Get Mystery Box with random crypto!

31 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በማላዊ ታግተው ለማስለቀቂያ ከቤተሰቦቻቸው 1ሺ ዶላር መጠየቃቸው ተጠቆ | 🇪🇹ኢትዮ University

31 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በማላዊ ታግተው ለማስለቀቂያ ከቤተሰቦቻቸው 1ሺ ዶላር መጠየቃቸው ተጠቆመ

የማላዊ ባለስልጣናት በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገሪቱ የገቡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በህገወጥ አዘዋዋሪዎች ታግተው ለማስለቀቂያ በነፍስ ወከፍ 1ሺ ዶላር እየተጠየቀባቸው እንደነበር አረጋግጫለሁ ማለቱን ኒያሳ ታይምስ የተሰኘው የሀገሪቱ የዜና ምንጭ ዘግቧል።

የሀገሪቱ የደህንነት ባለስልጣን ኬን ዚክሃሌ ንጎማ በሊሎንግዌ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አህመድ ሙሀመድ እና ዲሞራህ የተባሉ ኢትዮጵያውያን ጥንዶች 31 ኢትዮጵያውያን አግተው ኢትዮጵያ ካሉ ቤተሰቦቻቸው ለማስለቀቂያ 1ሺ ዶላር እየጠየቁ እንደነበር መረጋገጡን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ወደ ማላዊ ለመግባት 200 ዶላር እንደሚከፍሉ ባለስልጣኑ የገለፁ ሲሆን ህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎቹ ጥንዶች ለረዥም ጊዜ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ንግድ ተሰማርተው እንደቆዩ አብራርተዋል። ይህ ድርጊታቸው ከታወቀ በኋላ ከሀገሪቱ እንዲባረሩ ሲደረግ ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ስላሉበት ሁኔታ የተጠቀሰ ነገር የለም።

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝