Get Mystery Box with random crypto!

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎቹ | 🇪🇹ኢትዮ University

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎቹ የእውቅናና ማበረታቻ ፕሮግራም ሚያዚያ 10/2016 አዘጋጅቷል::

የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ዙፋን በደዊ በፕሮግራሙ ላይ ባደረጉት ንግግር ዝግጅቱ ተማሪዎች በፉክክር መንፈስ እንዲሠሩና የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ለማበረታታት እንደሆነ ገልፀዋል።

ተሸላሚ ተማሪዎች በኮሌጁ ስር ከሚገኙ 10 የትምህርት ክፍሎች ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ዓመት  ያሉና ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ውጤት ያስመዘገቡ መሆናቸው ታውቋል።

በኮሌጁ የጥራት ቁጥጥር አስተባባሪ ዶ/ር መቅደስ ማሞ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ዩኒቨርስቲው ከምንጊዜውም በላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ እንደመሆኑ ዓላማውን ከግብ ለማድረስ ተማሪዎች የበኩላቸውን አስተዋጾኦ ሊወጡ እንደሚገባ ጠቁመዋል። ለዚህም በየመንፈቅ ዓመቱ ተመሳሳይ ኘሮግራሞችን በማዘጋጀት የማነቃቅያ ስራዎች  እንደሚካሄዱ ገልጸዋል።

በማጠቃለያም የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ሴት ተማሪዎች በልዩነት የማበረታቻ ሽልማት የተሰጠ ሲሆን የጋራ ፎቶግራፍ በመነሳት ኘሮግራሙ ተጠናቋል።

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝