Get Mystery Box with random crypto!

ቮያጀር የተሰኘው እስፔሴ ክራፍት ወደ ጥልቁ ዩንቨረስ የሚደረገው ጉዞ ቀጥሎ ዛሬ እንሆ 45 ዓመቱን | Ethio cyber

ቮያጀር የተሰኘው እስፔሴ ክራፍት ወደ ጥልቁ ዩንቨረስ የሚደረገው ጉዞ ቀጥሎ ዛሬ እንሆ 45 ዓመቱን አስቆጥሯል።

ልክ በዛሬው ቀን የዛሬ 45 ዓመት በ1977 የናሳ ተቋም "ቮያጀር አንድ" የተሰኘውን እስፔስ ክራፍት ሰለ ሰው ልጆች ታሪክ ይዞ ወደ ጥልቁ ዩንቨረስ እንዲወነጨፍ አድርጎት ነበር እስፔስ ክራፍቱ አሁንም ድርሰ ጉዞ ላይ ሲሆን 45 ዓመታትን በፈጀው ጉዞ ከ25 ቢልዬን በላይ ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጧል በ2037 ከሰው ልጆች ጋር ያላለውን ግኑኝነት ያቋርጣል ይሄም የሚሆነው ከሰው ልጆች በእጅጉን በመራቁ እና ሳይንቲስቶች ከርቀቱ አንፃር መረጃዎችን መለዋወጥ ሰለሚቸገሩ ነው።

እስፔስ ክራፍቱ አላማው ሰለ ሰው ልጆች መረጃዎችን ይዞ ለሌሎች የተለዩ ፍጡሮች ማድረስ ነው ወይም የዚህ ዩንቨረስ ጥግ ላይ ድረስ ይጓዛል ተብሎ ይጠበቃል እስፔስ ክራፍቱ ከ 3000 ዓመት በዋላ ሙሉ ለሙሉ ከኛ ሶላር ሲስተም በመውጣት ወደ ሌላ ሶላር ሲስተም ወይም አዲስ አይነት ፀሐይ ጋር እና ፕላኔት ጋር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል ከብዙ ሚልዬን ዓመታት በዋላ ደግሞ ከኛ ጋላክሲ በመውጣት ጉዞዎን ይቀጥላል በዚህን ጊዜ አደለም የሰው ልጅ መሬት በራሷ ጠፍታ ይሆናል።

አለማችን ድምጥማጧ ቢጠፍ ፀሐይ ብትጠፍ የሰው ልጅ በዚህ አለም ላይ ሰለመኖራቸው ምንም አይነት መረጃ ባይኖር እንኳን ቮያጀር የተሰኘው እስፔስ ክራፍት የሰው ልጆች አሻራቸውን ያሳረፉበት የመጨረሻው ነገረ ሁኖ በዚህ ዩንቨረስ ውስጥ ይቀራል።

አሁንም ጉዞ ላይ ነው ከሽህ ዓመታት በዋላም ጉዞ ላይ ነው ከሚልዬን ዓመታት በዋላም ጉዛ ላይ ነው ከቢልዬን ዓመታት በዋላም እስፔስ ክራፍቱ ጉዞ ላይ ነው ምክንያቱም እየኖረክ ያለከው መጨረሻው የት እንደሆን የማይታወቅ ዩንቨረስ ወይም ጠጉ የት እንደሆነ የማይታወቅ ጥልቅ ዩንቨረስ ውስጥ ሰለሆነ ነው።

Share share