Get Mystery Box with random crypto!

ሦስት ዋንጫና ሁለት የወርቅ ሜዳልያ የግሏ ያደረገችው የማዕረግ ተመራቂ የኋላሸት ታለው ትባላለች። | 🇪🇹ኢትዮ University

ሦስት ዋንጫና ሁለት የወርቅ ሜዳልያ የግሏ ያደረገችው የማዕረግ ተመራቂ

የኋላሸት ታለው ትባላለች።  በዛሬው ዕለት የዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ካስመረቃቸው ተማሪዎች አንዷ ናት።ከፔዲያትሪክ ነርሲንግ ትምህርት ክፍል 4.00 አጠቃላይ ውጤት በማስመዝገብ ተመርቃለች።

ዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያዩ የጤና መስኮች በጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 300 ተማሪዎች አስመርቋል።

አዲስ አበባ ተወልዳ ያደገችው የኋላሸት፣ ከልጅነቷ ጀምሮ ለትምህርት ልዩ ፍቅር እንደነበራት ትናገራለች። ከዓመታት በፊት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ወስዳለች የጠበቀችውን ውጤት ባለማስመዝገቧ ኮሌጅ ገብታ ነርሲንግ በዲፕሎማ ተመርቃለች።

ህልሟ ሩቅ የሆነው የኋላሸት ዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ገብታ በእጅግ ከፍተኛ ማዕረግ ለመመረቅ በቅታለች።ባስመዘገበችው ውጤትም ሦስት ዋንጫዎችና ሁለት የወርቅ ሜዳልያዎችን የግሏ ማድረግ ችላለች።

ያስመዘገበችው ውጤት ለዓመታት የደከመችበት በመሆኑ መደሰቷን ጠቅሳ፤ በሙያዋ ሀገሯን በቅንነት ለማገልገል ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች።

ፍላጎት ጥረት ከታክለበት የማይሳካ ነገር የለም የምትለው ተመራቂዋ፤ በተለይ ሴቶች ለሚያጋጥማቸው ፈተና ሳይበገሩ ለስኬት መብቃት እንደሚችሉ መልእክቷን አስተላልፋለች።

(ኢ ፕ ድ)
ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝