Get Mystery Box with random crypto!

Ethio cyber

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiotefer — Ethio cyber E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiotefer — Ethio cyber
የሰርጥ አድራሻ: @ethiotefer
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 109
የሰርጥ መግለጫ

አላማችን በሳይንስ እና በቴክኖሎጂ የታነፀ ትውልድ መፍጠር ነው።
ሐሳብ አስተያዬት ለመስጠት👇👇👇
@Ethiospace1_bot
@unverseand 👈ለcross

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 51

2021-01-06 13:48:24
የአፅናፍ አለም ትንሹ ኮከብ እና ፕላኔት ጁፒተር

እንደሚታወቀው የኛ ጋላክሲ በሆነው ሚልክዌጋላክሲ ውስጥ ከ400 ቢልዬን በላይ ኮከቦች አሉ በዚህ ጋላክሲ ውስጥ ከተገኙ ኮከቦች መሀል "EBLM J0555-57Ab" የተባለው "red dwarf" ኮከብ ከኛ ምድር 600 የብርሃን አመት የሚርቅ ሲሆን ስፍቱ ደግሞ 180,000km ብቻ ነው ይሄም "saturn" ከተባለው ፕላኔት ጋር በስፍት ተመሳሳይ ነው።

ይሄ ኮከቡ በስበት መሬትን 300 እጥፍ የሚበልጣት ሲሆነ ይሄ ኮከብ የራሱ ፕላኔት የለውም ይልቁንም "EBLM JO555-57A" የተባለውን ኮከብ ልክ እንደ ፕላኔቶች ይዞራል ይሄ ኮከብ ከኛ ፀሐይ ጋር ተመሳሳይ ነው ኮከቡን ዙሮ ለመጨረስ ደግሞ 8 ቀን ብቻ ነው የሚፈጅበት

ይሄም ኮከብ እስከዛሬ ከተገኙ ኮከቦች ትንሹ ሲሆን "haydrogen" አተምን በጉልበቱ በማጣበቀ ወደ "helium" በመቀየር ብርሃን መፍጠር ይችላል እኛ ሶላር ሲስተም ውስጥ የሚገኙት ፀሐይ እና ጁፒተር ይሄንን ኮከብ በስፍት ይበልጡታል የጁፒተር ስፍት እንደሚታወቀው 140,000km ነው

ይሄ ማለተ ጁፒተር የተባለው ፕላኔት ይሄንን ኮከብ 22,000km ያክል በስፍት ይበልጣል

እና ለምን ጁፒተር የተባለው ፕላኔት ኮከብ አልሆነም

መልሳችን ሊሆን የሚችልው ይሄ ፕላኔት "hydrogen" አተምን በማጣበቅ ወደ "helium" በመቀየረ ብርሃንን ለመፍጠር የሚያስችል በቂ ስበት የለውም ወይም ሐይል የለውም ይሄም የሆነው በክብደቱ ምክንያት ነው "EBLMJO555-57Ab" የተባለው ኮከብ በስፍት ጁፒተር በተባለው ፕላኔት ይብለጥ እንጂ በክብደት 85 ጊዜ ጁፒተርን ያጥፈዋል በዚህ ምክንያት ከፍተኛ ስበተ ስላለው ሁለተ "hydrogen" አተሞችን በጉልበት እያጣበቀ ብርሃንን መፍጠር ይችላል

share share

@ethiotefer
2.0K viewsedited  10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-06 13:47:45 ​ኦርምኦል ቢኖር ለምን አገልግሎት ልንጠቀመው እንችላለነ? በጊዜ መጓዝን አውን ላይ ያሉ የፊዚክስ ሕጎች ይፈቅዳሉ?

ኦርምኦል በዋነኝነተ ከኛ በጣም የራቁ ቦታዎች ላይ እንድንሄድ ያስችለናል ተብሎ ይታሰባል ነገር ግን ኦርምኦል በዚህ አፅናፍ አለም ውስጥ ቢኖር ምን አልባት ወደሌላ አፅናፍአለም(universe) ባጭር ጊዜ ውስጥ ይወስደናል የሚል ግምት ሲሆን ብዙ አፅናፍ አለሞች ወይም በእንግልዘኛው "meltiverse" የሚኖሩ ከሆኑ ወደነዚህ አፅናፍ አለሞች መሄጃ ብቸኛው መንገድ ሊሆን ይችላል

ዎርምኦልን በማንኛውም ቦታ መፍጠር ከቻልን ምድር ላይ ልንጠቀመው እንችላለነ ለምሳሌ ከኢትዮጲያ ወደ አሜሪካ ፕሌን ሳንጠቀም ኦርምኦሎችን ብቻ ተጠቅመን ጉዞውን ባጭር ደቂቃ ውስጥ መጨረስ እንችላለነ

ሌላኛው ነገረ ደግሞ በጊዜ የሰው ልጆች መጓዝ የሚችሉ ከሆነ ወይም በእንግልዘኛው "time travel" የምነው ካለ አውንም ኦርምኦሎች ለዚህ አገልግሎት ሊውሉ ይችላሉ።

በጊዜ መጓዝ ማለተ ምን ማለት ነው?

በጊዜ መጓዝን አውን ላይ ያሉት የፊዚክስ ሕጎች ባይፈቅዱም በጊዜ መጓዝ ማለተ አውን ካለንበተ ወደዋላ መሄድ ወይም ወደፊት መሄድ ነው ምን አልባት ሺህ አመታትን ሊሆን ይችላል ወደፊት ወይም ወደዋላ የምንሄደው ይሄ ማለተ ትላንት የተበላሸብንን ነገረ እንደገና ወደዋላ ሂደነ ማስተካከል እንችላለን ወይም ወደፊት በመሄድ የወደፊቱን ማወቅ እንችላለነ።

በጊዜ መጓዝን በተመለከተ አንዳድ ማስረጃዎች አሉ ለምሳሌ ምንም እንኳን ዎርምኦል ባይኖርም "ታይም ማሽን" ተጠቅመው በጊዜ የሚጓዙ ሰዎች በኛ አለም ውስጥ እንዳሉ የሚያሳይ መረጃዎች አሉ ልዩ ምልክታቸው ደግሞ በጊዚያቸው በኛ አለም ውስጥ የሌሉ ልብሶችን, ጫማዎችን እንዲውም በዘመኑ ያልነበሩ ቴክኖሎጂዎችን ሲጠቀሙ መስተዋላቸው ነው

ለምሳሌ 1970 ዎቹ ስልክ ይዘውመ የሚያወሩ ሰዎች ታይተዋል እንዴት ማን ጋር ነው የሚያወሩት የሚለውን መልስ መስጠት የሚችል ሰው የለም ሌላው ደግሞ መቶ አመታትን ያስቆጠረው እጅግ የረቀቁ ቴክኖለጂዎች ተገኝተዋላ በዛ ዘመን እንዴት ኖሩ የሚለውን መልስ መስጠት የሚችል ሰው ግን አውንም አልተገኘም

ተጨማሪ በጊዜ መጓዝን እና ኦርምኦልን በተመለከተ ተጨማሪ ማወቀ ለምትፈልጉ "the flash" የተሰኘውን ፊልም ለማየት ሞክሩ

share share

@ethiotefer @ethiotefer
@ethiotefer
@ethiotefer @ethiotefer
1.6K viewsedited  10:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-03 16:58:43 ​የቀጠለ.......

ምን አይነተ ቴክኒክ ነበረ የተጠቀመው ይሄ ሳይንቲሲት?

መጀመሪያ መሬት ክብ ከሆነቸ በመሬት ወገብ አከባቢ ወይም በእንግልዘኛው "Equater" አከባቢ መሬት ከፀሐይ ጋር በቀጥታ ትይዩ ከሆነቸ ፀሐይን በቀጥታ ወደላይ እናያታለን በፀሐይቷ ምክንያት የሚፈጠረ የኛ ጥላ ደግሞ ከኛ አንፃር ዜሮ ድግሪ ነው

ይሄ ሳይንቲስት በሒሳባዊ መንገድ የመሬትን ስፍት የለካው በሁለተ በተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚወጣውን የፀሐይ ጨረረ የ"angle" ልዩነታቸውን በመፈለገ ነው ይሄንን የፈለገው ደግሞ በአውኑ ዘመን አስዋን እና አሌክዛንደር ተብለው በሚጠሩ የግብፅ ከተሞች ላይ ሲሆን በሁለቱ ቦታዎቸ ላይ ያለውን የፀሐይ ጨረረ የሚፈጥረውን ጥላ ተመርኩዞ ነው ይሄ ብቻ ሳይሆን በተመሳሳይ "longitude" ተመሳሳይ ሰሀተ እንዳለ ተርድቷል ወይም ከ"north pole" ወደ "south pole" ቀጥ ባሉት መስመሮች ላይ ተመሳሳይ ሰሀተ እንዳለ ገምቷል ለዚህም ነበረ ሁለቱን ከሞች የተጠቀማቸው

ያገኘውም የ"angle" ልዩነተ 7.2 ነበረ በመቀጠልም በሁለቱ ከተሞች መሀል ያለውን እርቀተ ለክቷል በወቅቱ ነገሮች የሚለኩት "km" ወይም በ"meter" ሳይሆነሰ "stadium" በሚባል ነገረ ነው በሁለቱ ከተሞች መሀል ያለው እርቀት 5000 stadia ነበረ ይሄንን እርቀተ ወደ ኪሎ ሜትር ስንቀይረው 787km ነው

ይሄ እርቀተ ከጎንደር እስከ አዲስ አበባ ይደርሳል ይሄንን የለካው መኪና ወይም ሌላ ነገረ ተጠቅሞ አደለም ግመሎችን ብቻ ተጠቅሞ ነው።

ይሄንን መሰዋትነተ የከፈለው ለ ገንዘብ ወይም ጥቅማጥቅም ለማግኘት አደለም ስንቁ ለማወቀ ያለው ጉጉት ብቻ ነው ወይም ለሳይንሱ ያለው ፍቅር ነው በዚህ ዘመን የምንኖር ሰዎች ለማወቅ ምን ያክል መሰዋትነተ እንከፍላለን ጥንት አባቶች ትምህርት ቤት ሳሄዱ አውቀትን የሚፈልጓት ወይም ለማወቅ የሚጥሩት በእንዲ አይነቱ መንገድ ነበር በዚህ ዘመን ግን ትምህርት ቤቶች በዝተዋል ሌሎች መንገዶቸም አሉ እኛስ እየተጠቀምናቸው ነው ወደ ትምህርት ቤት የምንሄደውስ ከምር ለማወቀ ነው ,እውቀትን ፍለጋ ነው ወይስ.... ሁላችንም እራሳችንን ልንጠይቅ ይገባል

ይሄ ሳይንቲስት የለካው ግመሎችን እየተጠቀመ ሰለነበረ የለካበተ መንግድ ጥራቱን የጠበቀ ወይም በ ሳይንሱ የሚጠበቅበትን "accuracy"ባለሟማላቱ የተነሳ በአውኑ ዘመን ከተለካው ቁጠር ጋር የተወሰነ የቁጥረ ልዩነተ እንዲፈጥር አድርጓል ሳይንቲስቱ በተመሳሳይ ሰሀተ በሁለቱ ቦታዎች ላይ ያለውን የፀሐይ ጥላ ለመለካት እጅግ የሚያስደንቅ ስራ ሰርቷል እንዲውም በእንዲ አይነተ መንገድ የመሬትን ስፍት አገኛለው ብሎ ማሰቡ በዚህ ዘመን ያሉ ሳይንቲስቶችን አስደንቋል እንዲውም ሐሳቡ እራሱ እንዴት መጣለት ብለው የሚጠይቁ ብዙዎች ናቸው

የሆነው ሁኖ ወደ ሒሳቡ ስንመጣ

በሁለቱ ከተሞች ያለውን እርቀተ "d" እንበለው በመቀጠለ ደግሞ በሁለቱ ከተሞች ያለውን የፀሐይ ጨረረ የፈጥረውን ጥላ አንግል በመቀናነስ ያገኘነውን አንግል "s" እንበለው አውን የምንፈልገውን የመሬት ዙሪያ ያለውን ስፍት ወይም "circumference" ነው አስተውሉ ይሄ 787km የመሬት "circumference" አንዱ አካል ነው ማለትም በ7.2 ድግሪ የመሬት አካል 787km ስፍት አለው እንደማለተ ነው አጠቃላይ መሬት ክብ ነች ሰለዚህ አጠቃላይ ድግሪዋ 360 ነው ሰለዚህ ለ7.2 ድግሪ 787km ከሆነ ለ360 ድግሪ ስንት ይሆናል?

የመሬት አጠቃላይ ድግሪ 360 ሲሆን "a" እንወክለው አጠቃላይ የመሬት ዙሪያ አጠቃላይ ስፍት ወይም "circumference" በ"c" እንወክለው።

given req answer

a=360° c=? if s=d
d=787km then c=a
s=7.2° s/a=d/c

c=a*d/s
ቁጥር ስንተካ

c=360*787/7.2

c=39,350km

"Circumference" ወይም መሬት ፍፁም ክብ ብትሆን መሬትን አንድ ዙር ዙሮ ለመጨረስ 39,350km መጓዝ አለብን እንደማለተ ነው።

በመቀጠል የመሬትን "radius" እንፈልግ።

circumference=2*pi*radius


Pi= 3.14

r=c/2*pi
r=39350/2*3.14

r=6,267km

ይሄንን ይመስላል ዘመናዊ የተባለው ልኬት የተደረገው ሰው ሰራሽ የሆኑ ሳተላይቶች መሬትን መዞር ከጀመሩ በዋላ ሲሆን
የመሬት "circumference" 40,070km ሲሆን "radius" ደግሞ 6,378km ነው

ያላቸውን ልዩነተ ማወዳደረ ትችላላቹ

ሌላው ነገረ መሬት ፍፁም ክብ ባለመሆኗ የተነሳ ብዙ አይንተ ልኬት አለ አቭርጄ ልኬቱ ግን ከላይ ያለውን ይመስላል

Share share

@ethiotefer @ethiotefer
@ethiotefer
@erhiotefer @ethiotefer
1.6K viewsedited  13:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-03 16:56:26 ​the radius of earth

ብዙ ጊዜ እንዴት የመሬትን "radius" ማወቅ ይቻላል ? እንዴት የመሬትን ከብደት ማወቅ ይቻላል ማን መዝኗት ነው ምን አይነተ ኪሎ ነው የመዘናት? እንዴት መሬት ግዙፍ ነገረ አደለቸ እንዴ ብለነ እንጠይቃለን ብዙ ሰዎችም ሲጠይቁ እንሰማለነ በርግጥ በቀጥተኛ መንገድ ካሰብን በርግጥም አዎ ከባድ ነገረ ነው ለምሳሌ የመሬት "radius" ማለተ ከመሬት ማሀለኛው ከፍል አንስቶ እኛ እስካለንበተ ያለው እርቀተ እንደሆነ ይታወቃል ወይም ለምሳሌ ኳስ መሬት ናት ብንል እኛ ያለነው ከላይ " ከከለመንደሪው" በላይ ነው "radius" የምንለው ደግሞ ከኳሱ ማሀለኛው ክፍል አንተስቶ እስከ እኛ ያለንበትን እርቀተ ነው ።

አዎ በርግጥም "radius" ማለተ ይሄ ከሆነ የመሬትን "radius" በቀጥታ መለካት አዳጋች ነው ይሄም የሚሆነው የመሬት መሀለኛው ክፍል ላይ መድረስ እጅግ ከባድ ነገረ ነው ምንም አይነተ የመቆፈሪያ ማሽን ቢኖረን እንኳን።

ለምሳሌ በአለም አቀፈ ደረጃ ወደተቻ ወደ መሬት የተቆፈረው 12km ብቻ ነው ነገረ ግን የመሬትሰ "radius" ደግሞ 6,378km ነው ይሄ ማለተ የመሬትን የማሀለኘው ክፍል ለማግኝተ ከ"radius" ሱ ላይ 13km ስንቀንስ 6365km ይቀራል ይሄ ማለተ ወደማለኛው የመሬት ክፍል ለመድረስ እንደገና 6365km መቆፈረ አለብን እንደ ማለተ ነው በዚህም ምክንያት ከመሬት መሀለኛው ከፍል ጀምሮ እኛ እስካለንበተ ድረስ በቀጥተኛው መንገድ መለካት አይቻልም

ይሄ ብቻ አደለም የመሬት መሀለኛው ክፍል እጅግ ሞቃታማ ከመሆኑ የተነሳ እስከ 6000 ዲግሪሴሊስሽ ይሞቃል ይሄ ሙቀተ ከፀሐይ የላይኛው ክፍል ካለው ሙቀተ ጋር ሊቀራረብ ይችላል ማነው ታዲ ከዚህ ቦታ ላይ ሁኖ እስከላኛው የመሬት ክፍል ወይም እኛ እስካለንበተ የመሬት ክፍል ያለውን እርቀትን የሚለካው?

ይሄንን ጥያቄ የሰው ልጆች ከመለሱ ግን ከ2200 አመተ በላይ ተቆጥሮል
ከክርስቶስ ልድተ 240 አመታት በፊት "archimedes" የተባለው ሳይንቲስት የአንድ ክብ ነገረ ዙሪያውን የምናገኝበተ ወይም በእንግልዘኛው "circumference" የምንለውን እንዲውም "radius" የምንላቸውን ነገረ እንዴት እንደምናገኝ ሒሳባዊ ትንታኔ ይዞ መቶ ነበረ ይሄ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ከብ ለሆኑ ነገሮች ሒሳባዊ ትንታኔ ይዞ መቶ ነበረ

በዚህው ጊዜ "Aristotle" የተባለው የግሪክ ሳይንቲስት መሬት ክብ ናት የሚለውን ሐሳብ ያራምድ ነበረ ከ"archimedes" ከ 30 አመተ በዋላ ብቅ ያለው "Eratosthenes" የተባለው ግብፃዊ ሳይንቲስት ደግሞ መሬት ክብ ከሆነች አጠቃላይ ዙሪያው ምን ያክል ነው ወይም በእንግልዘኛው፤ "circumference" የምንለውን ነገረ ለመፈለገ ጥረተ አርጎ ነበረ
ጥርት ብቻ ሳይሆን አውን ካለው ቁጥር ጋር በጣም ተቀራራቢ የሚባል ቁጥረ ለክቷል ይሄም የሆነው 276 B.C.E ላይ ነበረ

ይቀጥላል....

Share share

@ethiotefer @ethiotefer
@ethiotefer
@ethiotefer @ethiotefer
1.2K viewsedited  13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-02 18:42:12 ​ክፍል ሶስት

የዎርምኦል አፈጣጠር ምን ሊመስል ይችላል?

በ1916 አልበርት አንስታይን ብላክኦል እና ዎርምኦል የሚባል ነገረ በዚህ አፅናፍ አለም ውስጥ ሊኖሩ ይችላሉ ባለበት ቅርብ አመታት ውስጥ ሌላኝው ሳይንቲስት "ludwing flamm" የተባለው ደግሞ "white hole" ወይም ነጫጮቹ ኮከቦች እንዳሉ እና የብላክኦል ተቃራኒ ናቸው ሲል ሒሳባዊ ትንታኔዎችን ይዞ መቶ ነበር

ምንድነው የሚያቃርናቸው? ለምሳሌ ብላክኦሎች ማንኛውንም ነገረ ውጠው ያስቀራሉ ሌላው ነገረ ደግሞ ምንም ነገረ ከውስጣቸው መውጣት አይችልም በተቃራኒው "white hole" የምንላቸው ነገሮች ውስጥ ደግሞ ምንም ነገረ መግባት አይችልም ነገረ ግን ማንኛውም ነገረ መውጣት ይችላል ለምሳሌ ብርሃን መውጣት ይችላል በዚህም ምክንያት "white hole" ደምቀው ይታያሉ

እንደ "ludwing flamm" እሳቤ ከሆነ ዎርምኦል ጫፉ ላይ በአንድ በኩል ብላክኦል ሲገኝ በተቃራኒ በኩል ደግሞ white hole" ይኖራል ወይም እንዚህን ቁሶች የሚያገናኝ እስፔስታይም አለ ልክ እንደ ቱቦ እንደሱ አጠራል "space time coduit" ብሎታል ይሄም ነገረ ሁለቱን ነገሮች አስተሳሰሮቸዋል የሚል ሐሳብ ነው በወቅቱ ያቀረበው

የሆነው ሁኖ ዎርምኦል በተፈጥሮ ይገኛል ቢባልም እስካውን አልተገኙም ነገረ ግን እንደ አንዳድ ሳይንቲስቶች ግምት ዎርምኦሎች ያላገኘናቸው እጅግ በጣም ትንሽዬ የሆኑ ነገሮች ሰለሆነ ነው ይሄም በቀላሉ እንዳይገኝ አድርጓቸዋል የሚል ነው ወይም ዎርምኦል በማንኛው ቦታ ላይ ልናገኛቸው እንችላለን ነገረ ግን ስፍታቸው 1*10^-30cm ብቻ ነው ይሄም ከቦታ ቦታ እንድንሄድ አያስችልም ያሉ ሲሆን በ"expanding of universe" ምክንያት ግን ከኛ በጣም የራቁ አከባቢዎች ላይ ሰፍተው ሊገኝ ይችላል ወይም ከቢልዬን አመታት በዋላ በኛ አከባቢም ሊፈጠር ይችላል የሚል ግምት ነው ያላቸው

ሌላኛው ጉዳይ ደግሞ ዎርምኦሎች የተረጋጉ አደሉም የሚል ነው ወይም በእንግልዘኛው "stability" የላቸውም እንደነሱ ግምት ከሆነ በዎርምኦሎች በኩል ማለፈ አይቻልም

በአልበርት አንስታይን ይኖራሉ ተብለው የሚገመቱት ኦርምኦሎች ቶሎ ቶሎ የሚፈራርሱ ወይም ቶሎ እየተከፈተ ቶሎ የሚዘጉ ነገሮች ናቸው ተክፍተው እንዲቀሩ ወይም በእንግልዘኛው "stable" እንዲሆን ከተፈለገ የተለዩ ነገሮች ወይም በእንግልዘኛው "some very exotic type of matter" ተብለው የሚጠሩ ነገሮች ያስፈልገናል ወይም ሳይንቲስቶች "hsu" ብለው ይጠሩታል ይሄ ነገረ በዚህ አፅናፍ አለም ውስጥ ይኑር አይኑር የሚታወቀ ነገረ የለም

ነገረ ግን "exotic matter" ቀደም ብለው ሳይንቲሲቶች ያወሩለተ ሲሆን ምን አይነተ ባህሪ እንዳለው ይታወቃለ በአውኑ ዘመን ነገረ ግን በተፈጥሮ ባይገኝም ሰው ሰርሻ "exotic matter" በ "ISS" ውስጥ ለናሙና ተሰርቷል

በቅርቡ በተሰራ ጥናታዊ ፁሑፍ ደግሞ ኦርምኦሎች "exotic matter" በውስጣቸው ካለ የተረጋጉ እንዲውም ለርዥም ጊዜ ተከፍተው ያሉ ወይም የማይቀያየሩ ባጠቃላይ ቋሚ ቅርፅ ይኖራቸዋል የሚል ነው ይሄ ማለተ ዎርምኦሎች በውስጣቸው በቂ የሆነ "exotic matter" በተፈጥሮ ሊኖራቸው ይገባል ወይም "artificially" መጨመር ይኖርብናል የተረጋጉ እንዲሆኑ ከተፈለገ

ይቀጥላል...

share share

@ethiotefer @ethiotefer
@ethiotefer
@ethiotefer @ethiotefer
1.1K viewsedited  15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-02 18:41:59
ክፍል ሁለተ

ኦርምኦል እና እስፔስታይም መስመሮች

ከዚህ ቀደም ማንኛውም ነገረ በእስፔስታይም መስመሮች ላይ ነው የሚሄደው ወይም ተቀምጦ ያለው ብለነ ነበር እንዲውም ግራቪት የምንለው ነገር ስበት ሳይሆን በእነዚህ መስመሮች ላይ እንድንሄድ የሚያስገድድ አይል እንደሆነ አይተናል

ዛሬ ደግሞ ኦርምኦል ቢኖር እስፔስታይም ምን ይመስላል የሚለውን እናያለን በምስሉ ላይ እንደምናየው እስፔስታይም መስመሮች መሀል ላይ ወይም "2" ቁጥር ላይ በአቋራጭ ተገናኝተዋል

ለምሳሌ የኛ ፕላኔት ያለቹ "1" ቁጠር ላይ ነው ብንል "4" ቁጠር ላይ ደግሞ መሉ በሙሉ በውሃ የተከበበቹ ፕላኔት አለች እንበል ከመሬት ተነስተነ ወደዚህ ፕላኔት ለመሄድ ሁለተ አማራጭ አለነ አንደኛው በ"3"ኛው ቁጠር በኩል ዙረን መሄድ ሲሆን ይሄም በትክክለኛው መንገድ ሄድን እንደማለተ ሲሆን በዚህ መንገድ በብርሃን ፍጥነተ ከተጓዝን 40 አመት ይፈጅብናል ወይም በፈጣኗ እስፔስክራፍት ከሄድን ደግሞ 700,000 አመት ይፈጅብናል ነገረ ግን በ"2"ቁጠር በኩል አቋራጭ መንግድ እንዳለ ይታያል

ይሄም እነ አልበርት አንስታይን "space time" መስመሮች ውስጥ ድልዲ አለ ሁለተ የተለያዩ ቦታዎችን የሚያገናኝ ወይም የሚያስተሳስር ይሄም ደግሞ ከቦታ ቦታ ለመሄድ አቋራጭ መንገድ ነው ወይም ጊዜ ና እርቀትን በእጅጉ ይቀንሳል ያሉት "Einistein-Rosen bridge" ወይም hormhole ብለን የምንጠራው ነው

"2" ቁጥር ባለበተ ቀዳዳ መሄድ ከቻልን ጉዞውን በደቂቃ ውስጥ ልንጨርሰው እንችላለነ ማንኛውም ነገረ እኛን ጨምሮ እስፔስታይም መስመሮች ላይ ነን እስፔስታይም መስመሮች በአይን አይታዩም ግን በነሱ ምክንያት የሚመጣውን ተፅኖ ማየት ይቻላል ጥያቄው ይሄንን አጭር መንገድ እንዴት እናግኘው ወይም እንዴት እንፍጠርው ነው
1.2K views15:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-01 18:34:32
በ2020 የነበሩ የአንድ አመት የእስፔስ ሳይንስ ወሳኝ ክስተቶች ወይም ለውጦች

1, ጨረቃ ከመሬት 3.8cm ሸሽታለቸ ወይም እርቃለቸ አንድ ቀነ ደግሞ መሬትን በ30 ቀን ሳይሆን በ47 ቀን ነው ዙራ የምትጨርሰው

2, ፀሐይ 134 ትሪሌን ቶን የሚሆነውን ክብደቷን አታለች ይሄም የሆነው የብርሃን ጨረረን ለመፍጠረ ባደረገቹ ሂደተ ነው

የመሬት ኦርቢት ደግሞ 15cm ሰፍቶል

3, 150 ቢልዬን ኮከቦች በዚህ በሚታወቀው አፅናፍ አለም ወስጥ ተፈጥረዋል ከ100 ቢልዬን በላይ ኮከቦች ደግሞ ፈነዳድተው፣ ወደተለያዩ ነገሮች ተቀይረዋል

4, አንድሮሜዳ ጋላክሲ 3.5 ቢልዬን ኪሎሜትሮችን አቋርጦ ወደኛ ጋላክሲ ወደሆነው ሚልክዌ ጋላክሲ ተጠግቷል ከቢልዬን አመታት በዋላ ደግሞ ይጋጫሉ


5, የኛ አፅናፍ አለም(universe) ደግሞ 60 ትሪሌን ኪሎ ሜትሮችን ሰፍቷል

share share

@ethiotefer @ethiotefer
@ethiotefer
@ethiotefer @ethiotefer
1.7K viewsedited  15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-31 16:59:29 ​ባለ ሶስት ፀሐዩ(ኮከብ) ፕላኔት
ወይም በሳንቲፊክ ስሙ "HD 188753" ይባላል

ይሄ ፕላኔት ሶስት ፀሐዮች ያሉት ሲሆን ሁለቱ አጠገብ ለአጠገ የሉት ፀሐዮች በአንድ በኩል ሲገኙ ሌላኝው ደግሞ በተቃራኒ በኩል ይገኛል ይሄ ፕላኔት ጨለማ የሚባል ነገረ አያቅም ወይም የኛ ፕላኔት ቢሆን 24 ሰሀተ ቀን ነበረ ምሽት የሚባል ነገረ አናቅም ሌላኛው ደግሞ በዚህ ምድር ላይ ብንኖር ሁለተ ጥላ ይኖረን ነበረ ይሄም የሚሆነው በሁለቱ ፀሐዮች ምክንያት ነው መሬት የኛን ፀሐይ ዙራ ለመጨረስ 365 ቀን ሲፈጅባት ይሄ ፕላኔት ግን የኛን ፀሐይ የሚያክለውን ኮከብ ዙሮ ለመጨረስ 3.36 ቀን ብቻ ነው የሚፈጅበት ይሄም የሚሆነው ለኮከቡ እጅግ የተቃረበ ሰለሆነ ነው

ፕላኔቱ ሁለተ የፊዚክስ ሕጓችን የሻረ ወይም የሚቃረን ነው የመጀመሪያው ትላልቅ ፕላኔቶች ከሚዞሩት ኮከብ እጅግ ይርቃሉ ልክ እንደ ጁፒተር እና ሳተርን የሚል ሲሆን ፕላኔቱ ግን ከሶስቱ አንዱ ከሆነው አና ትልቅ ከሆነው ፀሐይ 8 ሚልዬን ኪሎ ሜትር ብቻ ነው የሚርቀው ፕላኔቱ ግን እጅግ ትልቅ ነው ልክ እንደ ጁፒተረ ለምን እንዲ ተጠጋ የሚለውን መልስ መስጠተ የሚችል እሳቤ የለም በዚህም ቅርበተ የተነሳ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ሙቀተ አለው ፕላኔቱ በቅፅል ስሙ "hot Jupiter" ይባላል ወይም የገሀነቡ ምድር ልንለው እንችላለነ።

ሁለተኛው ይሄ ፕላኔት የተቃረነው እሳቤ ደግሞ ፕላኔቶች ኮከቦችን እንደሚዞሩ ነበረ የሚታወቀው ነገረ ግን የዚህ ፕላኔት ኦርቢት ምን አይነተ እንደሆነ አይታወቅም ወይም ግልፅ አደለም ወይም ከዚህ በፊት ከሚታወቀው በተለየ መንገድ ነው ይሄ ፕላኔት የተገኘው በ2005 ሲሆን ይሄንን ፕላኔት ሳይንቲስቶች ደግመው ለማየት በ2007 የሞከሩ ሲሆን ፕላኔቱ ግን ጥፍቷል ወይም ይገኛል በተባለበት ቦታ አልተገኘም ይሄም የሆነው አውን ላይ ሌሎች ፕላኔቶችን ለማግኘተ የምንጠቀመው ቴክኖሎጂ ለዚህ ፕላኔት አይሰራም ወይም የተወሳሰበ ኦርቢት ስላለው በኮከቦቹ ዙሪያ የተ እንዳለ በርግጠኝነተ ማወቅ አይቻልም።

ይሄ ፕላኔት ከኛ ምድር 149 የብረሃን አመት ይርቃል
በምስሉ ላይ የሚታዩት ሁለቱ ኮከቦች ልክ እንደፕላኔቱ መሀል ላይ ያለውን ትልቁን ኮከብ የሚዞሩ ሲሆን በሁለቱ ኮከቦች ማሀል ያለው እርቀተ ሳተርን እና ዩራኑስ የሚባሉት በኛ ሶላርሲስተም ውስጥ የሚገኙትን ፕላኔት በማከላቸው ያለውን እርቀት ያክላል ሁለቱ ኮከቦች በክብደት ትልቁን ኮከብ ወይም መሀል ላይ ያለውን ፀሐይ በክብደት ይበልጣሉ።

ከምንትዬዎቹ ፀሐዮች ወይም ሁለቱ አጠገብ ለአጠገብ ያሉት ፀሐዮች ከትልቁ ፀሐይ የሚርቁት 18 እጥፍ ከፀሐይ እስከ መሬት ያለውን እርቀተ ነው ወይም ከፀሐይ እስከ ጁፒተረ , ዩራኑስ እስከሚባሉት ፕላኔቶች ያለውን እርቀት ይሸፍናል።

በነገራችን ላይ ይሄ ፕላኔት ብቻ አደለም ከአንድ በላይ ኮከብ ያለው በዙ የተገኙ አሉ በዚህ ጉዳይ በሌላ ቀን እንመለስበታለን።

share share

@ethiotefer @ethiotefer
@ethiotefer
@ethiotefer @ethiotefer
1.4K viewsedited  13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-30 13:38:55
ይሄንን ያውቃሉ ከዛሬ 910 አመተ በፊቲ ጨረቃ ሰማይ ላይ ለወራት ያክል አልታየችም ነበረ

በ 1118EC ጨረቃ ሰማይ ላይ ሳትታይ ለብዙ ቀናት አስቆጥር እንደነበር የተለያዩ ምንጮች ወይም በወቅቱ የነበሩ ፀሐፊዎች የፃፈቱ ነገረ ነው ነገረ ግን እንዴት ጠፍች የሚለውን የሚያብራራ አካል አልተገኘም ነበረ።

በቅርቡ የተደረገ ጥናት ግን ለምን ለብዙ ወራት ሳትታይ ቀረቸ የሚለውን መልስ መስጠት ችሏል

ከሞላ ጎደለ ከአንድ ሚሊንዬም አመተ በፊት መሬት ላይ አንድ ክስተተ ነበረ ይሄም እጅግ ግዙፍ የሆነ ጉም ከፍተኛ የሆነ የ"sulphr" የተሰኘ ንጥረነገረ የያዘ ሲሆን "stratosphere" በሚባለው የመሬት ከባቢ አየር ወስጥ በመቀመጡ የተነሳ መሬት ከሞላ ጎደለ ጨለማ ውስጥ ነበረቸ ለወራት ወይም ለአመት ያክል በስተመጨረሻ ግን ይሄ "sulpher" የተሰኘው ንጥር ነገረ የያዘው ጉም ወደ መሬት መልሶ ወርዷል

ይሄ ክስተተ መኖሩን የሚረጋግጡ ጥናቶች ተገኝተዋል "ice sheets" በሚባለው አከባቢ በተወሰደ ናሙና መሰረተ "sulphur aerosols" የሚባል ንጥረ ነገረ መገኘተ ተችሏል ይሄም ንጥረ ነገረ የሚፈጠረው እሳተጎመራ (volcanic eruptions) ምክንያት ነው ይሄ እሳተጎመራ የተፈጠረው በ11012EC አመት ላይ ሲሆነ የተፈጠረበተ አከባቢ ደግሞ "iceland's hekla" ይባላል የዚህ እሳተጎመራ ጭስ ወደ ላይ በመሄድ "stratospher" የሚባለው የመሬት ከባቢ አየር ውስጥ የመድረስ አቅም እንደነበረው ጥናቱ ያሳያል በዚህም ጭስ ምክንያት ነበረ ጨረቃ ለብዙ ቀናት ሳትታይ የቆየቹ
ነገረ ግን በፀሐይ ብርሃን ላይ የከፍ ጉዳት አላደረሰም ወይም ከጨረቃ መጥፍት ውጭ የተለየ ክስተተ እንዳልነበረ ይነገራል

share share

@ethiotefer @ethiotefer
1.4K viewsedited  10:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-30 13:38:39
ከኛዋ መሬት ጋር የሚመሳለው ፕላኔት ወይም "kepler-22b" ብለነ እንጠረዋለን

ይሄ ኤክሶ ፕላኔት ወይም በእንግልዘኛው "exoplanet" ወይም "extrasolar
planet" የሚባል አይነት ሲሆን
ይሄ ፕላኔት የሚዞረው ኮከብ "kepler-22" የሚባል ሲሆን ከኛዋ ኮከብ ፀሐይ እጅጉን ይመሳሰላል የኛ ፕላኔት ከኛ ፀሐይ 150ሚልዬን ኪሎ ሜትር የምትርቅ ሲሆን ይሄም እርቀተ ሕይወት ላላቸው ነገሮች ምቹ ያደርጋታል ይሄም "kepler-22b" የተሰኘ ፕላኔት ከራሱ ኮከበ(ፀሐይ) የሚርቀው ልክ እንደኛ ፕላኔት ነው ወይም ተመሳሳይ ነው ይሄም ሕይወት ያላቸው ነገሮች የሚኖሩበተ አከባቢ ነው ወይም በእንግልዘኛው "habitabel zone" ብለን የምንጠራው አከባቢ ነው

ይሄ ፕላኔት የተገኘው በ2011 ሲሆን "habitable zone" የሚባለው አከባቢ የተገኘ የመጀመሪያው ፕላኔት ነው
ውሃ በዚህ ፕላኔት የመገኘት እድሉ ሰፊ ነው ውሃ ደግሞ ሕይወት ላላቸው ነገሮች መሰረታዊ ነገረ ነው እናም ይሄ አለም ለሰው ልጆች ኦነ ለሌሎች ፍጡሮች ጥሩ መኖሪያ መሆን ይችላል

"kepler-22b" የተሰኘው ፕላኔት ከኛ ምድር የሚርቀው 600 የብርሃን አመተ ነው ወደዚህ ፕላኔት ለመሄድ አውን ላይ እጅግ ፈጣን የሚባለውን "New Horizons" የሚባለውን እስፔስክራፍት ብንጠቀም እንኳን 26 ሚልዬን አመተ ያስፈልገናል ይሄ እስፔስ ክራፍት የሚጓዘው በሰሀተ 59,000km እንደሆነ ይታወቃል

ይሄ ፕላኔት ከኛ ፕላኔት የሚበልጥ ሲሆን የራሱን ኮከብ ዙሮ ለመጨረሰ 290 ቀን ይፈጅበታል አስተውሉ የኛ ምድር የኛን ፀሐይ ዙራ ለመጨረስ 365 ቀነ ነው የሚፈጅባት ይሄ ብቻ ሳይሆን የኛ ኮከበ(ፀሐይ) እና የፕላኔቱ ኮከብ አንድ አይነተ ወይም በእንግልዘኛው "G-type" ብለን የምንጠራቸው የኮከብ ዝርያዎች ውስጥ ይመደባሉ
1.5K views10:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ