Get Mystery Box with random crypto!

Ethio cyber

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiotefer — Ethio cyber E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiotefer — Ethio cyber
የሰርጥ አድራሻ: @ethiotefer
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 109
የሰርጥ መግለጫ

አላማችን በሳይንስ እና በቴክኖሎጂ የታነፀ ትውልድ መፍጠር ነው።
ሐሳብ አስተያዬት ለመስጠት👇👇👇
@Ethiospace1_bot
@unverseand 👈ለcross

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2021-11-25 08:34:50 በጊዜ መጓዝ ማለት ምን ማለት ነው ? በዩቲውብ ቪድዮ ለቀናል

በጊዜ ለመጓዝ ሶስት አይነት ዘዴዎች አሉ በቪድዮ ላይ ተብራርተዋል

የዎርም ኦል ቴክኖሎጂ በጊዜ ለመጓዝ ይጠቅመን ይሆን በዚህ ጉዳይ ላይም ሐሳብ ሰተናል

ከይታ መሰወር እንችል ይሆን ?

የወደፊቱ የሰው ልጆች ስልጣኔ ምን ይመስላል ?

ሙሉን ቪድዮ ተመልከቱት "subscrib" እንዳይረሳ



540 views05:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-24 19:46:37 FRESHMAN EXAMS

ከዚህ በፊት ይህን CHANNEL ያውቃሉ?

@freshmanexams

ካላወቁ አሁኑኑ JOIN ብላችሁ ግቡ

ቻናሉ በውስጡ ብዙ ነገር አካትቷል የ11ና 12 ክፍል አጫጭር ኖቶች
የተለያዩ University ጥያቄዎች...


በዚህ ቻናል የሚታገኙት:

የ2012&2013 Fresh Man

MID EXAM
FINAL
COC EXAMS for Med,Eng

ለ11ና 12 ክፍል ተማርዎች በልዩ ሁኔታ የተዘጋጁ አጫጭር ኖቶች

General Facts


Freshman 1st and 2nd semester courses

ትኩስና አዳድስ ዜናዎች
-የዩኒቨርስቲ ጥሪ ማስታወቂያ
-የስራ ቅጥር ማስታወቂያ


Join at and share

@freshmanexams
@freshmanexams
@freshmanexams


@freshmanexams
@freshmanexams
@freshmanexams

@freshmanexams
@freshmanexams

Question or comment below

@freshmanexams12_bot
407 views16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-24 13:40:05
የአልበርት አንስታይን የአንፃራዊት ፅንሰ ሀሳብ ሰነድ በ13 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠ

አልበርት አንስታይን የአንፃራዊነት ፅንሰ ሀሳብ ስሌት ለመቅረፅ ሲሞክር በእጅ ፅሁፍ የሰፈረ ሰነድ በ13 ሚሊዮን ዶላር ተሽጧል።በፓሪስ በሚገኘው የክራይስቲ የጨረታ ቤት ሰነዱ የተሸጠ ሲሆን ዋጋው የሳይንሳዊ ሰነድ ክብረ ወሰን ሰብሯል።

የቲዎሬቲካል ፊዚክስ ሊቃውንት የሆነው አንስታይን ታላቅ ሳይንሳዊ ግኝቱን ከሚያሳዩ ሁለት ወረቀቶች መካከል የተሸጠው ሰነድ አንደኛው ነው።እ.ኤ.አ በ2015 ይህ ንድፈ ሀሳብ ከታተመ በኃላ ስለ ቦታ፣ ጊዜ እና ስበት የሰው ልጅ ያለው ግንዛቤ የቀየረ ሆኗል።


የሂሳብ ቅጂው የተፃፈው በ1913 እና በ1914 መካካል ባለው ጊዜ ውስጥ አንስታይን እና የስዊዘርላንድ ባልደረባው ሚሼል ቤሶ አማካይነት ነው። የአንስታይን በጣም ጥቂት ማስታወሻዎችን የያዘ ሰው እንደመሆኑ የእጅ ፁሁፉ ተገኝቶ ለዚህ መብቃቱ ያልተለመደ ያደርገዋል ሲል የጨረታ ባለሙያው ቪንሰንት ቤሎይ ተናግሯል።

ፅሁፍ በጥቁር እስኪሪብቶ የሰፈረና ንድፈ ሀሳቡን ለማስፈር በተደረገ ጥረት በርካታ ስህተቶች ይታዩበታል።ሰነዱን ማን እንደገዛው ባይገለፅም ባለ 54 ገፅ ስለመሆኑ ይፋ ተደርጓል።

የአንስታይን የአንፃራዊነት ፅንሰ ሀሳብ ስለ ስለ ፕላኔቶች ምህዋርና ስለ አፅናፈ ሰማይ ብርሃን የፈነጠቀ ነበር።ባለፈው ግንቦት ወር በአንስታይን የተፃፈው የንድፍ ሀሳብ ታዋቂው E=mc2 የያዘ ሰነድ በ1.2 ሚሊዮን ዶላር መሸጡ ይታወሳል። #ዳጉ_ጆርናል

atc news

የዩቲውብ ቻናላችንን subscribe ለማድረግ ወይም የለቀቅናቸውን ቪዲዮዎች ማየት ለምትፈልጉ በዚህ ሊንክ ታገኙታላቹ

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1
725 viewsedited  10:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-23 19:58:23
ምንድነው እየቀረፀ ያለው ?

ለምንስ በወታደሮች ይጠበቃል ?

ለምንስ ይደብቁናል እኛ የማናቀው ነገረ ይኖር ይሆን

share share

@ethioufo

@ethioufo
906 views16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-23 19:27:42 ሰለ ፀሐይ ግርዶሽ ዩቲወብ ላይ ቪድዮ ለቀናል

የፀሐይ ግርዶሽ መች መች ይታያል ?

ሙሉ የፀሐይ ግርዶሽ እንዴት ይፈጠራሉ ?

በኢትዮጵያ የፀሐይ ግርዶሽ መች ይታያል ?

ከ600 ሚልዬን ዓመት በዋላ ሙሉ የፀሐይ ግርዶሽ አይፈጠርም ለምን ?

"the general relative " የተሰኘዉ የአልበርት አንስታይን ንድፈ ሐሳብ እንዴት በጨረቃ ገርዶሽ ወቅት ሳይንሳዊ መሆኑ ተረጋገጠ ?

ሙሉን ቪዲዮ በማየት በቂ የሆነ መረጃ ታገኛላቹ "subscribe" እንዳይረሳ



962 viewsedited  16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-22 21:34:11
በ2020 ብቻ ከ500 ሺህ በላይ ሰዎች ዱካቸውን እንኳን ማግኘት ሳይቻል ደብዛቸው እንደጠፋ FBI አስታውቋል።

እነዚ ግለሰቦች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በሀገረ አሜሪካ ወደሚገኘው "Devil Head" ተብሎ ወደሚጠራው ስፍራ ለጉብኝት በሄዱበት በዛው ደብዛቸው እንደጠፋ FBI ባደረገው
ጥናት ያረጋገጠ ሲሆን ሞተው ይሆናል ብሎ እንዳይደመድም ከጠፉት ሰዎች ውስጥ ያንዳቸውንም ሬሳ ማግኘት እንዳልቻለ አስታውቋል።

ስፍራው "Devil Head" የሚል ስያሜን ያገኘው አካባቢው ላይ በቅርቡ ርቀት የሚኖሩ ሰዎች ከዚህ በፊት ሰው ያልሆኑ እንግዳ ፍጡራንን በምሽት ተመልክተናል ብለው በተደጋጋሚ ለፖሊሶች ሪፐርት በማድረጋቸው ነው።

የናሳው አነፍናፊ

ሰለ ኤልያኖች በዩቲውብ ለማየት "subscribe" እንዳይረሳ



1.2K viewsedited  18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-22 21:19:18 ​የስትሪንግ ንድፈሀሳብ (String theory)

ይሄ ንድፈሀሳብ የተፈጠረው የአልበርት አንስታይንን ንድፈ ሐሳብ እና የኳንተም ንድፈሀሳብን ለማስታረቅ ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ንድፈሀሳብ ከሁለቱም የተለየ አመለካከት ነው ያለው።

ለምሳሌ በእጃቹ የሚገኘውን ስልክ ዝንብላቹ እስከ መጨረሻው ለሁለት እከፈላቹት ብትሄዱ መጨረሻ ላይ አተምን (atom) ታገኛላቹ ከዚህ በዋላ አትምን ለመከፍፈል ብትሞክሩ ፕሮቶን ኒውትሮን እና ኤሌክትሮን ወደ ሚባሉ ነገሮች ትከፍፍላላቹ ከዚህ በዋላ ሶስቱን ነገሮች መከፈል አይቻልም ነገረ ግን ከቅርብ ዓመታት በዋላ እንዚህንም ኒውትሮን እና ፕሮቶን የሚባሉት ነገሮች ኳርክ(quark) ወደ ሚባሉ ነገሮች መክፈል ተቻለ ከዚስ በዋላ ኳርክን መከፈል ይቻል ይሆን የሚለው የብዞች ጥያቄ ሆነ

የስትሪንግ ንድፈሀሳብ መጣ እና ከዚህ በላይ መክፈል ይቻላል አለ በመቀጠልም የሁሉም ቁሶች መነሻ ወይም ሁሉም ነገሮች የተፈጠሩት ከሚርገበገቡ የሀይል ገመዶች(vibrating strands of energy strings) እንደሆነ ገለፀ።

ስለዚህ የበፊት እውቀታችን
የተገደበው ከአተም ውስጥ ከሚገኙት ፕሮቶን እና ኒውትሮን ያነሱ ኩዋርክ(Quark) የተባሉ ቅንጣቶች ላይ ነበር እነሱ ሲሰባበሩ ደግሞ የሚርገበገቡ ሌላ ስትሪንግ/ ገመድ(string) የተባሉ ሌሎች ቅንጣቶች እንዳሉ አሁን አውቀናል ማለት ነው። የእርግብግቦሹ ቅርፅ የሚነግረን የፓርቲክሉን ባህርይ እንደሆነም ይነግረናል።

እዚህ ንድፈ-ሀሳብ ላይ አንድ ችግር ብቻ አለ። የሚርገበገቡት ገመዶች(vibrating strings) በጣም የቅንጣት ቅንጣት ከመሆናቸው የተነሳ የእውነት መኖራቸውን ለማረጋገጥ የሚረዳ መሳሪያም ሆነ ቴክኖሎጂ አሁን ያለንበት ግዜ የለም። በሳይንስ እይታ ደግሞ የአንድ ነገር መኖር በሙከራ ካልተረጋገጥ ሳይንስ ሳይሆን ፍልስፍና ነው። ስለዚህ ስትሪንግ ንድፈሀሳብ ሳይንስ ሳይሆን ፍልስፍና ሁኖ ቀር

የስትሪንግ ንድፈሀሳብም እንደተጠበቀው ሰለ ዩንቨርስ በቂ የሆነ ነገርን ማቀርብ አልቻለም ሁለቱን ንድፈሐሳቦችንም ማስታረቅ አቃተው የኳንተም ንድፈሐሳብ እና የአልበርት አንስታይን ንድፈሐሳብም እስከዛሬ ሳይዋሀዱ አሉ።

እንደ ስትሪንግ ሀሳብ በዚህ ዩንቨርስ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ነገሮች የሚታዩትም የማይታዩትም ሕይወት ያላቸውም የሌላቸውም የተፈጠሩት ከታች እንደምታዩት በሚመስሉ ነገሮች ነው

የዩቲውብ ቻናላችንን subscribe ለማድረግ ወይም የለቀቅናቸውን ቪዲዮዎች ማየት ለምትፈልጉ በዚህ ሊንክ ታገኙታላቹ

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1
967 viewsedited  18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-22 21:18:52 የኩዋንተም እሳቤ እና የአልበርት አንስታይ ውዝግብ

አልበርት አንስታይን በኩዋንተም መካኒክስ ፅንሰሀሳብ ካልተስማሙ ሰዎች መካከለ አንዱ ነው በተለይ የአንድ ክስተት እውንታ የሚወሰነው በእድሎች ነው የሚለው ሀሳብ አልተዋጠለትም። ለዚያም ነበር "God doesn't play dice on the Universe" ብሎ የተናገረው፤ "ፈጣሪ በስነ- ፍጥረት ላይ ቁማር አይጫወትም" እንደማለት ነው። አንስታይን ይህን ይበል እንጂ የኩዋንተም መካኒክስ ሊቃውንቶች በየግዜው እያገኙዋቸው የመጡት ግኝቶች በግዜው የአንስታይን ንድፈሀሳቦች ስህተት እንደነበሩ ለማሳየት የሚቃጡ ነበሩ።

ነገረ ግን የአንስታይን ጀነራል ሪላቲቪቲ ንድፈ-ሀሳብ በሂሳባዊ ቀመር ተረጋግጦ የተነደፈ በመሆኑ እንከን ሊወጣለት አልቻለም። በሌላ በኩል ደግሞ የኩዋንተም መካኒክስ ተመራማሪዎችም ኤሌክትሮመግነጢሳዊ ሀይልንን እና የኒውክሌር ሀይሎች አዋህደው የነደፉት የንድፈሀሳባቸውን ተጨባጭነት በሂሳባዊ ቀመር አስደግፈው ስላስቀመጡ አዎንታዊ ምላሽ አግኝተዋል። ነገር ግን ሀለቱን ንድፈሀሳቦች እንድ ላይ የሚያዋህድ ተመራማሪ በግዜው አልተገኘም ነበር። ሁለቱም ንድፈሀሳቦች ዩኒቨርሳችን ላይ
ይሰራሉ፤ ከሰሩ ደግሞ የግድ መዋሀድ አለባቸው። የአንስታይን ጀነራል ሪላቲቪቲ የሚሰራው ለግዙፍ አካላት ነው ለፕላኔቶች፣ ለከዋክብት እና ሌሎች ትላልቅ ቁስ አካላት። ኩዋንተም መካኒክስ ደግሞ በብዛት የሚሰራው ለጥቃቅን አካላት ነው፤ አተሞች፣ ፓርቲክሎች ወዘተ... በመሆኑም እነዚህን ሁለት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ የሆኑ ንድፈሀሳቦች ማዋሀድ ፈታኝ ስራ ሆነ።

በ 1933 አልበርት አንስታይን ከጨቁዋኙ የ ጀርመን ናዚ ስርአት በመሸሽ አሜሪካ መጥቶ ፕሪንስተን ዩኒቨርሲቲ ያቁዋረጠውን ትምህርቱን ቀጠለ። ከዩኒቨርሲቲው ብዙም ሳይርቅ በሚኖርበት ቤት ብቻውን በመሆን እነዚህን ሁለት ንድፈሀሳቦች ለማዋሀድ ለአመታት ጣረ። በመጨረሻም በ1955 የማዋሀድ ስራውን ከግብ ሳያደርስ ከዚህ አለም በሞት ተለየ።

ሳይንቲስቶች ሁለቱን ንድፈሀሳቦች የማዋሀዱን ስራ 'ግራንድ ዩኒፊኬሽን'[Grand unification] ብለው ጠሩት። በግዜው የነበሩ አብዛኞቹ የፊዚክስ ሊቆች ሌት ተቀን የሚሰሩት ይህን ሆነ፤ ነገር ግን ጠብ የሚል ጠፋ።

ይህ ከመሆኑ ጥቂት አመታት በፊት (በ1940ዎቹ ውስጥ) የጀርመን ተወላጅ የሆነ ሾሮዲንገር የተባለ የፊዚክስ ሊቅ እጅግ ግዙፍ አካላትን ክብደታቸውን ሳንቀንስ ወደ በጣም አነስተኛ አካላት ማፈግ ብንችል በዙሪያቸው የሚፈጥሩት የስበት ሀይል እጅግ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ የቦታ-ግዜ ድርን (space time fabric) በእድጉ እንደሚያሰረጉዱ በሳይንሳዊ ቀመር አስደግፎ በማስረዳት የአልበርት አንስታይንን ሀሳብ በፅኑ ደግፎ ነበር።

ለዚህ ማረጋገጫ ያስቀመጠው ፀሊም ጉድጉዋዶችን (Black holes) ነበር። ባለፈው እንዳየነው ፀሊም ጉድጉዋዶች የሚፈጠሩት እጅግ ግዙፍ የሆኑ ከዋክብት ሲፈነዱ እንደሆነ ተረድተናል። ማንኛውም ኮከብ ሳይፈነዳ በፊት 2 አይነት ሀይሎች በላዩ ላይ ይኖራሉ። አንዱ ሀይል ከኮከቡ የውስጠኛ ክፍል ውስጥ በሚኖረው የኒውክሌር መብላላት ከውስጥ ወደውጭ የሚገፋ የግፊት ሀይል(Pressure) ሲሆን ሁለተኛው ሀይል ደግሞ በግዜ-ቦታ ስርጉደት ምክንያት ኮከቡን ከውጭ ወደውስጥ የሚገፋው የስበት ሀይል(Gravity) ነው። ሀለቱ ሀይሎች መጠናቸው እኩል እስከሆነ ድረስ(Equilibrum) ኮከቡ በህይወት ይቆያል። ነገር ግን ኮከቡ ውስጡ ያለው የኒውክሌር ሀይል ሲያልቅ በመለጠጥ ይፈነዳል። በዚህ ግዜ የግፊቱ ሀይል ይጠፋና የስበት ሀይል ብቻ ያይላል። ይህ የስበት ሀይል የኮከቡን መሀለኛ አካል(core) በማፈግ ክብደቱን ሳይቀንስ ወደ በጣም ጥቂት ቅንጣት ይቀይረዋል። ከዚህ በሁዋላ በግዜው ለነበሩት ለሁሉም የፊዚክስ ሊቆች አልመለስ ያለ አንድ ጥያቄ ተፈጠረ። የፀሊም ጉድጉዋዱ ወይም ብላክኦል መሀል ላይ የሚሰራው ንድፈሀሳብ ጀነራል ሪላቲቪቲ ነው?
(ግዙፍ ኮከብ በመሆኑ) ወይንስ ኩዋንተም መካኒክስ ነው?(ወደ ቅንጣት ኮከብ በመቀየሩ)።

ሁለቱን ንድፈሀሳቦች አንድ ላይ ማዋሀድ ደግሞ ትርጉም የሌለው ውጤት አመጣ። ዩኒቨርስ ግን ትርጉም አለው በመሆኑም መዋሀድ የግድ ሆነ። ልክ አንድ ቤት ውስጥ እንደሚኖሩ ሁለት የተለያዩ ቤተሰቦች ነገር ግን አውርተውም የማያውቁ ማን ማን እንደሆነም እንደማይተዋወቁ ቤተሰቦች ማለት ናቸው ሁለቱ ንድፈሀሳቦች።

ይህንን ትልቅ ችግር ለመፍታት ነበር ስትሪንግ ንድፈ ሀሳብ(string theory) የተነደፈው።

facebook page

ሰለ እስትሪግ ቲዎሪ በቃጣይ እንፅፍለን

የዩቲውብ ቻናላችንን subscribe ለማድረግ ወይም የለቀቅናቸውን ቪዲዮዎች ማየት ለምትፈልጉ በዚህ ሊንክ ታገኙታላቹ

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1
1.0K views18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-21 10:03:55 ዛሬ በረፍት ቀናቹ ዩቱውብ ላይ ልታዮቸው የሚገቡ ቪድዮዎች "subscrib" እንዳይረሳ

በጊዜ መጓዝ ማለት ምን ማለት ነው ?

በጊዜ ለመጓዝ ሶስት አይነት ዘዴዎች አሉ በቪድዮ ላይ ተብራርተዋል።

የዎርም ኦል ቴክኖሎጂ በጊዜ ለመጓዝ ይጠቅመን ይሆን በዚህ ጉዳይ ላይም ሐሳብ ሰተናል

ከእይታ መሰወር እንችል ይሆን ?

የወደፊቱ የሰው ልጆች ስልጣኔ ምን ይመስላል ?

ሙሉን ቪድዮ ተመልከቱት





2. ሰለ ቀዩ ጨረቃ

በዚህ ቪድዮ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ መቼ እንደሚታይ ጠቅሰናል።

የጨረቃ ግርዶሽ መቼ መቼ እንደሚፈጠር አብራርተናል ?

ከዚህ ክስተት ጋር የተገናኙ ነገሮች የሰው ጅብ, መጠፎ ልጆች መወለድ ወዘተ አይተናል

ቪድዮን ተመልከቱት





3. ጊዜ ምንድነው

የአይዛክ ኒውተን የ ጊዜ ሕሳቤ

የአልበርት አንስታይን የጊዜ ሕሳቤ

በፈጠንን ቁጥር ጊዜ እየቆመ ይሄዳል ለምን ?

የጅፔስ ቴክኖሎጅ የአልበርት አንስታይንን የጊዜ ሕሳቤ ይጠቀማል ለምን ?

ሙሉን ቪድዮ ተመልከቱት







4. ኤልያኖች እና ዩፎዎች

ዩፎዎ እና ኤልያኖች ማለት ምን ማለተ ነው ?

ዩፎች ለምንድነው የሚሰልሉን?

መንግስታቶች ጉዳዩን ለምን ይደብቁናል ?

ኤልያኖች ከየት ነው የሚመጡት?

ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ ምን አይነት ቴክኖሎጂን ይጠቀማሉ?

እንዲውም የተለያዩ ክስተቶች አሉ ሙሉን ቪድዮ ተመልከቱት





5. ብላክ ኦል, ዋይትኦል እና ዎርምኦል

ብላክኦሎች እንዴት ይፈጠራሉ ?

የብላክ ኦል አደገኛነት እንዴት ይገለፃል?

ዎይት ሆሎች እንዴት ይፈጠራል ?

ቢልዬን የብርሃን ዓመት የሚርቁ ቦታዎች ላይ እንዴት መሄድ ይቻላል?

የዎርም ኦል ቴክኖሎጅ ምንድነው ?

ሁሉኑም መረጃዎች እዚህ ያገኛሉ





6. የተለዩ አለማት ላይ የሚኖሩ ፍጥሩች ምን ሊመስሉ ይችላሉ

በሳይንቲስቶች አንደበት

ባለስምንት እግሩ ፍጡር እንዴት ነው የሚንቀሳቀሰው?

ሙሉን ቪድዮ ይመልከቱት





7. ሰለ ዩፎች የተገኙ አሳማኝ የቪድዮ መረጃዎች

የዩፎች የሰውነት አካል ሜክሲኮ ውስጥ....

የመንገድ ካሜራዎች የቀረፁት አስፈሪው ክስተት...

የአሜሪካው ፔንታጎን ይፍ ያደረገው መረጃ....

በሰው ልጆች ላይ የደረሱ ጠለፍዎች....

እንደው ግን ዩፎች የሉም ብሎ መደምደም አይከብድም

ሙሉን ቪድዮ ለማገኝት





8. ከጨረቃ እስከ መሬት ያለውን እርቀት እንዴት መለካት እችላለው

በዚህ ቪድዮ ምን አይነት ዘዴዎች ሳይንቲስቶች እንደሚጠቀሙ ተዳሷል

ይበልጥ ተመራጭ የሆነው የቱ አይነት ዘዴ ነው?

የጨረቃ ግርዶሽ ለልኬቱ አስፈላጊ ነገረ ነው ወይስ አደለም

ከ70 አመታት በፊት አሜሪካ ከጨረቃ አስከ መሬት ያለውን እርቀት የለካችበት ዘዴ ምን አይነት ነበር።

ሙሉን ቪድዮ ለማየት





9. የውሃው አለም እና የሚኖሩበት ፉጡሮች.....

የውሃው አለም ምን የሚያስደነቅ እውነታ አለው።

አኛ የሰው ልጆች የውሃው አለም ላይ መኖር እንችል ይሆን።

የውሃው አለም የኛን አለም ምን ያክል ይበልጣታል

ሙሉን ቪድዮ ለማየት






10. ያለፉት 100 አመታት የተፈጠሩ የጠፈረ ሳይንስ ዋና ዋና ክስተቶች

የጨረቃው ጉዞ.....

አሰቃቂው አደጋ...

የአሜሪካ እና የሩሲያ የጠፈር ፍጥጫ..

የቻይናው ሮከቴ አፍሪካ ውስጥ መከስከሱ....

ሙሉን ቪድዮ ለማየት





11. የፕላኔቶቻችን አስደናቂ እውነታዎች

የኛ አለም ከ20 ቢልዬን ኪሎ ሜተር ላይ ሁነን ስናያት ምን ትመስላለች?

የኛ ሶላር ሲስተም ዕድሜ ስንት ነው?

እጅግ ቀዝቃዛው ቦታ ጨረቃ ላይ ይገኛል ።

ሶላር ሲስተም ማለት ምንድነው

ሙሉን ቪድዮ ለማየት





12. ዳርክ ማተር እና ዳርክ ኢነርጂ ማለት ምን ማለት ነው?

ሚስጥራዊ ሰለሆነው ዳርክ ማተር ሳይንቲስቶች ምን የደረሱበት ውሳኔ አለ።

ዳርክ ኢነርጂ አፅናፍ አለምን ለምን ያሰፍል።

ሁለቱም ነገሮች ለምን ቲዎሪ ብቻ ሁነው ቀሩ።

ሰለመኖራቸው ምን የተገኘ ፍንጭ አለ

ሙሉን ቪድዮ ለማየት






ቻናላችንን ሰብስክራይብ ለማድረግ
https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1
786 views07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-20 19:36:18 ​የኩዋንተም መካኒክስ ፅንሰ-ሀሳብ

እንደ ኩዋንተም እሳቤ ማንኛውም በዩኒቨርስ ላይ የሚከናወን ተግባር እውን ሊሆን የሚችለው በመሆን ወይንም ባለመሆን እድል(Probability ) እንደሆነ ነው። አንድን ተግባር ለማከናወን ስንፈልግ የመሳካት እድሉ አንድ አንድሺኛ(1/1000) ሊሆን ይችላል ወይንም አንድ አንድሚሊዮነኛ(1/ 1000,000) ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ ይህን ፅሁፍ እየፃፍኩ ካለሁበት ቦታ ፊት ለፊት ትልቅ ግድግዳ ይገኛል፤ በግድግዳው ውስጥ አልፌ ቀጥሎ ያለው ከፍል ልገባ ልሞክር ብል የሚያየኝ ሰው 'ይሄ ሰው አብዱዋል' ወይም 'ለይቶለታል በቃ' ነው የሚለኝ።

በኩዋንተም መካኒክስ ንድፈ-ሀሳብ መሰረት ግን ግድግዳውን አልፌ መሄድ እችላለው። ግን የማለፍ እድሌ እጅግ እጅግ በጣም አነስተኛ በመሆኑ ነው በመጀመሪያ ሙከራዬ ማለፍ ያልቻልኩት፤ ምናልባት ለተከታታይ አንድ ሺህ አመታት ሳላቁዋርጥ በግድግዳው ውስጥ ለማለፍ ብሞክር ይሳካልኝ ይሆናል። ግን ይሄም ትልቅ ምናልባት ነው፤ የግዜ ችግር ካልሆነ ግን መሳካቱ አይቀርም።

ኩዋንተም መካኒክስ ሌላ የሚታወቅበት የ ትይዩ ስነፍጥረታት(Paralle Universe) ፅንሰ-ሀሳብ ነው። ይህ ፅንሰ-ሀሳብ እኛ ከምንኖርበት ስነ-ፍጥረት(universe) ውጪ ሌሎች በቢልዮኖች የሚቆጠሩ ስነ- ፍጥረታት እንዳሉ ይነግረናል።

መልቲቨርስ (multiver se) ብለን እንጠራቸዋለን። የእንግሊዘኛ ቃሉን ወስደን ስናየው Universe የሁለት ቃላት ጥምር መሆኑን እንረዳለን። Uni እና Verse፤ Uni 'አንድ' ወይም 'ተነጥላ' ማለት ሲሆን verse ደግሞ ስነፍጥረትን ያመለክታል። አጣምረን ስናነበው 'አንድ ስነ-ፍጥረት' እንደማለት ነው። በዚህ መሰረት multi ማለት 'ከአንድ በላይ' ሲሆን Multiverse 'ከአንድ በላይ ስነ-ፍጥረታት' የሚለውን ትርጉም ይሰጠናል።

በ ትይዩ- ስነፍጥረታት (Paralle l universe) ፅንሰ-ሀሳብ መሰረት በመልክም በቁመትም እኔን የሚመስል ሌላ 'እኔነቴ' በሌላ ዩኒቨርስ ውስጥ ይገኛል። በተግባር ግን የተለያየን ነን።
ለምሳሌ እኔ አንድ ካፌ ውስጥ ገብቼ ቡና ላዝ እችላለሁ፤ ሌላ ዩኒቨርስ ውስጥ ያለው ማንነቴ ግን ሻይ ሊያዝ ይችላል፤ ሌላኛው ዩኒቨርስ ላይ ያለው ደግሞ ወተት ሊያዝ ይችላል። በMultiverse ፅንሰ-ሀሳብ መሰረት ለአንድ ክስተት መፈፀም 1ሺህ እድሎች ካሉ 1ሺውም ይፈፀማሉ፤ ነገር ግን አንድሺውም የሚፈፀሙት በተለያዩ ዩኒቨርሶች ውስጥ ነው። እዛ ካፌ ውስጥ እያለው ብዙ ላዛቸው የምችላቸው ነገሮች አሉ እንደ ቡና፣ ሻይ፣ ወተት፣ ለስላሳ ወዘተ... ስለዚህ እዚህ ያለው ማንነቴ ቡና ካዘዘ ሌላኛው ማንነቴ ሻይ ሌላኛው ወተት ሌላኛው ለስላሳ ወዘተ...እያዘዙ ካፌው ውስጥ ያሉት አማራጮችን ይጣጣሉ ማለት ነው።

በተለያዩ ዩኒቨርሶች ውስጥ የተለያዩ ቁስ አካሎችን አንድ አይነት ባህርይ የማላበስ ሂደት ኩዋንተም ኢንታንግልመንት(Quant um entanglement) ተብሎ የጠራል። በዚህ ሂደት የተያያዙ ሁለት ቅንጣት አካሎችን (Particles ) በመሀከላቸው ምንም ያህል መራራቅ ቢመጣ ባህርያቸው ሊለያይ አይችልም። ይህ እንደ መንትያ ልጆች አርገን ማሰብ እንችላለን። መንትያዎቹ የተለያየ ቦታ ቢሆኑም ከሁለቱ አንዱ የደስታ ስሜት ሲሰማው ሁለተኛው ባለበት ቦታ ሆኖ በማያውቀው ምክንያት የደስታ ስሜት ይሰማዋል። ኩዋንተም ኢንታንግልመንትም ልክ እንደዚሁ ነው።

source - facebook page

የዩቲውብ ቻናላችንን subscribe ለማድረግ ወይም የለቀቅናቸውን ቪዲዮዎች ማየት ለምትፈልጉ በዚህ ሊንክ ታገኙታላቹ

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1
520 viewsedited  16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ