Get Mystery Box with random crypto!

Inspire Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia — Inspire Ethiopia I
የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia — Inspire Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @inspire_ethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 162.42K
የሰርጥ መግለጫ

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 55

2022-09-18 07:43:20
"አንድ አይን ያለው በአይን አይቀልድም" ይባላል፤ አንተም አንድ ህይወት ነው ያለህ፤ ፈጣሪ በሰጠህ ዕድሜ ያመንክበትን ማድረግ አለብህ! "እኔኮ አልችልም! ይሄ ይጎድለኛል! እድል የለኝም!" እያልክ እስከመቼ ትቀጥላለህ?

አንድ ሰው አስተሳሰቡን ሲቀይር ሁሉ ነገሩ ይቀየራል! እንዴት አርገን በአመለካከት ራሳችንን እንደምንለውጥ ደግሞ ዛሬ እናወራለን።

ዛሬ እሁድ ከቀኑ 11 ሰዓት በአርትስ ቲቪ እና በኢንስፓየር ኢትዮጵያ (Inspire Ethiopia) ዩቲዩብ ቻናል እንገናኝ!

ግሩም ዕለተ ሰንበት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
52.6K viewsSinework Taye, edited  04:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 20:24:52 ብቻህን አይደለህም!

ነገሮች በምትፈልገው መንገድ አልሄድ ሊሉህ ይችላሉ፤ ስራው፣ ትምህርቱ፣ ትዳሩ የፍቅር ግንኙነቱ አልጨበጥ ብሎ አስቸግሮህ ይሆናል፤ ብቻህን አይደለህም ሁላችንም ጋር የሆነ ጉድለት አለ።

በየቀኑ ራሳችንን ለማሳደግ ትናንሽ ነገሮችን እየጨመርን ከሄድን ይሄን የምናነብ ሁሉ ከፍታው ላይ እንገናኛለን! እውነተኛ ለውጥ የሚመጣው በሂደት እንጂ በድንገት አይደለም! ስለዚህ ጥረታችንን አናቆምም

ድንቅ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
55.8K viewsSinework Taye, 17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 08:07:44 ጠዋትህን ጠብቃት!

ህይወት የምርጫ ጉዳይ ናት ጠዋት ከእንቅልፋችን ስንነቃ ቀናችንን የሚወስን አማራጭ ይቀርብልናል ፤ ያኔ ግን ተጠንቅቀን መወሰን የእኛው ምርጫ ነው ቀናችን ብሩህ እንዲሆን ከተመኘን ጠዋታችንን በፍቅር እና ደስ በሚል መንፈስ ከእኛ አልፈን ለሌሎች ሰላምን ፍቅርን እና መልካምነትን በመስጠት እንጀምረዋለን ያኔ ቀኑ የእኛ ሲሆን እና በእኛ ላይ ሲያበራ ይውላል በተቃራኒውም ከመረጥን እንደዛው ስለዚህ ቀናችንን እንድንገዛው እና የእኛ እንድናረገው ጠዋታችንን እናስተካክለው!

መልካም ጁምዓ ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
58.1K viewsDaniel W., 05:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 20:23:32 ፅናት ያስፈልግሀል!

አንተን ከምትፈልገው ነገር የሚያገናኝህ የአላማ ፅናት ነው፤ በህይወት የሚያሸንፈው ብርቱ የሆነ ወይ አስተዋይ (Smart) የሆነው አይደለም፤ ውስጡ ላመነበት ነገር እስከ መጨረሻው የሚጓዝ ነው።

ወዳጄ ኑሮ ሊያደክምህ፣ ነገሮች ሊሰለቹህ፣ ህይወት ተደደጋሚ ልትሆን ትችላለች፤ የደስታን ጥግ ማየት ከፈለክ ግን ላመንክበት ጉዳይ መኖር ጀምር ከዛ በአላማህ ፅና!

አስገራሚ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
57.0K viewsSinework Taye, 17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 08:26:02 ራስህን ሁን!

በፍቅር ግንኙነትህ ላይ በጓደኝነት በስራ ቦታ ባጠቃላይ ህይወትህ ላይ ማንነትህን መቀየር እና ማስመሰል መሞከር ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍልሀል! መቼም ቢሆን ሰው ከራሱ ተነጥሎ ረጅም ጊዜያትን መቆየት አይችልም ቢችል እና ቢያደርገው እንኳን የሆነ ውስጡ በድብርት እና ራሱን በመጥላት ውስጥ ይገባል ሰዎችም እውነትን ስለማያዩበት እርሱ ጋር አብሮ መቆየትን መስራትን እና ለተሻለ ነገር መሾምን አይፈልጉም ስለዚህ የመጣው ቢመጣ እና የሆነው ቢሆን ራስህን ሁን የተሻለው አንተን ስራው ሰዎች ሳይሆኑ አንተ ራስህን እስክትቀበለው ድረስ ምርጥ አድርገህ ስራው!

ስኬታማ ቀን ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
58.3K viewsDaniel W., 05:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-14 20:42:57 በህይወት ስትኖር ማወቅ ያሉብህ 3 ነገሮች

የምትፈልገውን ሳይሆን የሚገባህን ነው የምታገኘው ስለዚህ በሙሉ አቅም መጣር አለብህ
ለብዙ ሰው የሚያስፈልገውን ስታረግ ላንተም የምትፈልገውን ሁሉ ታገኛለህ
ስትፈልገዉ ያጣከውን ነገር ትንሽ ከታገስክ በተራው ሲፈልግህ ታገኘዋለህ

የተባረከ ምሽት ተመኘንላችሁ
@inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
57.4K viewsSinework Taye, 17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-14 08:50:17 ከጥቂቶቹ ብንሆነስ!

ሁሉም ሰው ፊቱ የሚታየውን ደስታ የሚያይለት እና አብሮት ሊስቅ የሚችል ጓደኛ ያገኛል ነገር ግን የልቡን ጉዳት ተረድቶ የሚያቀልለት እና ከህመሙ የሚያድን ትንሽ ነው ፤ ከሳቀው ጋር ከመሳቅ በላይ የከፋውን እነደማስደሰት የሚያረካ ነገር የለም ! ከጥቂቶቹ አንዱ ምርጡ ጓደኛ ለመሆን የሚፈልግ ማነው?

ምርጥ ቀን ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
59.3K viewsDaniel W., 05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 09:36:56
ያንተ አመት ነው!

ዛፍ ለመትከል ወሳኙ ጊዜ ከ 20 ዓመት በፊት ነበር፤ ከዛ ቀጥሎ ግን ወሳኙ ጊዜ አሁን ነው! በምንፈልገው ጉዳይ ራሳችንን ለመለወጥ ጊዜው አልረፈደም፤ መወሰን ከዛ ወደ ተግባር መግባት ብቻ ነው ከኛ የሚጠበቀው። ቆራጥ ሆነን መለወጥ ለምንፈልግ ሁሉ ቀላል የሆኑ መንገዶችን እናወራለን!

ዛሬ እሁድ ከቀኑ 11 ሰዓት በአርትስ ቲቪ እና በኢንስፓየር ኢትዮጵያ (Inspire Ethiopia) ዩቲዩብ ቻናል እንገናኝ!

የለውጥ አዲስ አመት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
17.5K viewsSinework Taye, 06:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 20:07:07 ወዳጄ እንኳን አደረሰህ...እህቴ እንኳን አደረሰሽ!
ዛሬ ላይ የቆምን ሁሉ እድለኞች ነን፤ ያለፈውን አመት ያልተሻገሩ ከመቃብር በታች ያደሩ ብዙዎች ናቸው።

እኛ ግን የምንፈልገውን እንድንሆን፣ አላማ እንዲኖረን፣ ፍቅር እንዲኖረን፣ ትዳር እንዲኖረን፣ ልጅ እንዲኖረን፣ ሀብት እንዲኖረን ፣ ደስታና እርካታ እንዲኖረን ይሄ አመት ተጨምሮልናል። አመቱ የኛ ነው!

የሚያስገርም አመት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
28.6K viewsSinework Taye, 17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 09:01:08 ታሪክ ይቀየራል !

ህልም የሚመስሉ እደርስባቸዋለው ተብለው የማይታሰቡ ነገሮች በሙሉ እውን ይሆናሉ ፤ አይሳኩም የሚባሉ ሁሉ ተሳክተው ይገኛሉ ፣ በህልማችን እንኳን ይሆንልናን ብለን ያላሰብናቸውን ነገሮች ሆነውልን አይተናል! እና ለፈጣሪ ምን ይሳነዋል! ቀና እና ዝግጁ አድርገን ከጠበቅነው የፈለግነውን ቢደረግልን ብለን አብዝተን የተመኘነውን ነገር በደንብ አድርጎ ይሰጠናል! አስታውሱ በእስከዛሬ ህይወታችን ስንት ድንቅ ተዓምር አይተናል? ስለዚህ ተዓምራቱ ይቀጥላል!

ምርጥ ዋዜማ ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
32.3K viewsDaniel W., 06:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ