Get Mystery Box with random crypto!

ሁሌም በመልካም መልስ! አሸናፊ ሰው የሰዎችን ከባድ ስሜት መቆጣጠር የሚችል ነው ! ሰዎች በህይወ | Inspire Ethiopia

ሁሌም በመልካም መልስ!

አሸናፊ ሰው የሰዎችን ከባድ ስሜት መቆጣጠር የሚችል ነው ! ሰዎች በህይወት አጋጣሚ ብዙ ነገሮችን ሊያሳልፋ ይችላሉ ይከፋሉ፣ ይናደዳሉ፣ ይጨነቃሉ ከዛም በምንሰራበት ቦታ ወይ ደግሞ ያለንበት አካባቢ በዚያ ስሜት ውስጥ ሆነው ይገኙ እና የሚያስቀይም ንግግርን ሊናገሩን ይችላሉ ያኔ ታድያ እኛም ከእነርሱ በላይ የሚያስቀይም ንግግርን ከአንደበታችን ካወጣን ሊፈጠር የሚችለውን የማያልቅ ጭቅጭቅ እና አለመግባባት በዛ ላይ እርስ በራስ ከሚፈጠርብን ጥላቻ ባለፈ የዛን የተረበሸ ሰው ስሜት የባሰ መጉዳት ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍልስ እናስበዋለን? ሁሌም ባለን እና በተቻለን አቅም ሁሉ ለሰዎች መልካም እንሁን ከልባችን እናግዛቸው ምንም አይነት ምላሽ ይስጡን ጥሩነታችንን እናጋራቸው ያኔ እነርሱ በነበራቸው መጥፎ ስሜት ያፍሩበታል መልካምነታችን ይጋባባቸዋል አሸነፍን ማለት ይሄ አይደለ!

ደስ የሚል ረቡዕ ተመኘን
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ