2021-05-10 12:34:17
የመጀመሪያው የጠፈር ጉዞ ና ያልተነገሩ ክስተቶቹ
ዩሪ ጋጋሪን "ይኸው ከዓለም ርቄ ትንሽዬ ኩባያ መሳይ ዕቃ ውስጥ
እገኛለሁ መሬት ሰማያዊ ናት። ምንም ማድረግ አልችልም።"
ይህ ስንኝ የተወሰደው ከድምፃዊ ዴቪድ ቦዊ ዘፈን ነው። ድምፃዊው ዩሪ ጋጋሪን ወደ ጠፈር በተጓዘ ወቅት የተሰማው ይህ ሳይሆን አይቀርም ሲል ነው የገጠመው።
ጋጋሪን ወደ ሕዋ የተጓዘው ሁለት ሜትር ስፋት ባላት መንኮራኩር
ነው። የተጓዘው እንደ ጠፈር ተመራማሪ ሳይሆን እንደ መንገደኛ
ነበር። በወቅቱ መንኮራኩሯ ውስጥ ያሉ ቁልፎችን መነካካት ክልክል ነበር።ያኔ ጋጋሪን ምድር ላይ ካሉ ተቆጣጣሪዎች ጋር ያደረገው ንግግር ተተይቦ ተቀምጧል። ጽሑፉ ጋጋሪን ባየው ነገር ቀልቡ እንደተሰረቀ ያትታል።
ጋጋሪን በፈረንጆቹ ሚያዚያ 12፣1961 ያደረገው ጉዞ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ለሶቪዬት ሕብረት ትልቅ ድል ነበር።
ነገር ግን ታሪክ ለመፃፍ ቆርጦ የተነሳው ጋጋሪን ትልቅ ብርታት
የሚጠይቅ ሥራ ሠራ። ጋጋሪን ጥልቅ ወደሆነው ሚስጢራዊው
ሕዋ ያለማንም እርዳታ ተጓዘ።
ጠፈርተኛው ወደ ሕዋ ያደረገው ጉዞ ብዙ ጥያቄዎችን ለመመለስ
ያቀደ ነበር። አንደኛው ጥያቄ ሰው ሕዋ ላይ መቆየት ይችላል ወይ
የሚለው ነበር።
ሌላኛው ዓላማ መንኩራኩሯ ሕዋ ላይ ምን ያህል መቆየት ትችላለች የሚለውን መፍታት ነው።
የዛኔ መንኮራኩሮች ምን ያህል ደህንነታቸው የተጠበቀ ነው?
ከምድር ጋር ግንኙነት ማድረግ ይቻላል?
የምር ሰዎች ሕዋ ላይ
መቆየት ይችላሉን?
የሚሉት ጥያቄዎች ምላሽ አልነበራቸውም።"ያኔ ጋጋሪን የተወነጨፋባትን መንኮራኩር ለዘንድሮ ሳይንቲስቶች ብናቀርብ ማንም ሰው በዚህች ተስፋ በሌላት መንኮራኩር ለመብረር አይደፍርም" ይላሉ ኢንጅነር ቦሪስ ቼርቶክ። "በወቅቱ ሁሉም ነገር ሰላም ነው ብዬ ብዙ ሰነዶች ላይ
ፈርሚያለሁ። ጉዞው ሊሳካ ይችላል ብዬም ማስረገጫ ሰጥቻለሁ።
አሁን ዞር ብዬ ሳየው ብዙ አደጋ እንደተጋፈጥን ይሰማኛል።" የቮስቶክ ውድቀቶች ቮስቶክ የተሰኘው መንኮራኩር አስተኳሽ መሣሪያ አር-7 በተባለው
ሮኬት ላይ ተመሥርቶ የተሠራ ነው። ሮኬቱ ለመጀመሪያ ጊዜ
የተተኮሰው በፈረንጆቹ 1957 ነበር።
በዛው ዓመት የመጀመሪያው ሰው ሰራሽ ሳተላይት ስፑትኒክ 1
አር-7 ላይ ተመስርቶ ተተኩሶ ነበር። አር-7 አሁንም ሩስያ ወደ ጠፈር ሳይንቲስቶችን ለመላክ
የምትጠቀምበት ሮኬት ነው።
የመጀመሪያው የቮስቶክ ፕሮግራም የተወነጨፈው ግንቦት 1960 ነበር። ይህ ደግሞ ከጋጋሪን ጉዞ አንድ ዓመት ቀደም ብሎ የተካሄደ ነው።
ለመጀመጀሪያ ጊዜ በቮስቶክ አማካይነት የተተኮሰችው ሳተላይት
ከምድር ውጭ መውጣት ብትችልም ባጋጠማት ችግር ምክንያት አልተመለሰችም።
ነሐሴ 19 ቤልካ እና ስትሬልካ የተሰኙት ውሾች ወደ ሕዋ ተላኩ
ጉዟቸውን በስኬት አጠናቀውም ተመለሱ። ይህ በ1960ዎቹ ከተካሄዱ ሙራዎች ብቸኛው ስኬታማ ጉዞ ነበር።
ታኅሣሥ 1 ደግሞ ሌላ ሙከራ ተደረገ። አሁንም ተጓዦቹ ውሾች
ነበሩ ሙሽካ እና ፕቼልካ።
ነገር ግን ይህ ጉዞ ስኬታማ አልነበረም። ውሾቹን የጫነችው
ሳተላይት ስትመለስ ከታቀደላት ቦታ ውጭ በመሄዷ ምክንያት
አየር ላይ እያለች ከነውሾቹ እንድትደመሰስ ተደረገ።
ሶቪዬት ሕብረት ይቺን ሳተላይት ከጥቅም ውጭ ያደረገችው
ቴክኖሎጂዋ ለሌላ አገር ተላልፎ እንዳይሰጥ በመስጋት ነበር።
ሞስኮ ውስጥ የቆመው የዩሪ ጋጋሪን ሐውልት ጋጋሪ ሚያዝያ 12፣1961 ወደ ሕዋ ሲመጥቅ ጉዞው ከሞላ ጎደል ስኬታማ ነበር።
በወቅቱ አጋጥመው ከነበሩ ችግሮች መካከል አንዱ መንኮራኩሯ ከታሰበላት ከፍታ [አልቲትዩድ] በላይ መውጣቷ ነው።
መንኮራኩሯ 'ፍሬን' ባይኖራት ኖሮ ጋጋሪን ማድረግ የሚችለው
ሳተላይቷ በራሷ ጊዜ ወደ ምድር እንድትወርድ መጠበቅ ብቻነው።
ምንም እንኳ ጋጋሪን ከሳምንት በላይ ለሚሆን ጊዜ ምግብና
መጠጥ ይዞ ቢሄድም መንኮራኩሯ ከፍታዋን ጥላ ብትሄድ ኖሮ
ወደ ታች የምትወርደው በራሷ ጊዜ ስለሆነ ምግብና መጠጡ
ላይበቃው ይችል ነበር።
ዕድሜ ለፍሬኑ ጋጋሪን በረሃብ ከመሞት ተርፏል። ሌላኛው ሳተላይቷ የገጠማት ችግር ውስጥ የነበረው ሙቀት
መጠን እጅግ መጨመር ነው። ጋጋሪን ወደ ምድር ሲመለስ
በጣም ይወዛወዝ ስለነበር ራሱን ሊስት ይችል ነበር።
ጋጋሪን ወደ ምድር ሲመለስ መንኮራኩሯ ከምድር ጋር ተላትማ
ከመፈራረሷ በፊት በፓራሹት ወርዶ ነው የተረፈው። አንድ የሕዋ ጉዞ ስኬታማ ነው የሚባለው ጠፈርተኛው መንኮራኩሯ ውስጥ ሆኖ ምድር ላይ ማረፍ ሲችል ነው።
ይህንን ተከትሎ ባለሥልጣናት ጋጋሪን የመጨረሻዎቹን ኪሎ
ሜትሮች ከመንኩራኩሯ ጋር አልተጓዘም በሚል ጉዞው ስኬታማ አልነበረም ብለው ነበር።
ኋላ ላይ ግን በትክክል ተወንጭፎ ምድርን ዞሮ ከነጠፈርተኛው
በመመለሱ የጋጋሪን ጉዞ ስኬታማ ተብሎ እንዲመዘገብ ተደረገ።
ቢቢሲ ሩስኪ፤ ለበርካታ ሩስያዊያን ሳይንቲስቶች ጋጋሪን በተጓዘባት መንኮራኩር ዘንድሮ ትጓዛላችሁ ወይ? ብሎ ላቀረበው ጥያቄ፤ብዙዎቹ ጋጋሪን ያኔ የተጓዘው ስለተጋረጠበት አደጋ ብዙምስላላወቁ ነው ሲሉ መልሰዋል።
የገበሬ ልጅ የሆነው ጋጋሪን ወደ ጠፈር ሲመነጠቅ ማንም
አያውቀውም ነበር። ሲመለስ ግን የምድራችን ታዋቂው ሰው ሆነ።
ጋጋሪን ወደ ምድር ከተመለሰ በኋላ የሶቪዬት ሕብረትን የሕዋ
ፕሮግራም ለማስተዋወቅ ወደ ቼኮስሎቫኪያ፣ቡልጌሪያ፣ፊንላንድ፣
ዩናይትድ ኪንግደም፣ አይስላንድ፣ ኩባ፣ ብራዚል፣ ካናዳ፣ ሃንጋሪና
ሕንድ ተጉዟል።ጋጋሪን በድጋሚ ወደ ሕዋ ሊሄድ ዕቅድ ተይዞለት የነበረ ቢሆንም የአገር ጀግና በመሆኑ ምክንያት እንዳይበር ታግዷል።
ነገር ግን በርካታ ጠፈርተኞችን አሰልጥኗል። ጋጋሪ በ1968 ነበረ በአውሮፕላን አደጋ ምክንያት በ34 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው።
ጀግና አይሞትም!
Via bbc
Share Share
@ethiotefer @ethiotefer
@ethiotefer @ethiotefer
335 viewsedited 09:34