Get Mystery Box with random crypto!

Inspire Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia — Inspire Ethiopia I
የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia — Inspire Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @inspire_ethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 162.42K
የሰርጥ መግለጫ

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 59

2022-08-24 20:35:33 በፈጣሪህ እመን...ከዛ በራስህ እመን!

"ማየት ማመን ነው" ሲባል እንሰማለን ግን አንድ ነገር ካየኸውማ ማረጋገጥ ነው የሚባለው። ማመን ያለብህ ገና ያላየኸውን ነው፤ ገና እጅህ ውስጥ እንዲገባ የምትፈልገውን ደስታ፣ ሀብትና መንፈሳዊ እርካታ ገና ከመሳካቱ በፊት እንደሚሳካ እርገጠኛ መሆን ነው ማመን ማለት።

እልም ባለ ጨለማ ውስጥ ብርሀን የሚያይ ሰው ከምንም ነገር ይወጣል፤ ወዳጄ እምነት እንዳለው ሰው ሀያል የለም፤ አስፈሪ የሚመስሉ ሁኔታዎችና ነገሮች ሁሉ በእምነትህ ፊት ቁጫጭ ናቸው!

ውብ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
47.5K viewsSinework Taye, 17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 09:39:59 "አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም !"

ስላላወቅኩ ነው አልሰማውም ነበር ብለን ከፍርድ መዳን አንችልም በላይኛውም በዚህኛውም ምድር ጥፋት ሁልግዜም ጥፋት ነው ! በህይወትም ባለማወቅ ፣ ባለመረዳት ብዙ ነገሮችን አጥተናል ከዚህ በኋላ ግን እስቲ ይብቃን መንገዳችን የተበላሸ ሲመስለን ኑሮ ሲቆረቁረን እስቲ ራሳችንን እንፈትሸው ልክ ያልሆነውን ነገር ተምረን እንለውጠው ለማወቅ አንተኛ!

የተባረከ ቀን ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
48.7K viewsDaniel W., 06:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 20:40:44 እችላለሁ በል!

ለትልቅ አላማ ነው ወደዚህ ምድር የመጣኸው ግን የምትፈልገውን ሁሉ ማሳካት እንደማትችል እያመንክ ስለሆነ ከአብዛኛው ሰው ጋር ለመመሳሰል እየጣርክ ነው። እንደ ንስር ከፍ ብለህ መብረር እየቻልክ ለምን እንደ ዶሮ መሬት ትጭራለህ?

ትልቅ ነገር የምታሳካው መጀመሪያ በነፃነት ትልቅ ማሰብ ከቻልክ ነው፤ አየህ መጀመሪያ ሀሳብ ትዘራለህ ከዛ ወደ ተግባር ትገባለህ። ወዳጄ አልችልም የሚለውን ትብታብ በጥሰህ የፈለከውን ሁሉ ለማሳካት ፈጣሪ እንደፈቀደልህ ራስህን አሳምነው! አሁን ለራስህ እችላለሁ ከማለት ጀምር!

የሚገርም ምሸት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
50.7K viewsSinework Taye, 17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 07:39:52 "እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል!"

አንዳንዴ የሆነ ቦታ ላይ የምንፈልገው ነገር ይኖራል ከእርሱ ውጪ ምንም ነገር የሌለ ይመስለናል ፤ አልተሳካም ማለት በቃ አለቀልን መንገድ ላይ መቅረታችን ነው ፣ የእኛ ነገር አበቃ ተበላሸ ይመስለናል ግን ደግሞ ከአጠገቡ ሌላ ትልቅ እድል ትልቅ ህይወት ተቀምጦ ይጠብቀናል የፈጣሪ አላማ እኮ ሁሌም ለእኛ የሚበጀውን መስጠት ነው እንጂ ፈፅሞ ሊጥለን አይፈቅድም የአንዱን በር ሲዘጋብን ሌላውን ወለል አድርጎ እየከፈተው ነው ስለዚህ አትቁም ዞር ዞር ብለህ ተመልከት ይሄ ተዘጋ እንግድያው ያ ተከፍቷል በል መቼም አትቁም!

የስኬት ቀን ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
52.5K viewsDaniel W., 04:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 20:06:02 ለውጥ ህመም አለው!
53.6K viewsSinework Taye, 17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 08:00:49 ተማመን ጥያቄህ ይመለሳል!

"ፈጣሪ ለጥያቄዎችህ ሁሉ ፈጣን ምላሽ ሲሰጥህ እምነትን እያስተማረህ ነው ፤ ትንሽ ከዘገየ ትዕግስትን እያስተማረህ ነው ፤ በጣም ከዘገየ ግን ከጠየቅኸው የተሻለ እጥፍ እያዘጋጀልህ ነው!" ስለዚህ ጥያቄህን ለፈጣሪ ብቻ ስጥ ከዛ ግን መመለሱ እንደማይቀር እመን መንገዱ ይለያይ እንጂ ሁሉም ጥያቄ ይመለሳል!

የበረከት ሰኞ ይሁንላችው
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
54.1K viewsDaniel W., 05:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 20:02:34
ሰላም ለእናንተ ይሁን ቤተሰቦች አንዳንዶች ከ 20 ዓመት በኋላ ባለው ጊዜ ሁሌ የሚቆጫቸውን ስህተት ይሰራሉ፣ አንዳንዶች በዋዛ ፈዛዛ ያባክኑታል፣ ጥቂቶች ብቻ ተጠቅመውበት ያልፋሉ።

የማህበራዊ ሳይንቲስቶች እና ሳይኮሎጂስቶች በዚህ ዕድሜ የሚወሰን ውሳኔ ቀሪው ዘመናችንን ይወስነዋል ይላሉ። ገና 20 ያልሞላን፤ 40 ዓመት ያለፈን ብንሆን እንኳን ብዙ ነገር እናተርፍበታለን። የነገ ሰው ይበለን!

በ Inspire Ethiopia ዩቲዩብ ቻናል ነገ ጠዋት 2 ሰዓት እንገናኝ

ደስ የሚል ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia 
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
54.0K viewsSinework Taye, edited  17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 20:17:12 መለወጥ አለብህ!

ህልምህን ከመኖር በላይ የአይምሮ ሰላም የሚሰጥህ ነገር የለም፤ ወደምትፈልገው መንገድ መጓዝ የምትጀምረው መቼ ነው? ሰው እንዴት ወደ ምስራቅ መጓዝ እያለበት ወደ ምዕራብ ይሄዳል? ከማይጠቅሙህ ሰዎች ጋር መሆን የምታቆመው መቼ ነው? ጊዜህን በዋዛ ፈዛዛ የሚያባክኑ ነገሮችን ከህይወትህ ቆርጠህ የምታወጣው መቼ ነው?

ስኬትና የህይወት እርካታ ዋጋ ያስከፍላሉ፤ በነፃ አይገኙም። አንተ ደግሞ እንኳን ለሚጠቅምህ ለማይጠቅምህም ነገር ዋጋ ከፍለህ ታውቃለህ፤ አሁን ሰዓቱ ራስህን እስከ መጨረሻው ስለ መቀየር የምናወራበት ነው! ወዳጄ አሁን የሚያስደስትህን ሰው ስለመሆን በማሰብ ጀምር፤ ከዛ ወደ ተግባር ግባ! አለቀ ዋጋ መክፈል ይሄ ነው! መለወጥ አለብህ! ቆሞ መቅረት የለም!

ታሪካዊ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
13.0K viewsSinework Taye, 17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 07:42:26 የመፍትሄ ሰው ሁን !

ማደግ ከፈለግህ የመፍትሄ ሰው ሁን "መፍትሄ ወዳለበት ገንዘብ ይፈሳል " ስለዚህ ምንም የምሰራው አጣው ካልክ ውጣ እና ዞር ዞር ብለህ አካባቢህን ቃኝ ምን ምን የጎደለ ነገር አለው? ሰዎች ምን አስፈልጎቸዎል? በዚህ ምድር ላይ ያለ ስራ ሁሉ የተፈጠረው መፍትሄ ለመስጠት ነው ህክምናው፣ ትምህርቱ ፣ ምግብ ቤቱ ፣ ልብስ ሰፊው ፣ ሊስትሮው ሁሉም የሰዎችን ችግር በመቅረፋቸው ሰው ወደ እነርሱ እየሄደ ገንዘቡን ያፈሳል ! እድለኛነታችን የእኛ ሀገር ብዙ መፍትሄ የሚፈልጉ ጥያቄዎች መኖራቸው ነው ስለዚህ የመፍትሄ ሰው እንሁን! ያኔ ከእኛም ተርፈን ለብዙው እንሆናለን!

የተቀደሰ ሀሙስ ተመኘን
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
25.1K viewsDaniel W., 04:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 21:17:41 መፍራት የለም!

በህይወት አስጨናቂ ወቅቶች የሚመጡት ለአጭር ጊዜ ነው ግን የዘላለም ያህል ይረዝማሉ፤ ያንተ ማንነት ነጥሮ የሚወጣው በዚህ ከባድ ወቅት ነው፤ ጀግና ታላቅነቱ የሚታየው ከብርቱ ጠላት ጋር ሲፋለም ነው!

የገጠመህ ከባድ ችግር ከኋላው የፈጣሪን ስጦታ የያዘ ሊሆን ይችላል፤ አንተ አላየኸውም ማለት ደግሞ የለም ማለት አይደለም! ፈርተህ የትም አትደርስም የምትችለውን እያረክ መጋፈጥ አለብህ ወዳጄ!

ጣፋጭ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
29.2K viewsSinework Taye, edited  18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ