሆን አድርጌው ቢሆን ኖሮ' ትላለህ፤ እንዳትል ግን አሁን የምትቸለውን ሁሉ ሞክር እና ማን እንደሆንክ ለራስ አሳየው! አለዛ ቁጭት ነው ትርፍህ።

ግሩም ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
39.8K viewsSinework Taye, 17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 08:31:52 መጀመሪያ እኛን እንይ !

አብዛኛውን ግዜ ላሳኩ ሰዎች አስተያየት መስጠት ይቀናናል ፣ እንዲህ ቢያደርጉ ኖሮ እንደዚያ ቢፈጥሩ እኮ የተሻለ ያገኙ ነበር የተሻለ ይሆንላቸው ነበር ፣ እንደዚህም ቢጨምሩበት እንላለን እነሱ ያንን ነገር ሲያሳኩ እኮ ብዙ ነገሮችን ሞክረው አይተው ተረድተው ነው! ምን አልባት ግን እኛ እነሱ የደረሱበት ሩቧን እንኳን አልሞከርናትም አንዳንዴ አስተያየት ለመስጠት የምናባክነውን ግዜ ከነሱ ለመማር ብንጠቀመው ከእኛም አልፈን ለብዙዎች እንተርፋለን!

ደስ የሚል ቅዳሜ ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
41.8K viewsDaniel W., 05:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 20:01:02 ያንተ ተስፋ ማነው?!

እንደ አንተ ጭንቀትና ሀሳብ ቢሆን ዛሬን ማየት የማይታሰብ ነበር፤ ያንን ጊዜ ማለፍ ቅዠት ነበር፤ ግን አለፍከው፤ ያልገመትከው ሁሉ ሆነ አንተ ተስፋ ቆርጠህ ስትጨርስ ፈጣሪ ጀመረ። ያንተ ተስፋ የዚህ አለም ተለዋዋጭ ነገር አይደለም! ያንተ ተስፋ የማይለወጠው፣ በዘመናት የማያረጀውና የማያልፈው ፈጣሪህ ነው!

አስደሳች ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
43.3K viewsSinework Taye, 17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 08:18:13 ስኬት እና ደስታ በእጃችን ነው!

ስኬታማ እና ደስተኛ ሰዎች ፍቅር የተሞሉ ናቸው ፤ ሁሌም ቢሆን ከመስጠት አይቆጠቡም ከማድረግ ወደኋላ አይሉም ለመጣው ሰው ሁሉ ሰላም ፍቅር መረጋጋትን ይሰጣሉ ሁሉም ሰው እነሱ ባሉበት መገኘትን ይወዳል ፤ ስለዚህ ስኬትን እና ደስታህን እሩቅ አትፈልገው ከውስጥህ ፍጠረው ከልብህ ሁን ከልብህ ውደድ ከልብህ ስጥ ያኔ ከልብህ ትደሰታለህ!

ደስ የሚል ጁምዓ ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
44.1K viewsDaniel W., 05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 19:21:29
ሰላም ለእናንተ ይሁን ቤተሰቦች በህይወት መንገድ ላይ ሁሌም ምኞት አለ እንዲህ ባደርግ እንዲያ ቢሆንልኝ እዚያ ጋር ብደርስ እያልን ብዙ መጓዝ እናስባለን በዚህ መሀል ግን ዛሬ የምትባል ድንቅ ስጦታ እንዳለችን እንዘነጋለን ፤ ዛሬ የተሰጠንን ስጦታ ከማጣጣም ይልቅ ነገን በመናፈቅ እና ስለነገ በማሰብ የምናባክነው ግዜ ቀላል የሚባል አይደለም ! በዚህ ቪድዮ ዛሬን ስለመኖር እንወወያለን ድንቅ ስጦታችንን ከማጣጣም እንጀምር!

ደስ የሚል ምሽት ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
45.3K viewsDaniel W., 16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 08:26:55 ስኬት የኪራይ ቤት ነው!

ስኬት ዋጋ መክፈልን ይጠይቃል ልናገኘው ለምንፈልገው ነገር ሁሌም ልንተጋለት በየቀኑ ሊሰጠው የሚገባውን ነገር ልንሰጠው ይገባናል ! አንዴ አሳክቻለው ብለን ቆመን የምናየው ነገር አይደለም ዛሬም ነገም ከነገ ወድያው ከስር ከስሩ እየኮተኮትን ልናሳድገው ይገባናል ካለበዚያ ግን የቤቱን ኪራይ እንዳልከፈለ ሰው ዋጋ ባለመክፈላችን እንባረራለን!

የስኬት ጊዜ ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
45.8K viewsDaniel W., 05:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ