Get Mystery Box with random crypto!

Ethio cyber

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiotefer — Ethio cyber E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiotefer — Ethio cyber
የሰርጥ አድራሻ: @ethiotefer
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 109
የሰርጥ መግለጫ

አላማችን በሳይንስ እና በቴክኖሎጂ የታነፀ ትውልድ መፍጠር ነው።
ሐሳብ አስተያዬት ለመስጠት👇👇👇
@Ethiospace1_bot
@unverseand 👈ለcross

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 49

2021-03-17 18:30:56 ስለ Hacking ለማወቅ

programing ለመማር

ስለ ቴክኖሎጂ ለማወቅ

የተለያዩ app ለማግኘት

ስልክ እንዴት እንደሚጠለፍ ለማወቅ


wifi password እንዴት hack እንደሚደረግ

mega byte እንዴት እንደሚሰረቅ


telegram እንዴት hack እንደሚደረግ

ሁሉንም የ technology መረጃዎች እኛጋ ያገኛሉ



ይቀላቀሉን
️ ️ ️ ️
232 views15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-16 09:44:19 ​ሙሉ ለሙሉ መኖሩ ያልታወቀው ፕላኔት ወይም በእንግዘኛው "planet x"

ይሄ ፕላኔት አለ ተብሎ የሚታሰበው በኛው ስርሀት ፀሐይ ስር ወይም በኛ ሶላር ሲስተም ውስጥ ሲሆን ዘጠኛው ወይም ከፕላኔት ኔፕቱን ከጠሎ ያለ ፕላኔት ነው ።

ይሄ "planet x" የተባለ ፕላኔት ሊኖር ይችላል የተባለው አጠቃላይ ሰለስምንቱ ፕላኔቶች በተሰራ ሒሳባዊ ትንታኔ ነው እንደሚታወቅው ኔፕቱን የተባለው ፕላኔት መጀመሪያ መኖሩ የታወቀው በሒሳባዊ ትንታኔ ወይም በሀሳብ ደረጃ ነበረ ነገረ ግን በተገመተበት ቦታ እና አቅጣጫ ሊገኝ ችሏል ይሁን እንጂ ይሄ "planet x" የተባለው ፕላኔት በሒሳብ እና በአሳብ ደረጃ አለ ይባል እንጂ ፕላኔቱ እስካውን ሊገኝ አልቻለም ልክ እንደ ኔፕቱን ወይም እሰሰካውን የተ እንዳለ, እንዴት እንደሚሽከረከረ አይታወቅም ይሄ ብቻ ሳይሆን አንዴም እንኳን በቴሌስኮፕች አይን አለመግባቱ ነው።

ሰለ ፕላኔቱ ሳይንቲስቶች የሰሩት ጥናት አደሚያሳየው ከሆን ፕላኔቱ የኛን መሬት በክብደተ አስር እጥፍ እንደሚያክል ወይም ሳተርን ከተባለው ፕላኔት ጋር በክብደት አቻ ነው ይሄ ፕላኔት አንድ ዙር ፀሐይን ዙሮ ለመጨረስ ከ10,000 አመት እስከ 20,000 አመት ያስፈልገዋል ይሄም የሆነው ፕላኔቱ እጅግ ከፀሐይ እርቆ ሰለሚገኘ ነው በጠፈር ሳይንስ ሕግ ከኮከባቸው እርቀው የሚገኙ ፕላኔቶች ኮከባቸውን በእረጅም አመተ ውስጥ ዙረው ሲጨርሱ በጣም ቅርብ ለምሳሌ እንደ ሜርኩሪ ያሉ ፕላኔቶች ደግሞ ባጭር ጊዜ ውስጥ ዙረው ይጨርሳሉ።

ይሄ ፕላኔት አለ ተብሎ የሚታስብበተ ቦታ ከፃሐይ እስከ መሬት ያለውን እርቀተ ከ200 እስከ 1200 ሊያጥፍ ይችላል ወይም ምን አልባት ከፀሐይ 200ቢልዬን ኪሎ ሜትሮች ይርቃል ይሄም ከፀሐይ እጅግ እሩቅ የሚገኝ ፕላኔት ያስብለዋል ሰለዚህ ፕላኔት ጠፍርተኞቹ ብዙ ነገረ ይበሉ እንጂ ይሄ ፕላኔት የመገኘት እድሉ ወይም ቻንሱ 1/150,000 ነው ባጠቃላይ ትንሽዬ ቻንስ ያለው ይመስላል

ይሄ ፕላኔት ለምን አልተገኘም?

እንደ አንዳዶች መላምት ከሆነ ይሄ ፕላኔት እንደሌሎች ፕላኔቶች አደለም ፀሐይን የሚዞረው ማለትም ሁሉም ፕላኔቶች ፀሐይን የሚዞሯት ትይዩ ሁነው ነው ወይም በእንግልዘኛው አቀማመጣጨውን "plane orbital " ልንለው እንችላለነ ግልፅ ለማረግ ያክል ፀሐይ መሀል ላይ ስትሆን ፕላኔቶቹ ግን በትይዩ ይዞሯታል ለዚህ ሁሉም ፕላኔቶች ላይ ሁናቹ የተቀሩትን ፕላኔቶች ማየት ትችላላቹ ምክንያቱም ትይዩ ሁነው ሰለሚንቀሳቀሱ በዚህም ምክንያት ነው መሬት ላይ ሁነን ሁሉንም ፕላኔቶች ማየት የምንችለው ነገረ ግን ይሄ "planet x" የተባለ ፕላኔት ፀሐይን የሚዞራት እደተለመደው አይነተ አደለም ወይም በተፃራሪ አቃጣጫ ወይም በእንግልዘኛው "perpendicular" ሁኖ ነው የሚዞረው ከሌሎቹ ፕላኔቶች አንፃር ሰለዚህ ይሄ ፕላኔት በተለመደው አይነተ ቴክንሎጂ ላይገኝ ይችላል የሚል መላምት አለ።

share share

@ethiotefer @ethiotefer

@ethiotefer @ethiotefer
508 viewsedited  06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-12 21:05:15 ወቅታዊ....

የፊታችን መጋቢት 12 ትልቅ አስትሮይድ ምድርን ተጠግቶ ያልፋል።

ናሳ በፈረንጆቹ መጋቢት 21 አንድ ትልቅ አስትሮይድ ምድርን ተጠግቶ እንደሚያልፍ ተናገረ፡፡ እንደ የህዋ ምርምር ተቋሙ መረጃ ከሆነ ትልቁ አስትሮይድ ከምድር 1.25 ሚሊዮን ማይሎች ያክል ይቀርባታል፡፡

ይህ አጋጣሚም ለተመራማሪዎች አስትሮይድን በቅርበት የመመልከት እድል ይፈጥርላቸዋል ሲል አሜሪካዊው የህዋ ምርምር ተቋም ተናግሯል፡፡ ተቋሙ አክሎም አስትሮይዱ ከ20 ዓመታት በፊት የተገኘ እና በመጠኑም 3000 ጫማዎች የሚያክል ዲያሜትር ይደርሳል ብሏል፡፡

ለመሬት ቅርብ የሆኑ ነገሮችን የሚያጠናው ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ፓውል ኮዳስ የዚህን 2001 FO32 ኦርቢታዊ መተላለፊያ በትክክል እናውቀዋለን ያሉ ሲሆን አስትሮይዱ ከ1.25 ሚሊዮን ማይሎች በላይ ወደ ምድራችን ሊቀርብ አይችልም ሲሉ አረጋግጠዋል፡፡ ይህም በግርድፉ መሬት ከጨረቃ ካላት ርቀት 5.25 እጥፍ ያክል ማለት ነው፡፡ ምንም እንኳን አስትሮይዱ እንዲህ ባለ ርቀት መሬትን እንደሚያልፋት ቢነገርም ለአደጋ የሚያጋልጥ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

ይህ አስትሮይድ በሰዓት 77 ሺህ ማይሎች ያክል እየተምዘገዘገ ያለ ሲሆን ከሌሎች አስትሮይዶች አንጻር ሲታይ በጣም ፈጣን እንቅስቃሴ ላይ ያለ ነው፡፡ አሁን ላይ ስለ አስትሮይዱ የታወቁት ነገሮች ጥቂት ሲሆኑ ወደ ምድር የበለጠ እየተጠጋ ሲሄድ ብዙ ነገሮችን መረዳት ይቻላል ሲሉ አንድ የናሳ ተመራማሪ ተናግረዋል፡፡

ናሳ እንደሚለው ከሆነ የስነ ፈለክ ተመራማሪዎች ስለ አስትሮይዱ ስሪትና መጠን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማዎቅ ትልቅ ተስፋን ሰንቀዋል፡፡ ተቋሙ የፀሐይ ብርሃን አስትሮይዱን በሚያገኘው ጊዜ በአለቱ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ማዕድናት ሞገዶችን ሲውጡ አንዳንዶች ደግሞ ያንጸባርቃሉ ሲል ተናግሯል፡፡ እነዚህን ተንጸባራቂ ሞገዶች በመጠቀም ተመራማሪዎች በአስትሮይዱ ላይ የሚገኙ ማዕድናትን ምንነት መለየት እንደሚችሉ የምርምር ተቋሙ አስገንዝቧል፡፡

አስትሮይዱንም በደቡባዊ ንፍቀ ክበብ እንዲሁም በሰሜናዊ ዝቅተኛ አካባቢ ሲያልፍ መካከለኛ ቴሌስኮፕን በመጠቀም መመልከት ይቻላል ሲል ናሳ ተናግሯል፡፡ ይህንንም ለማድረግ የኮከብ ቻርትን መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡

ATC NEWS

ለተጨማሪ መረጃ "Daily Science to all"

https://t.me/sciencetoall/11055

Share Share

@ethiotefer @ethiotefer

@ethiotefer @ethiotefer
186 views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-11 17:59:49 በተለምዶ ሰማይ ወይም የሁሉም ነገረ መጨረሻ ብለን የምናስበው ነገረ በሰው ልጆች አይን የሚታይ አደለም ወይም አፅናፍ አለም ከሚታሰበው በላይ ጨለማ ነው አፅናፍ አለም መጨረሻ ወይም የአፅናፍ አለም ጥግ የተ እንደሆነ እና ምን እደሚመስል አይታወቅም መሬት ላይ ሁነን የምናየው ሰማያዊ ነገረ የሁሉም ነገረ መጨረሻ ሰማይ ሳይሆን ከመሬት የተወሰነ ኪሎ ሜትሮችን እርቆ የሚገኘ ነገረ ነው

ይሄ ሰማያዊ ነገረ የሚፈጠረው በቅርብ እርቀት ወይም በመሬት ከባቢ አየረ ውስጥ ሲሆን ሳተላይቶች ከዚህ እርቀው ነው የሚገኙት ወይም ሳተላይቶች ላይ ሁነን ይሄንን ሰማያዊ ነገረ ወደ ታች ነው የምናየው ወይም ጨረቃ ላይ ሁነን ምድርን ስናያት ደግሞ መሬት ሰማያዊ ፕላኔት መስላ ትታያለች

አይዛክ ኒውት አንድ ግኝት ነበረው ይሄም የፀሐይ ብረሃን የሰባት ቀለሞች ስብጥር እንደነበረ እና ሰባቱንም ቀለሞች የራሱን ዘዴ በመጠቀም መነጣጠል ችሎ ነበረ ከፀሐይ የመጣውን የብርሃን ጨረረ በመጠቀም።

በየቀኑ የምናየው ብርሃን የሰባት ቀለሞች ሁደተ ሲሆን ፍሬኪዌንሲውም(frequency) በተማሳሳይ የሰባቱ ቀለሞች ድምር ነው ሰለዚህ ሁሉንም "frequncey" መነጣጠለ ከቻለን ሰባቱንም ከለሮች ለየብቻ ማየት እንችላለን የፀሐይን ብርሃን ለሰባት የተለያዩ ከለሮች መነጣጠለ ከሚችሉ ነገሮች አንዱ አየር ወይም የአየር ሞለኪሎች(molecules) ሲሆኑ ሁለተኛው ደግሞ ውሃ ነው።

ምድር ላይ ሁነን የምናየው ሰማይ ለምን ሰማያዊ ሆነ?

የፀሐይ ብርሃን ወደ መሬት ከባቢ አየረ ውስጥ ሲገባ የተለያዩ የአየር ሞለኪሎች ያጋጥሙታል በዚህ ወቅት ከሞለኪሎቹ ጋር እየተጋጨ ወደ ተለያዩ ቦታዎች ይበተናል በዚህ ወቅት ሰማዊ ከለር ከሌሎቹ ከለሮች አፈትልኮ በመውጣት ለብቻው ይንቀሳቀሳል ምክንያቱም እጅግ ፈጣን የብርሃን አይነተ ሰለሆነ ከሌሎቹ አንፃር በዚህ ወቅት ሰማያዊ ብርሃን ሰማይ ላይ በቀላሉ ይታያል በዚህ ምክንያት ከመሬት ሁነን ወደ ላይ ስንመለከተ ሰማያዊ ይታየናል

የፀሐይ ብርሃን በውሃ ውስጥ ሲያልፍ ደግሞ ለ ሰባት የተለያዩ ከለሮች ይከፍፈላል ይሄም የሚሆነው በውሃ (droplet) አማካኝነተ ሲሆን አንድ ወጥ የሆነው የፀሀይ ብርሃን "frequency" ወደ ተለያዩ "frequency" ዎች ይበትነዋል በዚህም ወቅት ሰባት የተለያዩ የብርሃን ቀለማት ይፈጠራሉ

ቀስተ ደመና የሚፈጠረውም በዚው መንገድ ነው ማለትም የፀሐይ ብርሃን በደመናው ውስጥ በሚያልፍበት ወቅት ደመና ውስጥ ያለው የውሃ "droplet" ያገኘዋል በዚህ ወቅት የፀሐይ ብርሃን በውሃ ጠብታዎች(droplet) ውስጥ ይንፀባረቅ እና ወደ ተለያዩ የብርሃን ቀለማት ይቀየራል

ሁሉም ቀለሞች የሚፈጠሩበት የራሳቸው "frequency" አላቸው ለምሳሌ ብርሃን ፍሬኩንሲው 610 THz ከሆነ የሚፈጠረው ብርሃን ሰማያዊ ይሆናል የቀይ ደግሞ 430 THz ነው በእንዲ አይነተ መንግድ ቀለማትን እንለያለን

Share share

@ethiotefer @ethiotefer
@ethiotefer
@ethiotefer
446 viewsedited  14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-11 17:58:22 "James Webb Space" የተሰኘው ቴሌስኮፕ እንዴት 12 ቢልዬን አመት ወደ ዋላ ሊወስደን ይችላል?

ይሄ ቴሌእስኮ በቅርብ ወራት ውስጥ ወደ ጠፈረ የሚላክ ሲሆን አፅናፍ አለም ከ12 ቢልዬን አመተ በፊት ምን አይነተ ገፅታ እደነበረው ያሳያል ተብሎ ይታመናል። ይሄ እንዴት ሊሆን ይችላል?

ሚስጥሩ ብርሃን ነው , የሰው ልጆች ሆኑ ማንኛውም ነገረ የብርሃን ጨረረ ሲኖር ብቻ ነው ማየት የሚችሉት ወይም ሌሎች የብርሃን አይነት ጨረሮች ሲኖሩ ብቻ ነው።

አይኖቻችን ያለ ብርሃን ምንም ናቸው ለምሳሌ አንድ ሰው የቤቱን ብር አየ ስንል ከፀሐይ የመጣው ብርሃን በሩ ላይ ካረፈ በዋላ አንፀባርቆ ወደ አይኑ ሲገባ ብቻ ነው በሩን የሚያየው ከዛ ውጭ ምስል አይምሮ ውስጥ አይቀረፀም ወይም አይታይም በሩ ላይ ተንፀባርቆ የሚሄደው ብርሃን ደግሞ እጅግ ፈጣን ሰለሆን በሩን በቅፅበት ያየነው ይመስላል ነገረ ግን በቅፅበት የሚሆን ነገረ የለም
ማለትም ብርሃን ከበሩ ተነስቶ ወደ አይኑ ሲገባ የሆነ ጊዜ ይወስድበታል

ምንም እንኳን ከኛ ብዙ ያራቀነ ነገረ ስናየው በቅፅበት ልንለውል እንችላለን ከብርሃን ፍጥነተ አንፃር ነገረ ግን በጣም እሩቅ ሲሆን እንደዛ ብሎ መደምደም አይቻልም

ለምሳሌ ጨረቃን መሬት ላይ ሁነን ስናያት የምናየውም የጨረቃ ገፅታ ከአንድ ሰከንድ በፊት የነበረውን እንጂ በቅፅበት ያላትን ገፅታ አደለም ፀሐይን ስንመለከታት ደግሞ ከ8 ደቂቃ በፊተ የነበረውን የፀሐይን ገፅታ እንጂ በቅፅብት አደለም የምናያት

የማታዎቹ ኮከቦችን ስናያቸው ደግሞ በቅፅበት ያላቸውን ገፅታ ሳይሆን ከሽህ ወይም ከሚልዬን አመት በፊት የነበራቸውን ገፅታ ነው ልናይ የምንችለው ማለትም የኮከቦቹ ብርሃን እኛ ምድር ላይ የሚደርሰው ከሽህ ወይም ከሚልዬን አመት ጉዞ በዋላ ነው ይሄ ብቻ አደለም በዚቺ አውን በምናይበት ቅፅበት ኮከቦቹ ጠፍተው ወይም የሆነ ነገረ ሁነው ሊሆን ይችላል ነገረ ግን ይሄንን ለውጥ ለማየት ሌላ ሽህ ወይም ሚልዬን አመት ሊያስፈልገን ይችላል ይሄ ሁሉ የሚሆነው ብርሃን በሰከንድ 300,000km እየተጓዘ ነው

ለምሳሌ "NGC1052-DF2" የተሰኘው ጋላክሲ ከሰው ልጆች 70 ሚልዬን የብርሃን አመት ይርቃል ዳይነሶሮች ከኛ አለም ከጠፉ ደግሞ 65 ሚልዬን አመተ አልፎታል የተለዩ ፍጥሮች በዚህ "NGC1052-DF2" የተባለ ጋላክሲ ውስጥ አሉ ብለን ብናስብ እና ከኛ እጅግ የረቀቀ ቴሌስኮፕ ቢኖራቸው ማለትም የኛ ምደር ላይ ያለውን ነገረ በሙሉ ማየት የሚያስችል ነው ብንል እና አውን በዚች ቅፅበት ወደ ሚልክዌ ጋላክሲ ውስጥ ወደ ሚገኘው ፀሐይ እና ፀሐይን ወደምትዞረዋ መሬት ቢመለከቱ የሚያዩት ከ65 ሚልዬን አመት በፊት የጠፉትን ዳይንሰሮችን(Dinosaurs) ይሆናል

ይሄ በቅርቡ ይላካል ተብሎ የሚጠበቀው ቴሌስኮፕ 12 ቢልዬን አመተ ወደ ዋላ ይወስደናል ማለተ 12 ቢልዬን አመተ ሙሉ ተጉዙ የመጣውን ብርሃን አጉልቶ ያሳየናል እንደማለተ ሲሆን ብርሃኑ አንፀባርቆ የመጣበትን ፕላኔት ወይም የኮከብ ገፅታ ያሳያል ማለተ ነው ብርሃኑ አንፀባርቆ የሚመጣው ውይም ምድር ላይ የሚደርሰው ከ12 ቢልዬን አመተ በዋላ ነው ይሄ ማለተ ደግሞ ብርሃኑ ወደ መሬት ይዞ የሚመጣው ብርሃን የያዘው መረጃ ከ12 ቢልዬን አመት በፊት የነበረውን ነገረ ሁኔታ ወይም ታሪክ ነው።

ይሄ ቴሌስኮፕ እንደ አብል ቴሌስኮፕ ምድርን አደለም የሚዞረው ...ቴሌስኮፑ የሚዞረው መሬትን ሳይሆን ፀሐይን ነው ልክ እንደፕላኔቶች ነገረ ግን በመሬት ትይዩ ነው የሚዞረው ፀሐይን ሰለዚህ መረጃዎችን በቀላሉ ወደ ምድር ይልካል ተብሎ ይጠበቃል

ቴሌስኮፗች ስራቸው የሩቅን ነገረ አቅርቦ ማሳየተ ነው ወይም አግዝፎ ማሳየት ነው ወይም አንፀባርቆ የመጣውን ብርሃን በማግዘፍ የሰው ልጆች እዲያዩት ማመቻቸተ ነው እና ለምን ምድር ላይ እንዳሉ አንጠቀማቸውም ወይም ለምን ወደ ጠፈረ መላክ አስፈለገ ?

እንዚህ እስፔስ ነከ ቴሌስኮፖች ብዙዎቹ እጅግ በጣም ሰንሴቲቪ ናቸው ማለትም በቀላሉ ሊታወኩ ይችላሉ ለምሳሌ ምድር ላይ ብዙ አይነተ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮአዊ ብርሃኖች አሉ ሰለዚህ እንዚህ ብርሃኖች ከረቁ ቦታ የሚመጡትን ብርሃኖች የማጥፍት ወይም የማወከ አቅም አላቸው ሌላው ደግም የመሬት ከባቢ አየረ ወደ መሬት ብርሃን እንዳይመጣ የማገድ አቅም አለው ሰለዚህ መፍትሔው ቴሌስኮፖችን ድቅድቅ ጨለማ ወደሆነው ጠፈረ መላክ ነው

share share

@ethiotefer @ethiotefer

@ethiotefer

@ethiotefer @ethiotefer
483 viewsedited  14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-10 21:22:47
አስገራሚ ቻናል

በየቀኑ የሚገራርሙ እውነታዎች ሚለቀቁበት

አስገራሚ ዜናዎች

እየተዝናኑ እውቀት የሚጨብጡበት

አሁኑኑ ይቀላቀላሉ Join Now
162 views18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-05 20:36:33 ​ወቅታዊ ጠፈረ ነከ ዜናዎች

UAE(United Aerb Emrete) ወደ ማርስ እስፔስ ክራፍት የላከቹ ከሰባት ወር በፊት ሲሆን እስፔስክራፍቱ ማርስ ላይ ደርሶ ማርስን መዞር የጀመረቹ ባለፈው ሁለተ ሳምንት ውስጥ ነበረ
እስፔስ ክራፍቱ በዋንኝነት የሚያጠናው የማርስን የአየር ባሀሪ ነው

ይሄ እስፔስ ክራፍት ከምድር የተነሳው ባለፈው አመት "july 2020 " ሲሆን ከ7 ወረ በዋላ ማርስ ጋር መድረስ ችሏል
ይሄም ዱባይ ወደ ቀዮ ፕላኔት ወደሆነቹ ማርስ እስፔስክራፍት የላከች አምስተኛዋ አገረ ያስብላታል ከአረቡ አለም ደግሞ የመጀመሪያዋ አገረ ነች እስፔስ ክራፍቱ ማርስን በተሳከ ሁኔታ መዞሩን ተከትሎ የዱባይ ከተሞች እና ፎቀች በቀይ አሸብረቀው ታይተው ነበረ

በተመሳሳይ ናሳ እጅግ የረቀቀቹን ሮቨር ማርስ ላይ ማሳረፈ የቻለው በዚህ ሁለተ ሳምንት ውስጥ ሲሆን እስከዛሬ ወደ ማርስ ከተላኩ ሮቨሮች ሁሉ እጅግ የረቀቀው በቅርቡ የተላከው ሮቨሩ(Rover) ነው ሮቨር የራሱ የሆነ በራሪ ሂሊኮፍተረ ያለው ሲሆን እጅግ የጠራ ምስል እና ቪድዮ ወደ ምድር መላክ ጀምሯል

ይሄ ሮቨር አጠቃላይ 471 ሚልዬን ኪሎ ሜትር ተጉዟል ማርስ ላይ ለመድረስ ይሄንን ሮቨር ይዞ ሲንቀሳቀሰ የነበረው እስፔስክራፍት 19,500km በሰሀት ይጓዝ ነበረ ሄንን ጉዞ ለማጠናቀቀ 43 ቀን ብቻ ነው የፈጀበተ ይሄ በጣም የረቀቀ የተባለው ሮቨር በማርስ ምድር ሕይውት ያለው ነገረ ሰለመኖሩ የጠናል ተብሎ ይጠበቃል ለዚህም አላማ ሲባል ሮቨሩ ያረፈበተ የማርስ ምድር ለጥናቱ የተሻለ ነው በሚል የተመረጠ አከባቢ ነው ይሄ እስፔስ ክራፍት ማርስ ጋር የደረሰው "Feb 18 2021" ነበረ

share share

@ethiotefer @ethiotefer

@ethiotefer @ethiotefer
81 viewsedited  17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-05 20:30:30 አይዛክ ኒውተን ይበልጥ የሚታወቅበተ ግኝቱ ደግሞ ሶስቱ የእንቅስቃሴ ሕጎች ሲሆኑ ብዙዎቻችን እናቀዋለነ ብዬ አስባለው

እንዚህ ሶስቱ የእንቅስቃሴ ሕጎች በሳይንሱ እንዲውም በጠፈረ ሳይንስ ትልቅ ድርሻ አላቸው ለምሳሌ እሮኬት የሚቶከሰው የኒውተንን ሶስተኛ የእንቅስቃሴ ሕግ ተጠቅሞ ነው ፕሌን አየረ ላይ የሚበረው የኒውተንን የእንቅስቃሴ እጎች ተጠቅሞ ነው።
ባጠቃላይ ተፈጥሮዊ እና ሰው ሰራሽ የሆኑ ነገሮችን በሙሉ የኒውትን የእንቅስቃሴ ሕግ ጠብቀው ነው የሚንቀሳቀሱት

አይዛክ ኒውተን ሌላው የፈጠረው ነገረ ካልኩለስ(calculus) የሚባለውን ሒሳብ ሲሆን ካልኩለስ የሚባለው ሒሳብ በውሰጡ(limits,continuity,derivatives,integerts and infiniti series) የሚባሉትን ሒሳብ የያዘ ነው።

ምንም እንኳን ኒውተን የካልኩለስ ፈጣሪ ይባል እንጂ በየጊዜው እያደገ የመጣ ሒሳብ ነው ያለ ካልኩለስ የአውኑ አለም ወይም አውን የሰው ልጆች የደረሱብት የቴክኖሎጅ ደረጃ አይታሰብም በተለይ በሳይንሱ አለም ለምሳሌ "engineering " አይታሰብም የካልኩለስ ሒሳብ በኢትዮጲያ ከ12ኛ ክፍል ጀምሮ የሚሰጠ ሲሆነ በ engineering ፊልድ ወደ ግቢ ከገባቹ ደግሞ ትምህርታቹ በአብዛኛው ካልኩለስ ይሆናል።

አይዛክ ኒውተን ያገኘው ሊላው ነገረ ደግሞ የፀሐይ ብርሃን የሰባት ቀለሞች ውደተ እንደሆን እናም የራሱን መሰሪያ በመሰራት መሰሪያው የፀሐይን ብርሃን ለሰባት ከለሮች ከፍሎ በማሳየቱ እሳቤው ትክክል እንደነበረ አረጋግጧል

ከዚህ ግኝት በዋላ እኛ የምናየው ሰማይ ለምን ሰማያዊ ሆን ቀስተ ደመና እንዴት ነው የሚፈጠረው የሚሉትን ጥያቄዎች በተሻለ መንገድ መመለስ እንዲችሉ ያደረገ ግኝት ነበረ።

የአይዛክ ኒውተንን ታሪክ እና ስራዎች በትነሹ ይሄንን ይመስላል

Share share

@ethiotefer @ethiotefer

@ethiotefer @ethiotefer
89 viewsedited  17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-05 20:29:11 የመሬትን ክብደት እንዴት ማገኝት ይቻላል የአይዛክ ኒውተንን ቀመር በመጠቀም

የመሬትን ክብደት የምንፈልገው በአንተ ወይም በአንቺን እና በመሬት መሀል ያለውን አይል ተጠቅመን ነው

አንተ ከፎቅ ላይ እየወደከ ነው ብለነ ብናስብ በአንተ እና በመሬት መሀል ያለው አይል ግራቢቲ ሲባዛ የአንተ ክብደተ ነው ወይም F=m1g በዚህ መጠን ነው ወደታች የምትገፍው በሌላ አባባል ደግሞ ይሄንን አይል F=Gm1m2/r^2 በሚለው ማግኘት እንችላለን ማለተ ነው
m1 የአንተ ክብደተ ሲሆን m2 ደግሞ የመሬት ነው "g" ደግሞ መሬት እኛን የምትስበት የፍጥነተ መጠነ ነው ይሄም ቋሚ ቁጥር ሲሆን ያገኘው ጋሊሎጋላሊ የተባለው ሳይንቲስት ነው መጠኑ ደግሞ g=9.81N/kg ነው አውን ወደ ሒሰቡ እንግባ

F=m1g=Gm1m2/r^2

ይሄ ማለተ

m1g=Gm1m2/r^2

m1 የአንተ ክብደት ሲሆን በሁለቱም ጎን ይገኛል ለዚህ እናጣፍው ከዛን እንደሚከተለው ይቀራል

g=Gm2/r^2 ወይም

m2= gr*r/G

"r" ማለተ በአንተ እና በመሬት መሀል ያለው እርቀተ ወይም በአንተ እና ከመሬት መሀለኛው ክፍል አንስቶ ያለው እርቀተ ነው አንተ ያለከው መሬት ላይ ነው ለዚህ አንት ከመሬት መሀለኛው ክፍል የምትርቀው በመሬት "radius" መጠነ ነው የመሬትን radius እንዴት እንደተገኘ ደግሞ ከዚህ በፊት አይተናል

በተመሳሳይ

G=0.0000000000667=6.67*10^-11

ሰለዚህ ሶስቱንም ቁጥሮች እናቃለነ ማለትም G,g,r ሰለዚህ አሁን እንተካው...

m2=9.81*(6.4*10^6)^2/6.7*10^-11

ይሄንን ቁጥር በካልኩሌተር ስንሰራው

m2=6*10^24 ይመጣል

ወይም የመሬት ክብደተ 6000,000,000,000,000,000,000,000,000 kg ነው

የፀሐይንም ክብደተ በተመሳሳይ መንገድ መፈለገ ይቻላል ወይም በቀጣይ እነሰራዋለነ

share share

@ethiotefer @ethiotefer

@ethiotefer @ethiotefer
87 views17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-05 20:28:45 የአይዛክ ኒውተን ግኝቶች በትንሹ

አይዛክ ኒውተን ካገኛቸው ግኝቶች አንዱ ወይም በጠረፈረ ሳይንሱ አልመ ትልቅ ድርሻ ያለው ምርምር ሲሆን ጥናቱም በሁለተ ክብደተ ባላቸው ነገሮች ማሀል መሳሳብ አለ ይሄም ፔላኔቶች በፀሐይ ዙሪያ ለምን እንደሚዞሩ እንዲውም ጨረቃ ከመሬት ተነጥላ ለምን እንደማትሄድ ሰዎች ለምን በመሬት እንደሚሳቡ ያስረዳ ሐሳብ ነበረ

"universal gravitational law" የሚባለው የኒውተን እሳቤ ስናብራራው እንደሚከተለው ነው

ማንኛውም ቁሱ ክብደት ካለው ማንኛውንም ነገረ የመሳብ አቅም አለው ይሄ ማለት ሰው ከሰው ሊሳሳብ ይችላል ወይም ሰው ድንጋይን ፕላኔት ጨረቃን ፀሐይ ፕላኔትን የኛ ፕላኔት እኛን ልትስብ ትችላለቸ በተቃራኒው እኛ መሬትን እንስባለን ምክንያቱም ክብደት ስላለን እና ስላላቸው ።

በሁለተ ቁሶች መሀል ያለውን አይል(force) እንዴት ነው የምንፈልገው

አይዛክ ኒውትን ያገኘው እሳቤ ለዚህ መልስ የሚሰጥ ነው ይሄም የሁለቱ ቁሶች ክብደት ከአይሉ ጋር ቀጥታ ግንኙነተ ያለው ሰሆን በሁለቱ ቁሶች መሀል ያለው እርቀተ ጋር ግን የተቃረነ ግንኙነተ ወይም (inversely) ነው ይሄም ሲፃፍ

F=Gm1m2/r^2

ይሆናል

m1 = የአንደኛው ቁስ ክብደተ
m2= የሁለተኛው ቁስ ክብደተ
G= " universal gravitational constant" የሚባል ቋሚ ቁጥር ነው
r = በሁለቱ ቁሶች መሀል ያለው እርቀተ
F= በሁለቱ ቁሶች መሀል ያለው አይል ወይም (Force) ነው

ይሄ ማለተ የፀሐይን እና የመሬትን ክብደተ ካወቀን በመሀላቸው ያለውን አይል ማገኘት እንችላለን እንደማለተ ነው
"G" የተባለውን ቋሚ ቁጥር ያገኘው ሳይንቲስት "Cavendish" የሚባል ሳይንቲስት ሲሆን ይሄም የተገኘው ኒውተነ በኖረበተ ዘመነ ሲሆን ይሄም 1798 ነበረ ሳይንቲስቱ ይሄንን ቁጥር ለማምጣት ብዙ ሙከራዎችን አድርጎ ነበረ ይሄም ቁጥር በጣም ትንሽ ሲሆን እንዲሚከተለው ይፃፍል

G=0.0000000000667310

ይሄም ማለተ በሁለተ ቁሶች መሀል ያለው አይል በጣም ትንሽ እንደሚሆን ያሳያል በዚህም ምክንያት አኛ ከሌሎች ሰዎች ወይም ግውዝ ነገሮች ጋር የለውን መሳሳብ አንረዳውም በቀላሉ መሬት ግን በጣም ትልቅ ክብደተ ስላላት ይታወቀናል መሬት ከኛ የተሻለ ክብደተ ስላላት አኛ ወደሷ እንሳባለነ ከኛ ያነሰ ክብደተ ያለው ነገረ ደግሞ ወደኛ ይሳባል ነገረ ግን አይሉ በጣም ትንሽ ሰለሆነ ለውጡን በቀላሉ ላንረዳው እንችላለነ

ይሄ ቀመር ለጠፈረ ሳይንስ ከፍተኛ የሆነ አስተዋፆ አለው ይሄም የፕላኔቶችን ክብደተ የኮከቦችን ክብደተ, ፍጥነታቸውን እንዲውም ስፍታቸውን ሌላው ደግሞ የሳተላይቶችን ፍጥነት እንዲውም ከኛ ምን ያክል እንደራቁ ይሄንን ቀመረ ተጠቅመን ማግኘት እንችላለን።

share share

@ethiotefer @ethiotefer

@ethiotefer @ethiotefer
90 views17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ