Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹ኢትዮ University

የሰርጥ አድራሻ: @ethiouniversity1
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 126.79K
የሰርጥ መግለጫ

Promotion ለምትፈልጉ ....🌀 @Euads🌀
@hilwauniversity
Use this for idea and question @ethiouniversity1bot

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2024-04-09 19:01:35
የመውጫ ፈተና መቼ ይሰጣል?

የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ የቅድመ ምረቃ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች መረጃ ማሰባሰብ ሥራ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየተከናወነ ይገኛል።

ተቋማቱ ለፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎች የተሟላ መረጃ እስከ ሚያዚያ 5/2016 ዓ.ም ድረስ በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በኩል ተረጋግጦ እንዲላክ ትምህርት ሚኒስቴር ማሳሰቡ ተሰምቷል።

የመውጫ ፈተናው በሰኔ ወር አጋማሽ እንደሚሰጥ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
17.2K views16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 21:21:28
#MoE

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችን የራስ ገዝ ሽግግር የሚያሳልጡ ፍኖተ ካርታ እና መመሪያ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ።

የዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ መሆን ተቋማቱ በአስተዳደራዊ፣ አካዳሚያዊ እንዲሁም በሰው ሃብትና ፋይናንስ አስተዳደር ጉዳዮች ነፃነትን ከተጠያቂነት ጋር የሚያገኙበት የአሰራር ስርዓት እንደሆነ በሚኒስቴሩ የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።

የዩኒቨርሲቲዎችን የራስ ገዝ ሽግግር ለማሳለጥ የሚያስችሉ የፍኖተ ካርታ እና የመመሪያ ዝግጅት በቅርቡ ተጠናቀው ወደ ሥራ እንደሚገቡ ጠቁመዋል።

ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ እየተሠራ ሲሆን ተቋማቱ ከአደረጃጀት ጀምሮ ለሽግግሩ የሚያግዟቸውን ተግባራት እያከናወኑ እንደሆነ ኃላፊው አስረድተዋል።

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ ራስ ገዝ ለመሆን የሰው ኃይል፣ ሃብት የማመንጨት አቅም፣ የመሰረተ ልማትና የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓታቸው እንዲሁም ዓለም አቀፍ ትስስራቸው እንደሚታይ ገልፀዋል። #ENA

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
18.3K views18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 19:24:12
#AAEB

የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ መካከለኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ሰኔ 4 እና 5/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

በተመሳሳይ የ6ኛ ክፍል የአንደኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 12 እስከ 14/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ፈተናዎቹ በተጠቀሱት ቀናት በጠዋት እና ከሰዓት መረሐግብር እንደሚሰጡ ቢሮው ያወጣው የድርጊት ጊዜ ሰሌዳ ያሳያል።

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
16.9K views16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 18:15:30
የዒድ አል ፊጥር በዓል #እሮብ ይከበራል ።

ዛሬ ጨረቃ ባለመታየቷ ነገ ረመዷን 30 ሆኖ ዒድ አል ፊጥር በዓል ደግሞ
#እሮብ ሚያዝያ 2 እንደሚከበር ይፋ ተደርጓል ።

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ ከወዲሁ እንኳን ለ1445ኛ የዒድ አል ፊጥር በዓል በሰላም አደረሳቹ ለማለት እንወዳለን ። ኢድ ሙባረክ

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
15.5K viewsedited  15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 12:02:50
#BahirdarUniversity

ለኦርጅናል ዲግሪ ህትመት ፈላጊዎች በሙሉ

በውል መጠናቀቅ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የኦርጅናል ህትመት አዲስ ውል የያዝን በመሆኑ የአገልግሎቱ ፈላጊወች ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
18.1K views09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 09:54:29 ለ 1ኛ አመት ተማሪዎች በ 2ኛ ሴሚስተር ቲቶሪያል የምንሰጣቸው ኮርሶች

የ ሁለተኛ ሴሚስቴር ምዝገባ ተጀምሯል።

የ 2ኛ ሴሚስተር #Common_Course ትቶሪያላችን መማር ለምትፈልጉ ምዝገባው ተጀምሯል።

ሁለተኛ ሴሚስተር 
Economics,
Emerging Technology,
Communictive English 2,
anthropology,
Civics,
Global,
C++ እና 
Applied Maths 1,

በነዚህ Coursoች ላይ ትቶሪያሎች እየተዘጋጁ ስለሆነ መማር የምትፈልጉ መመዝገብ ትችላላችሁ።

የክፍያ ሁኔታ
  3ት ኮርስ መርጠው ለሚማሩ 100 ብር ብቻ
  4ት ኮርስ እና ከዛ በላይ 150 ብር ብቻ ከፍላችሁ መማር ነው።

ለመመዝገብ @Ethiounads ላይ ከፍላችሁ መቀላቀል ነው።

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
15.8K views06:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 08:34:03
በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ሰርቪስ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 12 ሰዎች ቆስለዋል።

በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ሰርቪስ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 12 ሰዎች መቁሰላቸውን ፋስት መረጃ ከዩኒቨርሲቲው ሰምቷል። በሳምንቱ መጨረሻ መርሃ ግብር አይራ ካምፓስ አስተምረው ሲመለሱ ሁለት መምህራኖች እና አንድ ሹፌር በመኪና አደጋ ህይወታቸው አልፏል።

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
16.1K views05:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-07 19:19:56
አንድ የታሪክ ተመራማሪ በመቅደላ ጦርነት የተሰረቁት የአፄ ቴዎድሮስ አልባሳት የት እንዳሉ ለማወቅ እየጣሩ ነው ተባለ

በእንግሊዝ አንድ የታሪክ ተመራማሪ ከ156 ዓመታት በፊት የተሰረቁት የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ አልባሳት የት እንዳሉ ለማወቅ እየጣሩ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ በእንግሊዝ ወረራ ወቅት እጅ አልሰጥም ብለው መቅደላ ላይ የራሳቸውን ሽጉጥ ጠጥተው ከሞቱ በኋላ ለብሰውት የነበረው የክብር ካባ እና የአንገት ልብስ ከአስክሬናቸው ላይ ተገፍፎ ተወስዷል።

አልባሳቱ ወደ እንግሊዝ ከተወሰዱ በኋላም በስታሊይብሪጅ፣ ስታምፎርድ ፓርክ ሙዚየም ውስጥ ተቀምጠው እንደነበር ሲገለፅ ሙዚየሙ በ1950ዎቹ ከፈረሰ በኋላ ግን እነዚህ ጥንታዊ ቅርሶች የት እንዳሉ አይታወቅም ተብሏል።

በጉዳዩ ላይ መጽሐፍ የጻፉት ሔቨንስ የተባሉት የታሪክ ተመራማሪ እንደሚሉት በመቅደላ ጦርነት ወቅት የተወሰዱ ቅርሶች ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በአገሪቷ ውስጥ ይገኛሉ። ከሐር የተሠራው የንጉሡ ትንሽ የአንገት ልብስም ስታሊይብሪጅ ውስጥ በሚገኘው ሰታምፎርድ ፓርክ ሙዚየም ውስጥ ተቀምጦ ነበር።

ሙዚየሙ በ1950ዎቹ ከፈረሰ በኋላ የንጉሡ የአንገት ልብስ ወይም የካባው ክፍል በሆነ ሰው ቤት ውስጥ እንደሚገኝ ሔቨንስ እምነት እንዳላቸው እና የተረፉት ሌሎች ቅርሶችም ወደ ሌሎች የአካባቢው ሙዚየሞች መሰራጨታቸውን ገልፀዋል።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የታሪክ ምሁሩ ለታሜሳይድ የአካባቢ ጥናት ተቋም፣ ለመዘክሮች እና ለማንቸስተር ሙዚየም ጥያቄ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
17.7K views16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-07 14:32:28 የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አሰጣጥ

"ግልጽ የሆነ መመርያ እስከሚወጣ ድረስ የክብር ዶክትሬት እንዳይሰጥ ተከልክሏል።"
- የትምህርት ሚኒስትሩ

የተበታተነ አሠራርን ለመቅረፍ ግልጽ የሆነ መመርያ እስኪወጣ ድረስ ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክትሬት የሚባል ነገር መስጠት እንዲያቆሙ እንደተነገራቸው የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለፁ፡፡

ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት ‹‹የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ "የዶክትሬት ዲግሪና የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሽልማት በኢትዮጵያ" በሚል ጭብት ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተካሔደ ምሁራዊ ውይይት ወቅት ነው።

በኢትዮጵያ የክብር ዶክትሬት ሲሰጥ በተበታተነ ሁኔታ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች መስጠት እንዲያቆሙ ውሳኔ መተላለፉን ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አሰጣጥን በተመለከተ መመርያ እያዘጋጀ መሆኑንና መመርያውንም በዚህ ዓመት አጠናቆ ለመጨረስ ሒደት ላይ እንደሆነ ሚኒስትሩ አክለዋል፡፡

በኢትዮጵያ እስካሁን 79 ሰዎች የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እንደተሰጣቸው አስረድተው ከነዚህም 68 በመቶ የሚሆነው ለክልል ሰዎች የተሰጠ እንደሆነ ገልጸዋል።

በመድረኩ የመነሻ ጽሑፍ ያቀረቡት ፕ/ር ማስረሻ ፈጠነ በበኩላቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሲሰጥ አካዳሚያዊ ያልሆነ ዕውቅናን በመንተራስ እንደሆነና ተሸላሚዎችም ካላቸው ክህሎት፣ ስብዕና እንዲሁም ያበረከቱት አስተዋጽኦ ጋር በተያያዘ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አሰጣጥን የተመለከተ መመርያ እንዳላቸው አንስተዋል።

በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በርካታ ሰዎችን እያሳሰበ የመጣው ጉዳይ ዩኒቨርሲቲዎች የራሳቸው ሰው የሚሉትን ብቻ በመምረጥ የክብር ዶክትሬት እየሰጡ መሆኑ ነው ብለዋል፡፡

የክብር ዶክትሬት ዲግሪን ከዩኒቨርሲቲዎች የሚያገኙ ሰዎች ጭምር እንደመጠሪያ እንደሚጠቀሙበትና ይኼም በጣም የተሳሳተ ነገር እንደሆነ ገልጸው፣ በርካታ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችም ይኼንን ድርጊት እንደሚፈጽሙ አስታውሰዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክትሬት ዲግሪ የሰጧቸው ሰዎች ያልተገባ ድርጊት ከፈፀሙ፣ የክብር ዶክትሬት ዲግሪውን መንጠቅ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡ #ሪፖርተር

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
17.4K views11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-06 19:04:29
31 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በማላዊ ታግተው ለማስለቀቂያ ከቤተሰቦቻቸው 1ሺ ዶላር መጠየቃቸው ተጠቆመ

የማላዊ ባለስልጣናት በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገሪቱ የገቡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በህገወጥ አዘዋዋሪዎች ታግተው ለማስለቀቂያ በነፍስ ወከፍ 1ሺ ዶላር እየተጠየቀባቸው እንደነበር አረጋግጫለሁ ማለቱን ኒያሳ ታይምስ የተሰኘው የሀገሪቱ የዜና ምንጭ ዘግቧል።

የሀገሪቱ የደህንነት ባለስልጣን ኬን ዚክሃሌ ንጎማ በሊሎንግዌ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አህመድ ሙሀመድ እና ዲሞራህ የተባሉ ኢትዮጵያውያን ጥንዶች 31 ኢትዮጵያውያን አግተው ኢትዮጵያ ካሉ ቤተሰቦቻቸው ለማስለቀቂያ 1ሺ ዶላር እየጠየቁ እንደነበር መረጋገጡን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ወደ ማላዊ ለመግባት 200 ዶላር እንደሚከፍሉ ባለስልጣኑ የገለፁ ሲሆን ህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎቹ ጥንዶች ለረዥም ጊዜ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ንግድ ተሰማርተው እንደቆዩ አብራርተዋል። ይህ ድርጊታቸው ከታወቀ በኋላ ከሀገሪቱ እንዲባረሩ ሲደረግ ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ስላሉበት ሁኔታ የተጠቀሰ ነገር የለም።

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች   ቻናል
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
18.6K views16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ