Get Mystery Box with random crypto!

Ethio cyber

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiotefer — Ethio cyber E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiotefer — Ethio cyber
የሰርጥ አድራሻ: @ethiotefer
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 109
የሰርጥ መግለጫ

አላማችን በሳይንስ እና በቴክኖሎጂ የታነፀ ትውልድ መፍጠር ነው።
ሐሳብ አስተያዬት ለመስጠት👇👇👇
@Ethiospace1_bot
@unverseand 👈ለcross

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-25 20:36:18 ​​አውሮፕላኖች አየር ላይ እንዴት ሊንሳፈፉ ቻሉ?

ፕሌኖች አየር ላይ ተንሳፎ ለመሄድ ሁለት ተግዳሮቶች አሉባቸው አንደኛው አየር ላይ ለመንሳፈፈ የመሬት ስበት ይከለክላቸዋል ሁለተኛው ደግሞ ወደ ፊት ለመሄድ ሰበቃ እና የተለያዩ ጋዞች ይከለክላቸዋል የሳይንቲስቶችም ትልቁ ስራ እንዚህን አይሎች በተቀራኒ የሚቋቋም ሐይል መፍጠር ነው ችግሩ እንዴት እንፍጠራቸው የሚለው ነው።

ሳይንቲስቶች በራሪ ነገርን ለመፍጠር ብዙ ዓመታት ጥረት አድርገዋል ልክ እንደ አዋፍትም የሚበሩ መሳሪያዎችን ለመፍጠር ሞክረዋል ነገር ግን አልተሳካም በስመጨረሻ ግን አንድ ነገረ አገኙ የፕሌኖች ከንፍ በአየር ላይ ለመንሳፈፈ ትልቁን ሚና ይጫወታሉ የሚለው ነበር።

ነገሩ እንዲ ነው የፕሌኖችን ክንፍ በትክክለኛው መንገድ ዲዛይን ካደረግነው በዋላ በመሬት ላይ የሚሄድ አንድ ተንቀሳቃሽ ነገር ላይ ብንገጥመው እና እጅግ በፍጠነት ወደፊት ያንን ነገር ማንቀሳቀስ ስንጀምር ወደላይ እንሳፈፍለን የሚለው ሐሳብ ነው።

አስተውላቹ ከሆነ እጅግ በጣም የሚፈጥን መኪና ውስጥ ሁናቹ ስትሄዱ ከፍተኛ የሆነ ንፍስ በአጠገባቹ ሲሄድ ይታወቃቹዋል የፕሌኖቹ ክንፍምም ይሄንን ንፍስ ወደ ፊት እንዳይሄድ በማገድ ወደ ታች ይገፈዋል በዚህ ወቅት "action reaction " በሚለው የፊዚክስ ሕግ መሰረት ፕሌኑ ይንሳፈፍል በዚህ ሕግ መሰረት አንድነ ነገረ ወደታች ከገፍቹት እሱም በተመሳሳይ ሐይል ወደላይ ይገፍቹዋል ለዚህም ነው ክንፎቹ ንፍሱን ወደታች የሚገፉት።

በአሁኑ ዘመን ያሉ ፕሌኖችም ለተወሰኑ ደቂቃዎች ያክል በመሬት ላይ እጅግ በፍጥነት ይንቀሳቀሳሉ በዚህ ወቅት የሚፈጠረውን ንፍስ በመጠቀም ደግሞ የፕሌኑ ክንፍ ንፍሱን ወደ ታች ይገፈዋል በዚህ ወቅት ፕሌኑ አየር ላይ ይነሳፈፍል ፕሌኖችም መንደርደሪያ ያሰፈለጋቸው ለዚህው ነው

በነገራችን ላይ አንድ ፈጣን መኪና ብትኖሯቹ እና ከላዮ ላይ ትክክለኛውን ቅርፅ የያዘ ክንፍ ሰርታቹ ብትገጥሙላት እና እጅግ በፍጥነት ቀጠ ያለ መንገድ ላይ ብትነዷት ከደቂቂዎች በዋላ አየር ላይ ልትንሳፈፉ ትችላላቹ ነገረ ግን ወዲያው ትወድቃላቹ ለምን ?

ይቀጥላል

ይቀጥል የምትሉ like እና "subscribe"

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1
1.9K views17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 07:22:39
ቮያጀር የተሰኘው እስፔሴ ክራፍት ወደ ጥልቁ ዩንቨረስ የሚደረገው ጉዞ ቀጥሎ ዛሬ እንሆ 45 ዓመቱን አስቆጥሯል።

ልክ በዛሬው ቀን የዛሬ 45 ዓመት በ1977 የናሳ ተቋም "ቮያጀር አንድ" የተሰኘውን እስፔስ ክራፍት ሰለ ሰው ልጆች ታሪክ ይዞ ወደ ጥልቁ ዩንቨረስ እንዲወነጨፍ አድርጎት ነበር እስፔስ ክራፍቱ አሁንም ድርሰ ጉዞ ላይ ሲሆን 45 ዓመታትን በፈጀው ጉዞ ከ25 ቢልዬን በላይ ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጧል በ2037 ከሰው ልጆች ጋር ያላለውን ግኑኝነት ያቋርጣል ይሄም የሚሆነው ከሰው ልጆች በእጅጉን በመራቁ እና ሳይንቲስቶች ከርቀቱ አንፃር መረጃዎችን መለዋወጥ ሰለሚቸገሩ ነው።

እስፔስ ክራፍቱ አላማው ሰለ ሰው ልጆች መረጃዎችን ይዞ ለሌሎች የተለዩ ፍጡሮች ማድረስ ነው ወይም የዚህ ዩንቨረስ ጥግ ላይ ድረስ ይጓዛል ተብሎ ይጠበቃል እስፔስ ክራፍቱ ከ 3000 ዓመት በዋላ ሙሉ ለሙሉ ከኛ ሶላር ሲስተም በመውጣት ወደ ሌላ ሶላር ሲስተም ወይም አዲስ አይነት ፀሐይ ጋር እና ፕላኔት ጋር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል ከብዙ ሚልዬን ዓመታት በዋላ ደግሞ ከኛ ጋላክሲ በመውጣት ጉዞዎን ይቀጥላል በዚህን ጊዜ አደለም የሰው ልጅ መሬት በራሷ ጠፍታ ይሆናል።

አለማችን ድምጥማጧ ቢጠፍ ፀሐይ ብትጠፍ የሰው ልጅ በዚህ አለም ላይ ሰለመኖራቸው ምንም አይነት መረጃ ባይኖር እንኳን ቮያጀር የተሰኘው እስፔስ ክራፍት የሰው ልጆች አሻራቸውን ያሳረፉበት የመጨረሻው ነገረ ሁኖ በዚህ ዩንቨረስ ውስጥ ይቀራል።

አሁንም ጉዞ ላይ ነው ከሽህ ዓመታት በዋላም ጉዞ ላይ ነው ከሚልዬን ዓመታት በዋላም ጉዛ ላይ ነው ከቢልዬን ዓመታት በዋላም እስፔስ ክራፍቱ ጉዞ ላይ ነው ምክንያቱም እየኖረክ ያለከው መጨረሻው የት እንደሆን የማይታወቅ ዩንቨረስ ወይም ጠጉ የት እንደሆነ የማይታወቅ ጥልቅ ዩንቨረስ ውስጥ ሰለሆነ ነው።

Share share
2.4K views04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 21:40:17
አምስት በሰው ልጆች የተገኙ አወዛጋቢ ቅሪት አካላቶች።

በአርኮሎጂስቶች የተገኙት እነዚው ራስ ቅሎች የምን እንደሆኑ በግልፅ አይታወቅም ።

በርግጥ ብዙዎቹ የሰው ልጅ የራስ ቅል ቢመስሉም እንዳልሆኑ ግን ማረጋገጥ ተችሏል ምን አልባትም እኛ የማናቃቸው እና ከሰው ልጆች ጋረ ተቀራራቢ የሆኑ ወይም የኤልያኖች አፅም ይሆን ?

መረጃዎቹ ይቀጥላሉ "like" እና "subscribe"

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13
2.1K views18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 21:38:44
የጊዜ ልዩነት በኢትዮጵያ

በምስራቁ ጫፍ በሚገኘው ኦጋዴን እና በምዕራብ ጫፍ በሚገኘው አኮቦ መካከል የ1639km ልዩነት ያለ ሲሆን በሁለቱ ጫፎች መካከል ደግሞ የአንድ ሰአት ልዩነት አለ ይሄም ማለተ ኦጋዴን ላይ ቀድሞ ይጨልማል ቀድሞ ይነጋል ወይም የአኮቦ ሰአት ከኦጋዴን ሰአት በአንድ ሰአት የተንቀራፈፈ ነው።

ይሁን እንጂ ለአሰራር እንዲያመች ተብሎ ሁለቱም ቦታዎች ላይ ያሉት ሰአቶች የጊዜ ክልላቸው (UTC+03:00) ተደርጓል ወይም አንድ አይነት አቆጣጠር አንዲከተሉ ተደርጓል

ምንጭ - geography of Ethiopia and the Horn

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13
2.1K views18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 20:53:16 የመጨረሻ ክፍል

የብላክኦሎች መጨረሻ ምንድነው?

በዚህ አፅናፍ አለም ውስጥ የሚኖር ማንኛውም ነገረ ጠፊ ነው ብላክኦሎችም ጭምር አንድ ቀን ይሞታሉ ወይም ይጠፍሉ ብላክኦሎች የተለያዩ ነገሮችን ውጠው በማስቀረት እራሳቸውን ያሳድጋሉ ክብደታቸው ደግሞ 100 ቢልዬን እጥፍ የኛን ፀሐይ ሊያክል ይችላል።

እንደ "general relativity " እሳቤ ከሆነ ኮከቦች ወደ ብላክኦል ከተቀየሩ በዋላም መሀል ላይ ያለው ሐይል ወደማል ሁሉን ነገረ መሳብ ወይም ይበልጥ ለማኮማተረ የሚያደርገውን ጥረተ አያቆምም ምንም እንኳን ውጨኛው የብላክኦል ክፍል መጠኑ ባይቀየርም ወይም መኮማተር ባይችልም ነገረ ግን ፕላኔት,ኮከበ ወዘተ እየሳቡ ወደራሳቸው ውስጥ እየከተቱ በሄዱ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ ስፍታቸው እና ክብደታቸው እየጨመረ ይሄዳል።


በ1974 "stephen hawking" የሚባለው ሳይንቲስት አንድ እሳቤን ይፍ አድርጎ ነበረ ይሄም ብላክኦሎች ትናንሽ ጨረሮችን እንደሚያወጡ ብዙዎቹ ጨረሮች ደግሞ "photons" የሚባሉ ነገሮች ናቸው የሚል ነበረ ይሄ ሂደተ "hawking Radiation" በሚል ይታወቃል በዚህም ምክንያት ብላክኦሎች መጠናቸው እየቀነሳል ወይም በእንግልዘኛው "shrink" እያደረጉ ይሄዳሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ መጠናቸው ቀንሶ ቀንሶ አንድ ቀነ እስከመጨረሻው ይጠፍሉ የሚል ሳይንሳዊ ምልከታ ነበረው።

ይሄ ብቻ አደለም ትላልቅ ብላክኦሎች ትንሽ ጨረረ ሲያወጡ ትንንሾቹ ደግሞ በጣም ብዙ ጨረረ ያወጣሉ በዚህም የተነሳ ትናንሽ ብላክኦሎች በፍጥነተ ይጠፍሉ የሚል ሐሳብ ነው።

ይሄንን እሳቤ ሳይንቲስቶች ለማረጋገጠ ብዙ ጥረት አርገው ነበር ይሄ እሳቤ ከተገኘ ከዓመታት በዋል ሳይንቲስቶች ጠፈር ውስጥ "Hawking radiation" መኖሩን አረጋግጠዋል ይሁን እንጂ ይሄንን ጨረረ ከብላክኦል ሲወጣ በቀላሉ አናየውም።

"Hawking radiation" እጅግ ቀርፍፍ ሂደተ ነው በዚህም የተነሳ ብላክኦሎች ሳይጠፉ ለረጅም ዓመታት መኖር ይችላሉ ለምሳሌ የኛን ፀሐይ የሚያክል ብላክኦል 1*10^67( 67 ዜሮ ያለው ቁጥር ) ይሄንን ያክል ዓመተ ሳይጠፍ መኖር ይችላል።

በኛ ጋላክሲ መሀል ያለው ብላክኦል " Sagittarius A*" የሚባል ሲሆን 1*10^84 አመት ይቆያል ሙሉ በሙሉ ሳይጠፍ በጠቃላይ ብላክኦሎች ሳይሞቱ እጅግ በጣም በጣም ብዙ ዓመተ መኖር ይችላሉ።

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13
2.4K viewsedited  17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 20:37:14 ETHIO SCIENCE AND ASTRONOMY pinned Deleted message
17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 20:35:41 ክፍል አምስት

ሰለ ብላክኦል አስገራሚ እውነታዎች እና እሳቤዎች

በዚህ አፅናፍ አለም ውስጥ ከተገኙ ብላክኦሎች መካከለ በክብደቱ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ብላክኦል "NGC 4889"የሚባል ሲሆን በየቀኑ አንድ ኮከብ ይውጣል ወይም ይመገባል ይሄ ብላክኦል በየቀኑ አንድ ኮከበ ይብላ እንጂ በአንድ ሚልዬን አመተ ውስጥ ስፍቱ የሚጨምረው 1% ብቻ ነው
ይሄ ብላክኦል 32 ቢሊዬን እጥፍ ከፀሐይ ይመዝናል

የኛ አፅናፍ አለም(universe) የተፈጠረው ወይም የመጣው ከብላክኦል ነው ምክንያቱም እንደ "bigbang" እሳቤ ይሄ አፅናፍ አለም የተፈጠረው እጅግ ሞቃታማ እና በጣም ከተኮማተረ ወይም ከፍተኛ የሆነ ዴንስቲ(density) ካለው ነገረ ነው ይሄ ማለተ አፅናፍ አለም የተፈጠረው ከ"singularity" ነው ወደሚል ድምዳሜ ይወስዳል
እንደሳይንቲስቶች ግምት በያንዳዱ ብላክኦል ውስጥ ያለው "singularity" ለተለያዩ አፅናፍ አለመ መወለደ ወይም መፈጠሮች ምክንያት ሊሆን ይችላል።

"primordial" የሚባሉት የብላክኦል አይነቶች እጅግ በጣም ትንሽ ሲሆን ምን አልባት አተመን"atom" ሊያክሉ ይችላሉ ወይም ተራራን ሊያክሉ ይችላሉ

አብዛኛው ጋላክሲዎች መሀል ላይ ትላልቅ ብላክኦሎች ወይም አነስ ያሉ ብላክኦሎች አሉ ይሄ ብቻ አደለም ሁሉም ኩዋክብቶች የሚዞሩት በጋላክሲያቸው መሀል ላይ ያለውን ብላክኦል ነው እንደ አንዳድ ሳይንቲስቶች ሀሳብ ብላክኦሎች ከሌሉ ጋላክስ ብሎ ነገረ የለም ወይም ጋላክሲዎች የሚፈጠሩት በብላክኦሎች ምክንያት ነው ይሄም ማለተ ትላልቅ ኮከቦች ሲያረጁ ብላክኦል ይሆናሉ ከዛን ሌሎች ነገሮች ብላክኦሉን ይዞራሉ እንዲውም በዙሪያው የተለያዪ ኳክብቶች፥ ይፈጠራሉ ከዛን ጋላክሲ ይሆናሉ።

ምንም እንኳን ጋላክሲዎች ያለ ብላክኦል አይፈጠሩም ይባል እንጂ "A2261-BCG" የተባለው ጋላክሲ ማሀሉ ላይ ምንም አይነተ ብላክኦል የለውም ለምን እንደሆነ ግን የሚታወቀ ነገረ የለም

እንደ"quantum loop gravity" እሳቤ ብላክኦል ውስጥ ያለው "singularity"ከፍተኛ ዴንሲቲ(density) ስላለው እስፔስታይም እጅጉን በመለጠጡ የተነሳ የዚህ ስፔስታይም መስመሮች እስከወደፊቱ ድረስ ሊለጠጡ ይችላሉ በሌላ አበባል የወደፊቱን ሊያሳዩን ይችላሉ ወይም ወደፊት ሊያስኬዱን ይችላሉ ወይም በእንግልዘኛው "time travel" የምንለው በዚህ ስፍራ ላይ ሊኖር ይችላል ማለትም ለምሳሌ ብላክኦል ውስጥ የገባ ነገረ በገባበተ ቅፅበተ በሌላ ጊዜ ላይ ይከሰታል ወይም ይፈጠራል ምን አልባት አሁን ካለንበተ 1000 ዓመተ በዋላ ወይም በፊት የነበረበት ጊዜ ላይ ሊሆን ይችላል እንዲ አይነቱን ክስተተ በእንግልዘኛው "time travel" ብለን እንጠረዋለነ።

እድሜ ጠገቡ ብላክኦል የተገኘው በአውስትራሪያ ሳይንቲስቶች ሲሆን እድሜ ደግሞ 12.7 ቢልዬን አመተ ነው ይሄ ማለተ አፅናፍ አለም ከተፈጠረ 1 ቢልዬን አመተ በዋላ የተፈጠረ እንደማለተ ነው እንደሚታወቀው ኩዋክብት ወደ ብላክኦል ለመቀየር ቢልዬን አመታት ያስፈልጋቸዋል ሰለዚህ በዚች አጨር ጊዜ ውስጥ እንዴት ኮከብ ወደ ብላክኦል ተቀየረ የሚለውን መልስ መስጠት የተቸገሩት ሳይንቲስቶች አፅናፍ አለም እንደተፈጠረ አብረው የተፈጠሩ ብላክኦሎች አሉ ወደሚል ድምዳሜ እንዲመጡ ያስገደደ ግኝተ ነው ይሄ ብላክ ኦል 8000 እጥፍ በኛ ካላክሲ መሀል ላይ ያለውን ብላክኦል በክብደተ ይበልጣል።

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13
1.9K viewsedited  17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 20:10:53 ​ክፍል አራት

የብላክኦል ሌላኛው ገፅታ ምን ይመስላል አዲስ አለም ላይ ወይም አፅናፍ አለም ላይ በድንገት ብትከሰቱ ምን ይሰማቹዋል ?

ብላክኦል ውስጥ ምን እተፈጠረ ነው? በሌላኛው ጫፍ ያለው የብላክኦል ክፍል ምንድነው ? የሚሉትን ጥያቄዎች በርግጠኝኘተ መመለስ ባይቻልም ብዙ እሳቤዎች ወይም መላምቶች አሉ።

ለምሳሌ ብላክኦሎች ወደሌላ አፅናፍ አለም(universe) መሄጃ መንገዶች ናቸው የሚለው አንደኛ ነው

ብዙ አፅናፍለ አለሞች ወይም በእንግልዘኛው " multiverse"
የምንለው ነገረስ ይኖር ይሆን?

የኛን አፅናፍ አለም የሚመስል ወይም በእንግልዘኛው "parallel universe" የምንለው ነገረ ይኖር ይሆን?

"muletiverse" እና "parallel universe " ምንድነው ልዩነታቸውስ ?

"parallel universe" የምንለው የኛን አፅናፍ አለም የሚመስል ሲሆን የኛን የሚመስል ፕላኔት የኛን የሚመስል ጋላክሲ,ኮከቦች ወዘተ ያሉበተ ነው ወይም አንቺን, አንተነ ወይም እኔን የሚመስል ሰው ያለበተ አፅናፍ አለም(universe) ነው።

"multiverse" የምንለው ደግሞ አጠቃላይ የአፅናፍአለሞች ስብሰብ ነው ይሄ ማለተ "parallel universe" የምንለውም አዚህ ውሰጥ ይካተታል።

እንደሳይንቲስቶች ግምት ይሄ አፅናፍአለም(universe) በ"bigbang" ወቅት ሲፈጠረ ሌሎች ይሄንን የሚመስሉ አፅናፍ አለሞቸ ተፈጥሮል የሚል ነው አንደ እስቢያቸው ከሆነ ማለቂያ የለሽ አፅናፍአለሞች ወይም በእንግልዘኛው (infinite universe) ተፈጥረዋል የሚል ምልከታ አለ።

የሆነው ሁኖ ብላክኦል ምንድነው ተፅኖው በዚህ "multiverse" ውስጥ።

ብላክኦል ወደተለያዩ አፅናፍአለሞች መሄጃ መንገድ ነው ወይም በተቃራኒ በኩል ያለው የብላክኦል ቀዳዳ ወደሌላ አፅናፍአለም ይወስዳሉ የሚል ምልከታ ነው ያለው ይሄ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ አፅናፍአለሞችን የሚያስተሳስር ብቸኛው ነገረ ሊሆን ይችላል የሚል እሳቤ ነው ያለው ሰለዚህ ወደተለያዩ አፅናፍ አለማት ብላክኦልን ተጠቅመን መሄድ እንችላለን ማለት ነው ወይም ብላክኦል ውስጥ ሰምጠን ሳይሆን የምንቀረው ሌላ አፅናፍ አለም ላይ ነው የምንፈጠረው እንደማለት ነው።

"parallel universe","multiverse" እንዲውም ብላክኦል ወደሌሎች ዩኒቨርስዎች መውሰጃ መንገድ ነው የሚሉት ሐሳቦች በሳይንቲስቶች ይነገር እንጂ ምንም አይነተ ሳይንሳዊ ማስረጃ የላቸውም ወይም ሳይንሳዊ ግምቶች ናቸው።

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13
1.6K viewsedited  17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 19:43:43
ክፍል ሶስት

የብላክኦል የመጀመሪያው ምስል

ሳይንቲስቶች ለመጀመሪያ ጊዜ የብላክኦልን ምስል ለአለም ሕዝብ በ2018 ይፍ ሲያረጉት ምስሉ ላይ እንደምታዩት ይመስል ነበረ።

ብላክኦልን ከርቀተ ሆነ ማየተ አየቻልም ነገረ ግን "event horizon" ከሚባሉ የብላኮኦል ክፍል ውጭ ያለውን ነገረ ግን ማየት ይቻላል።
ብርሃንን እንዲውም "x rays" ጨምሮ ማንኛውም ነገረ ከብላክኦል ማምለጠ አይችልም ወይም አንዴ "event horizon" ከሚባለው የብላክኦል አከባቢ አልፎ ከገባ መውጣት አይችልም ይሄ ማለተ ብላክኦል ውስጡ ምን እንደሚመስል ማየት አይቻልም ወይም መመራመር አንችልም።

የናሳ ቴሌስኮፖችም ማጥናት የሚችሉት ከብላክኦል ዙሪያ "event horizon " ከሚባለው ቦት በቅርበተ ያሉትን ነገሮች ብቻ ነው እዚህ አከባቢ ያለው ማንኛውም ነገረ በሚልዬን ሰኔትግሬድ ይሞቃል በብላክኦሉ ስበተ ምክንያት ይሄም ነገረ "x-ray" ጨረረ ይለቃል። ሌላው ደግሞ ብላክኦል እራሱ ያለበትን አከባቢ ያኮማትረዋል።

ምንም እንኳን ብላክኦልን በተለመደው ቴሌስኮፕ መመልከት ባይቻልም በስበቱ ምክንያት የሚፈጥረውን ተፅኖ በረቀቁ ቴሌስኮፖች ማይት ይችላል።

ምስሉ ላይ የምናየው ብላክ ኦል M87 ከተባለ ጋላክሲ መሀል ላይ የሚገኘ ሲሆን ክብደቱ የኛን ፀሐይ 6.5 ቢልዬን እጥፍ ይሆናል፣

ይሄንን ምስል ማግኘተ የተቻለው "event horizon" በተባለ ቴሌስኮፖ በመጠቀመ እንዲውም ስምንት የራዲኦ(radio) ተሌስኮፖችን በማቀናጀተ የተገኘ አስገራሚ ምስል ነው።

ይቀጥላል....

share share

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13
1.6K viewsedited  16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 19:26:48 ​ክፍል ሁለት

ብላክኦል ምንድነው?

ማንኛውም ነገረ ስፍቱ(radius) ከ"schwarzschild radius" ካነሰ ብላክኦል ይባላል ወይም ማንኛውም ነገረ ከሆነ ቦታ ላይ ጥሶ ለመውጣት ከብርሃን ፈጥነተ በላይ መፍጠን የሚያስፈልገው ከሆነ ያ አከባቢ ብላክኦል ነው።

ብላክ ኦል የሚጨበጠ ወይም የሚዳሰሰ ነገረ አደለም ልክ እንደኳስ የሚመስል ሲሆን ውስጡ ድቅድቅ ያለ ጨለማ ነው ውስጡ ምን እየተካሄደ እንዳለ የሚታወቀ ነገረ የለም መሀል ላይ ግን "singularity" የሚባለው ነገረ ነው ያለው ከርቀተ ብላክኦል ሲታይ የጦቆረ ነገረ ነው የሚመስለው።

ብላክኦል ሁለተ ክፍሎች ያሉት ሲሆን የመጀመሪያው "event horizon" የምንለው ሲሆነ የአንድ ብላክኦል ዳር ወይም የብላክኦል ወሰኑ የሚያልቅበተ ክፍሉ ነው።

"event horizon" የሚባለው አከባቢ ጊዜ(time) ቁሞ ነው ያለው ወይም ጊዜ ትርጉም የለሸ ነው በዚህ አከባቢ የምንኖር ቢሆን ኑሮ ምንም አይነት የሰውነት እድገት አይኖረንም ወይም ማርጀት ብሎ ነገረ የለም ከዚህ አከባቢ አምልጦ(escape) ለምውጣት በብርሃን ፍጥነተ በላይ መሄድ አለብን ይሄ ደግሞ የሚቻል አደለም ።

"event horizon" የሚባለው አከባቢ የብላክኦል የዳር ክፍሉ ወይም የአንድ ብላክኦል የመጨረሻው ወሰኑ ነው ወደዚህ አከባቢ የሆነ ነገረ ገባ ማለተ ወደ ብላክኦሉ ገባ ማለተ ነው መውጣት ብሎ ነገረ የለም ወደ ሁለተኛው የብላክሆል ክፍል ወደሆነው "singularity" መሄድ ብቻ ነው አማራጩ።

ሁለተኛው የብላክኦል ክፍል "singularity" የሚባለው ነገረ ሲሆነ ሰለዚህ ነገረ ብዙ የሚታወቅ ነገረ የለም።

በ"singularity" እና "event horizon " በሚባሉ የብላክኦል ቦታዎች ያላቸው እርቀተ "schwarzschild radius(R)" ነው ይሄንን እርቀተ

R=2Gm/c*c

በዚህ ቀመር ማግኘተ ይቻላል።

በኛ ጋላክሲ መሀል ያለው ብላክኦል " schwarzschild radius " ሱ ወይም ከ"event horizon" እስከ "singularity " ያለው እርቀተ 12 ሚልዬን ኪሎሜትር ብቻ ነው ሁሉም በኛ ጋላክሲ ውስጥ የሚገኙት ኮከቦች የኛን ፀሐይ ጨምሮ ይሄንን ጋላክሲ ይሽከረከራሉ።

"abell 85 glaxy cluster" የሚባለው ብላክኦለ በአፅናፍ አለመ(universe) ውስጥ ከተገኙ ብላክኦሎች መሀለ ትልቁ የሚባለው ሲሆነ ክብደቱ የኛን ፀሐይ 40ቢልዬን እጥፍ ነው ወይም በኛ ሚልክዌ ጋላክሲ ውስጥ ካሉት ሁለተ ሶስተኛውን የኮከቦች ክብደተ ይሸፍናል

በአፅናፍ አለም ውስጥ ትንሹ የሚባለው ብላክኦል "XTE J1650" የሚባል ሲሆን ክብደቱ የፀሐይን 3.8 እጥፍ ነው።

ይቀጥላል....

share share

@ethiotefer @ethiotefer
@ethiotefer @ethiotefet
1.6K views16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ