Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹ኢትዮ University

የሰርጥ አድራሻ: @ethiouniversity1
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 126.79K
የሰርጥ መግለጫ

Promotion ለምትፈልጉ ....🌀 @Euads🌀
@hilwauniversity
Use this for idea and question @ethiouniversity1bot

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2024-04-21 13:18:52
#Update

ዲላ ዩኒቨርስቲም የምግብ በጀት እጥረት እንደገጠመው ገልጿል

እንደ ሀገር ባጋጠመን የምግብ በጀት እጥረትና የምግብ ጥሬ ዕቃ ዋጋ በየቀኑ ከመጨመር ጋር በተያያዘ የተማሪዎች የምግብ በጀታቸው ሙሉ በሙሉ ካለቀ ወራት ያስቆጠረ ሲሆን ተቋሙ በሚያደርገው ድጎማ ተማሪዎቻችን ትምሀርታቸውን አቋርጠው እንዳይወጡ በተወሰነ ስቶራችን ውስጥ ባሉን የምግብ ጥሬ ዕቃዎች እና በአትክልት የምግብ አገልግሎት እየሰጠን እንደምንገኝ የሚታወቅ በመሆኑ በአስቸኳይ የምግብ ጥሬ ዕቃ ግዥ አቅርቦ እንዲሟላልን የጠየቅን ስለሆነ በቀጣይ የአቅርቦት ሁኔታ እስከሚስተካከል #በትዕግስት እንድትጠባበቁ ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡


ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
13.6K viewsedited  10:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-21 09:05:19
ይኼ ከወላይታ ዩኒቨርስቲ የተማሪ መመገቢያ አዳራሾች አንዱ ላይ የተለጠፈ ማስታወቂያ ነው።

"ዩኒቨርስቲው በጀት ስለጨረሰ የተሰጣችሁን ብሉ" ነው አንድምታው። ወላጅ/አሳዳጊ ልጁን ወደ ዩኒቨርስቲ ሲልክ መንግስትን አምኖ ነው። "ልጄ ቀለም ይቆጥርልኛል" ከሚለው ባሻገር "ቤት እንዳለውም ባይሆን ቢያንስ ልጄ አይራብም፣ ደህንነቱ ይጠበቃል" የሚል ያልተፃፈ የጋራ ውሉን ተማምኖ የአብራኩን ክፋይ ስስቱን ወደ ትምህርት ተቋማት ይሰዳል።

መንግስት ለነዚህ የትምህርት ተቋማት በጀት መድቦ አደራውን ለመወጣት እንደሚሞክር ቢጠበቅም፤ ለምግብ የተሰጠኝ ገንዘብ ከወራት በፊት አልቋል የሚል ዜና ያውም ለተማሪዎቹ ምጣኔ እና ኃብት አስተዳደርን ከሚያስተምር ተቋም ሲነገር ያስደነግጣል... ያሳፍራል... አይደለም ወላጅን ማንኛውንም ሰው ጭንቀት ላይ ይጥላል።


እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ እንጠይቃለን:

1. ለአመት የተበጀተ በጀት በምግብ ዋጋ ንረት ግማሽ ላይ የሚያልቀው ምግቡን የሚገዙት ከዚምባቡዌ እና ቬንዙዌላ ነው ወይ? በጀቱ ሲበጀት ይህን የገበያ ለውጥ ታሳቢ ማድረግ ለምን አልተቻለም?

2. ትምህርት እንዳይቋረጥ ባለው ጥሬ ዕቃ አገልግሎት እየሰጠሁ ነው ያለው ዩኒቨርስቲው የጠቀሳቸው ጥሬ ዕቃዎች መቼ የገቡ፣ በምን አይነት የንፅህና ይዞታ ላይ ያሉ፣ ምን ያህል ጊዜ የሚያቆዩ ናቸው?

3. በህክምና ምክንያት የተለየ ምግብ መብላት ያለባቸውን ተማሪዎችስ እንዴት ለማስተናገድ ታስቧል?

3. ወትሮም ሆድ ጠብ የማይለው ምግብ መጠን እና ጥራቱ ሲያንስ የተማሪዎች ጤና እና ንቃት የሚያሳርፈውን ጉዳት እንዴት ሊያካክሱት አሰቡ? የልጆቹ የትምህርት አቀባበል ላይ ተፅዕኖ አይኖረውም?

Surafel Dereje
ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
@ethiouniversity1
14.8K views06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-21 07:24:35
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሶሻል ወርክ ትምህርትን በሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራም መስጠት ሊጀምር ነው።

የዩኒቨርሲቲው ሶሻል ወርክ ትምህርት ክፍል ፕሮግራሙን ለመክፈት በሀገር አቀፍ ደረጃ የፍላጎት የዳሰሳ ጥናት ማካሔዱ ተገልጿል።

ፕሮግራሙን ለማስጀመር አዲስ ስርዓተ ትምህርት በማዘጋጀት በባለሙያዎች ሲያስገምግም ቆይቷል።

በዚህም የተሰጡትን ማስተካከያዎች በማካተት የማረጋገጫ አውደ ጥናት አካሒዷል፡፡

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
13.6K views04:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 20:25:32
#Update

የመውጫ ፈተና አገልግሎት ክፍያ

ከኢ...ዲ.ሪ.ት/ሚ/ር በቁጥር 8/342/562/16 በቀን 09/08/2016 ዓ.ም በተፃፈው ደብዳቤ መሰረት ከሰኔ 14-212016 ዓ.ም ድረስ ለሚስጠው የመውጫ ፈተና አገልግሎት ክፍያን አስመልከቶ ተፈታኝ ተማሪዎች #እያንዳንዳቸው 500.00 /አመስት መቶ ብር/ እስከ ሚያዝያ 15/2016 ዓ.ም ድረስ እንዲከፍሉ አሳውቋል።

በዚሁ መሰረት በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገኙ የዘንድሮ አመት ተመራቂ ተማሪዎች ክፍያውን ይከፍሉ ዘንድ ዩንቨርሲቲዎች እያሳሰቡ ይገኛል።

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
14.0K views17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 14:12:24
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎቹ የእውቅናና ማበረታቻ ፕሮግራም ሚያዚያ 10/2016 አዘጋጅቷል::

የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ዙፋን በደዊ በፕሮግራሙ ላይ ባደረጉት ንግግር ዝግጅቱ ተማሪዎች በፉክክር መንፈስ እንዲሠሩና የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ለማበረታታት እንደሆነ ገልፀዋል።

ተሸላሚ ተማሪዎች በኮሌጁ ስር ከሚገኙ 10 የትምህርት ክፍሎች ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ዓመት  ያሉና ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ውጤት ያስመዘገቡ መሆናቸው ታውቋል።

በኮሌጁ የጥራት ቁጥጥር አስተባባሪ ዶ/ር መቅደስ ማሞ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ዩኒቨርስቲው ከምንጊዜውም በላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ እንደመሆኑ ዓላማውን ከግብ ለማድረስ ተማሪዎች የበኩላቸውን አስተዋጾኦ ሊወጡ እንደሚገባ ጠቁመዋል። ለዚህም በየመንፈቅ ዓመቱ ተመሳሳይ ኘሮግራሞችን በማዘጋጀት የማነቃቅያ ስራዎች  እንደሚካሄዱ ገልጸዋል።

በማጠቃለያም የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ሴት ተማሪዎች በልዩነት የማበረታቻ ሽልማት የተሰጠ ሲሆን የጋራ ፎቶግራፍ በመነሳት ኘሮግራሙ ተጠናቋል።

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
                
13.8K views11:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 19:10:57
ባለ ዘርፈ ብዙ ባለሙያ የJimma University ተመራቂ ተማሪ።

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሚያዝያ 05/2016 ዓ.ም ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል ባለ ዘርፈ ብዙ ባለሙያው ተመራቂ
ዶ/ር በዛብህ ብርሃኑ ይገኝበታል ።

ከመደበኛ ትምህርቱ ጎን ለጎንም ስነ-ፅሁፍ የሚወደው ተማሪው መፅሐፍትን ማሳተምና የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ በመፃፍ በሃገር አቀፍ ደረጃ ትልቅ እውቅና አግኝቷል።

ምንም እንኳን የሜዲካል ትምህርት በባህሪው ጊዜ የሚፈልግ ቢሆንም በቅርቡ የሚያሳትመውን ጨምሮ አራት መፅሐፍትን ሲፅፍና ከ6 በላይ ሲትኮም ድርሰቶችን ሲከትብ በትምህርቱ ላይ ተፅዕኖ እንዳልፈጠረበት ተመራቂው ይናገራል።

በጥርስ ህክምና የዶክተሬት ተመራቂው በዛብህ ብርሃኑ በሀገራችን በተለያዩ ቴሌቪዥን የሚተላለፉ ተከታታይ ድራማዎች ላይ በደራሲነት ተሳትፏል ፣ በርካታ ሲትኮሞችንም በመፃፍ Mr. sitcom የሚል ስም አግኝቷል።

በደራሲነት ከተሳተፈባቸው ስራዎች መካከል ዘጠነኛው ሺ ከ35 ክፍል በላይ ፤ መስሪያ ቤት ፣ ሳሎኑ ፣ ዶክተሮቹ ፣ ፊሽካዎቹና አንድ ላይ የተሰኙ ድራማዎች ላይ በደራሲነትና በዳይሬክተርነት ተሳትፏል። በርካታ የቴሌቪዥን እና የራዲዮ ማስታወቂያ አዘጋጅቷል።

ደራሲ ዶ/ር በዛብህ ብርሃኑ የአፍ ጤና አጠባበቅ ለልጆች እና ለወላጆች የሚል መማሪያ መፅሐፍ አዘጋጅቶ ያጠናቀቀ ሲሆን መፅሃፉ በቅርቡ ለህትመት እንደሚበቃ ተናግሯል።

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════
13.4K views16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 19:07:43
#ለዩኒቨርሲቲ_ተማሪዎች

ከዓመታት በፍት ዩኒቨርሲቲዎች የፍሬሽማን ኮርስ መስጠት ሲጀምሩ አብሮ የተመሰረተ፣ ፈር ቀዳጅ ማዕከል ነው። ለዓመታት ስኬታማ ጉዞ አድርጓል፣ በርካታ ተማሪዎች የልጅነታቸውን ህልም እውን እንድያደርጉ እገዛ በማድረግ የራሱን አሻራ አስቀምጧል።

ወደ ማዕከሉ የተቀላቀሉ ተማሪዎችን 97% ከመቶ በማሳለፍ እንድሁም ከፍተኛ ውጤት እንዲያመጡ በማድረግ ተወዳጅነት እና ተመራጭነትን አትርፏል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን በመጀመሪያው ሴስምተር ተቀብሎ የከፍተኛ ውጤት ባለቤት እንድሆኑና የሚፈልጉትን ዲፓርትመንት እንድገቡ የአንበሳውን ድርሻ ተወጥቷል።

አጭር ፣ ግልጽ እና ለመረዳት ቀላል የሆኑ ቲቶርያል ቪድዎችን ፣ ለ4 ተከታታይ ዓመታት የወጡ የፍሬሽማን ጥያቄዎችን ከነሙሉ ማብራሪያዎቻቸው ጋር አቅርቦላችኋል።

የሁለተኛ ሴምስተር ኮርሶችን በተሻለ ጥራት ለመስጠት ሙሉ ዝግጅት ጨርሶ እነሆ ይላችኋል።

ለምዝገባ
@havanacademy_bot

ምስክርነት
https://t.me/havanacademyinfo/44

share and join
@havanacademy

Customer Support Center:
Call, SMS, for 24 hr/7 days.

+251973194557
+25192928 4321

For more
On YouTube:
Website: www.havanacademy.com
TikTok:
12.8K views16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 20:19:33
#Dilla

በዛሬው ዕለት በጌዲዮ ዞን እና አካባቢው በጣለው ከባድ ዝናብ በሰው እና ንብረት ላይ ውድመት አድርሷል። በዲላ ዩኒቨርስቲ  እስካሁን በሰው ላይ ይህ ነው የተባለ ጉዳት አልደረሰም።

ሆኖም የግቢው ያሉ ዕፀዋት በፎቶ በምትመለከቱ ጉዳት ደርሶባቸዋል። አሁን ላይ ሙሉ ለሙሉ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጧል።

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
15.8K viewsedited  17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 19:03:36
ሦስት ዋንጫና ሁለት የወርቅ ሜዳልያ የግሏ ያደረገችው የማዕረግ ተመራቂ

የኋላሸት ታለው ትባላለች።  በዛሬው ዕለት የዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ካስመረቃቸው ተማሪዎች አንዷ ናት።ከፔዲያትሪክ ነርሲንግ ትምህርት ክፍል 4.00 አጠቃላይ ውጤት በማስመዝገብ ተመርቃለች።

ዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያዩ የጤና መስኮች በጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 300 ተማሪዎች አስመርቋል።

አዲስ አበባ ተወልዳ ያደገችው የኋላሸት፣ ከልጅነቷ ጀምሮ ለትምህርት ልዩ ፍቅር እንደነበራት ትናገራለች። ከዓመታት በፊት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ወስዳለች የጠበቀችውን ውጤት ባለማስመዝገቧ ኮሌጅ ገብታ ነርሲንግ በዲፕሎማ ተመርቃለች።

ህልሟ ሩቅ የሆነው የኋላሸት ዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ገብታ በእጅግ ከፍተኛ ማዕረግ ለመመረቅ በቅታለች።ባስመዘገበችው ውጤትም ሦስት ዋንጫዎችና ሁለት የወርቅ ሜዳልያዎችን የግሏ ማድረግ ችላለች።

ያስመዘገበችው ውጤት ለዓመታት የደከመችበት በመሆኑ መደሰቷን ጠቅሳ፤ በሙያዋ ሀገሯን በቅንነት ለማገልገል ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች።

ፍላጎት ጥረት ከታክለበት የማይሳካ ነገር የለም የምትለው ተመራቂዋ፤ በተለይ ሴቶች ለሚያጋጥማቸው ፈተና ሳይበገሩ ለስኬት መብቃት እንደሚችሉ መልእክቷን አስተላልፋለች።

(ኢ ፕ ድ)
ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
14.4K views16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-10 19:17:50
#MoE

የአገር ውስጥ የምርምር ጆርናል አርታኢዎች እና አሳታሚዎች ለ Plagiarism ችግር ልዩ ትኩረት በመስጠትና ቅድመ ፍተሻ በማድረግ የምርምር ጆርናል ጥራትን እንዲያስጠብቁ ትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ።

በርካታ በአገር ውስጥ የሚታተሙ የምርምር ጆርናሎች ፅሁፎች (Manuscripts) የPlagiarism መጠናቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ከሚሰጠው ነጥብ በላይ መሆኑን በዚህ ዓመት ባደረገው የፍተሻ ሥራ ማረጋገጡን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በመሆኑም ከመጋቢት 30/2016 ዓ.ም. ጀምሮ የPlagiarism መጠኑ ከ 30% በላይ የሆነ የምርምር ጆርናል ለፍተሻ ብቁ የማይሆንና ዕውቅና የማይሰጠው መሆኑ ተገልጿል።

ለዚህም ሚኒስቴሩ የተሻሻለ መመሪያ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መላኩ ታውቋል።

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
13.6K views16:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ