Get Mystery Box with random crypto!

የአልበርት አንስታይን የአንፃራዊት ፅንሰ ሀሳብ ሰነድ በ13 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠ አልበርት አንስ | Ethio cyber

የአልበርት አንስታይን የአንፃራዊት ፅንሰ ሀሳብ ሰነድ በ13 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠ

አልበርት አንስታይን የአንፃራዊነት ፅንሰ ሀሳብ ስሌት ለመቅረፅ ሲሞክር በእጅ ፅሁፍ የሰፈረ ሰነድ በ13 ሚሊዮን ዶላር ተሽጧል።በፓሪስ በሚገኘው የክራይስቲ የጨረታ ቤት ሰነዱ የተሸጠ ሲሆን ዋጋው የሳይንሳዊ ሰነድ ክብረ ወሰን ሰብሯል።

የቲዎሬቲካል ፊዚክስ ሊቃውንት የሆነው አንስታይን ታላቅ ሳይንሳዊ ግኝቱን ከሚያሳዩ ሁለት ወረቀቶች መካከል የተሸጠው ሰነድ አንደኛው ነው።እ.ኤ.አ በ2015 ይህ ንድፈ ሀሳብ ከታተመ በኃላ ስለ ቦታ፣ ጊዜ እና ስበት የሰው ልጅ ያለው ግንዛቤ የቀየረ ሆኗል።


የሂሳብ ቅጂው የተፃፈው በ1913 እና በ1914 መካካል ባለው ጊዜ ውስጥ አንስታይን እና የስዊዘርላንድ ባልደረባው ሚሼል ቤሶ አማካይነት ነው። የአንስታይን በጣም ጥቂት ማስታወሻዎችን የያዘ ሰው እንደመሆኑ የእጅ ፁሁፉ ተገኝቶ ለዚህ መብቃቱ ያልተለመደ ያደርገዋል ሲል የጨረታ ባለሙያው ቪንሰንት ቤሎይ ተናግሯል።

ፅሁፍ በጥቁር እስኪሪብቶ የሰፈረና ንድፈ ሀሳቡን ለማስፈር በተደረገ ጥረት በርካታ ስህተቶች ይታዩበታል።ሰነዱን ማን እንደገዛው ባይገለፅም ባለ 54 ገፅ ስለመሆኑ ይፋ ተደርጓል።

የአንስታይን የአንፃራዊነት ፅንሰ ሀሳብ ስለ ስለ ፕላኔቶች ምህዋርና ስለ አፅናፈ ሰማይ ብርሃን የፈነጠቀ ነበር።ባለፈው ግንቦት ወር በአንስታይን የተፃፈው የንድፍ ሀሳብ ታዋቂው E=mc2 የያዘ ሰነድ በ1.2 ሚሊዮን ዶላር መሸጡ ይታወሳል። #ዳጉ_ጆርናል

atc news

የዩቲውብ ቻናላችንን subscribe ለማድረግ ወይም የለቀቅናቸውን ቪዲዮዎች ማየት ለምትፈልጉ በዚህ ሊንክ ታገኙታላቹ

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1