Get Mystery Box with random crypto!

Inspire Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia — Inspire Ethiopia I
የቴሌግራም ቻናል አርማ inspire_ethiopia — Inspire Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @inspire_ethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 162.42K
የሰርጥ መግለጫ

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 57

2022-09-03 20:36:04 ትኩረትህን ቀይር!

ግራንት ካርደን የተባለ ሚሊየነር "በጣም የሚያበሳጭ ነገር በገጠመኝ ቁጥር ወረቀት አውጥቼ ትልቁ ህልሜን እፅፈዋለው፤ ከዛ እንደገና አዲስ ጉልበት እና ሀይል እሞላለሁ" ይለናል። አይንህን ከትናንሾቹ ችግሮችህ ንቀልና ትልቁ መድረሻህ ላይ አድርግ!

ትኩረትህ ወዳለበት ጉልበትህ ይፈሳል፤ ከጥቃቅን ድክመቶችህ እና ሰው ምን ይለኛል ከሚለው ጭንቀትህ ይልቅ ስለ ትልቁ ፍላጎትህ ማሰቡ ብርታት ይሰጥሀል። በህይወት ወሳኙ የገጠመህ ችግር አይደለም...ወሳኙ ያንተ ምላሽና ቆራጥነት ነው!

የደስታ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
12.2K viewsSinework Taye, 17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 10:45:54 የሞተን ውሻ ማንም አይደበድበውም !

ካልሰራህ ማንም ሰው ሊተችህ እና እንዲህ ሁን እንዲያ አድርግ ሊልህ አይችልም ትችቶች ወቀሳዎች እና ነቀፌታዎች የሚበዙት ከፍ ያለ ቦታ ላይ ያለ ሰው ነው ስለዚህ ትችቶች ከፍ ማለትህን መታየትህን የሚያሳይህ ምልክት ነው እና በርትተህ መንገድህን ቀጥል!

ደስ የሚል ቅዳሜ ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
5.7K viewsDaniel W., 07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 20:32:59 እግረ መንገድህን መኖር አቁም!
22.3K viewsSinework Taye, 17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 09:27:20 ከሁኔታዎች በላይ ሁን!

ወዶ የሚያጠፋ ሰው የለም ሁሉም ለጥፋት የሚያበቃው የደረሰበት የህይወት ውጣ ውረድ ነው ያለበት ቦታ የሚያስገኘው ፣ ነገር ግን አንድ ነገር ማድረግ ይችላል ፤ ራሱን መቆጣጠር ስሜቶቹን መጠበቅ ያኔ ሁኔታዎቹ ካስገደዱት ማንነት ወጥቶ የተሻለ ሰው ይሆናል ፣ ክፋ መሆን ለማንም የተበደለ ሰው ይቀለዋል ከዛ አልፎ ግን በደሉን ትቶ መልካም ሆኖ የሚያሸንፍ እሱ ጀግና ነው ህይወት ራሷ ትከፍለዋለች! እኛ ሰዎች ከሁሉም ነገር በላይ ነን ልንቆጣጠራቸው ነው የተፈጠርነው! ስጦታችንን እንጠቀምበት!

የተባረከ ቀን ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
10.9K viewsDaniel W., 06:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 20:01:03 ማቆም የለም!

ነገሮች ከፍ ዝቅ እያሉ ይሆናል፣ ከመቀጠል ይልቅ ማቆም የተሻለ የሚመስልበት ሁኔታ ውስጥ ልትገባ ትችላለህ ግን ሁሉንም እርግፍ አርጎ መተው ቀላል ነው፤ ሀይል ሰብስቦ መቀጠል ነው ከባዱ!

ወዳጄ ለራስህ የምትሆነው ከዛ ለምትወዳቸው የምትደርሰው ተስፋ ሳትቆርጥ ከቀጠልክ ብቻ ነው። ለዛ ነው መበርታት ያለብህ፤ ዳይ ያቆምከውን ቀጥል አሁኑኑ!

ተስፋ የሞላው ህይወት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
22.3K viewsSinework Taye, 17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 09:12:38 አቋም

አቋም የሌለው ሰው በንፋስ አቅጣጫ ይመራል በዚህ ሲሉት በዚያ ሁሌም በተመራበት ነው የራሱ የሆነ የእኔ የሚለው መንገድ አይኖረውም የራሱ የሆነም ህይወት አይኖርም የሌሎችን ህይወት እየኖረ የሌሎችን ህልም እያሳካ እኔ የኔ የሚለው ነገር ሳይኖረው ማንነቱ ሳይታወቅ ያልፋል ፤ ሁሌም ቢሆን የኔ የምንለው የምንመራበት ህግ እና አቋም ልንገነባ ይገባናል ያኔ የኔ ያልነውን የተመኘነውን ውብ ህይወት ለማጣጣም እድል ይኖረናል!

ደስ የሚል ሀሙስ ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
29.6K viewsDaniel W., 06:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:17:33 በጠዋት ተነስ!

"ሺ አመት አይኖር ለምን ረፈድ አርጌ እንቅልፌን አልተኛም" ብሎ ውስጥህ ሊነግርህ ይችላል። እንዲህ በለው ሰበበኛውን ድምፅ "ልክ ነህ ህይወት ስታበቃ ማንም አይከለክልህም ሺ አመት ትተኛለህ፤ አሁን የምትኖረው እድሜ ግን የተገደበ ነው ስለዚህ በጠዋት ተነስ!!"

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
15.3K viewsSinework Taye, 18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 08:27:21 እኔ ምን ማድረግ እችላለው?

በህይወት ለሚፈጠሩብን ጥያቄዎች ሆነ ችግሮች ሁሌም ልንጠይቀው የሚገባን ጥያቄ እኔ ምን ማድረግ እችላለው የሚል መሆን አለበት ፤ ለማደግ : ችግሮቼን ለማሸነፍ : ካለውበት ለመውጣት : ለማሳካት ሌላውን ሳልጠብቅ እኔ እንዴት ማድረግ እችላለው ስንል እኛ ያለንን ሙሉ አቅም በሚገባ እናወጣዋለን ሁሉም ነገር ከእኛ አቅም ሲያልፍ ነው አጋዥ የሚያስፈልነው!

ደስ የሚል ቀን ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
884 viewsDaniel W., 05:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:53:57 አንተ ነህ!

የሆነ ሰው ደፍሮ እስኪያደርገው ድረስ ያ ነገር አይቻልም ነበር፤ ያ ሰው አንተ ነህ! ያመንክበትን አድርግ!

ውብ ምሽት ተመኘን
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
16.9K viewsSinework Taye, 16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 08:08:13 እቅድ

እቅዶቻችን ለስንፍናችን መጠለያ ሊሆኑ አይገባም ፤ አዲስ ዓመት ላይ አደርገዋለው ሰኞ ሲመጣ እጀምራለው ምቹ ቀን ሲመቻችልኝ ይሆናል ወሩ ሲያልቅ እያልን ልናዘገያቸው አይገባም ፤ ሀሳብ እኛ ጋር ከቆየ እና ካልሰራንበት ወደሚሰሩበት መሻገሩ አይቀርም ስለዚህ እናስተውል የምናቅደው የእውነት ለማድረግ ነው ወይስ እፎይታ ጎዜ ለማግኘት ነው?

የስኬት ቀን ተመኘን
@Inspire_ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
26.2K viewsDaniel W., 05:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ