Get Mystery Box with random crypto!

​የኩዋንተም መካኒክስ ፅንሰ-ሀሳብ እንደ ኩዋንተም እሳቤ ማንኛውም በዩኒቨርስ ላይ የሚከናወን ተግ | Ethio cyber

​የኩዋንተም መካኒክስ ፅንሰ-ሀሳብ

እንደ ኩዋንተም እሳቤ ማንኛውም በዩኒቨርስ ላይ የሚከናወን ተግባር እውን ሊሆን የሚችለው በመሆን ወይንም ባለመሆን እድል(Probability ) እንደሆነ ነው። አንድን ተግባር ለማከናወን ስንፈልግ የመሳካት እድሉ አንድ አንድሺኛ(1/1000) ሊሆን ይችላል ወይንም አንድ አንድሚሊዮነኛ(1/ 1000,000) ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ ይህን ፅሁፍ እየፃፍኩ ካለሁበት ቦታ ፊት ለፊት ትልቅ ግድግዳ ይገኛል፤ በግድግዳው ውስጥ አልፌ ቀጥሎ ያለው ከፍል ልገባ ልሞክር ብል የሚያየኝ ሰው 'ይሄ ሰው አብዱዋል' ወይም 'ለይቶለታል በቃ' ነው የሚለኝ።

በኩዋንተም መካኒክስ ንድፈ-ሀሳብ መሰረት ግን ግድግዳውን አልፌ መሄድ እችላለው። ግን የማለፍ እድሌ እጅግ እጅግ በጣም አነስተኛ በመሆኑ ነው በመጀመሪያ ሙከራዬ ማለፍ ያልቻልኩት፤ ምናልባት ለተከታታይ አንድ ሺህ አመታት ሳላቁዋርጥ በግድግዳው ውስጥ ለማለፍ ብሞክር ይሳካልኝ ይሆናል። ግን ይሄም ትልቅ ምናልባት ነው፤ የግዜ ችግር ካልሆነ ግን መሳካቱ አይቀርም።

ኩዋንተም መካኒክስ ሌላ የሚታወቅበት የ ትይዩ ስነፍጥረታት(Paralle Universe) ፅንሰ-ሀሳብ ነው። ይህ ፅንሰ-ሀሳብ እኛ ከምንኖርበት ስነ-ፍጥረት(universe) ውጪ ሌሎች በቢልዮኖች የሚቆጠሩ ስነ- ፍጥረታት እንዳሉ ይነግረናል።

መልቲቨርስ (multiver se) ብለን እንጠራቸዋለን። የእንግሊዘኛ ቃሉን ወስደን ስናየው Universe የሁለት ቃላት ጥምር መሆኑን እንረዳለን። Uni እና Verse፤ Uni 'አንድ' ወይም 'ተነጥላ' ማለት ሲሆን verse ደግሞ ስነፍጥረትን ያመለክታል። አጣምረን ስናነበው 'አንድ ስነ-ፍጥረት' እንደማለት ነው። በዚህ መሰረት multi ማለት 'ከአንድ በላይ' ሲሆን Multiverse 'ከአንድ በላይ ስነ-ፍጥረታት' የሚለውን ትርጉም ይሰጠናል።

በ ትይዩ- ስነፍጥረታት (Paralle l universe) ፅንሰ-ሀሳብ መሰረት በመልክም በቁመትም እኔን የሚመስል ሌላ 'እኔነቴ' በሌላ ዩኒቨርስ ውስጥ ይገኛል። በተግባር ግን የተለያየን ነን።
ለምሳሌ እኔ አንድ ካፌ ውስጥ ገብቼ ቡና ላዝ እችላለሁ፤ ሌላ ዩኒቨርስ ውስጥ ያለው ማንነቴ ግን ሻይ ሊያዝ ይችላል፤ ሌላኛው ዩኒቨርስ ላይ ያለው ደግሞ ወተት ሊያዝ ይችላል። በMultiverse ፅንሰ-ሀሳብ መሰረት ለአንድ ክስተት መፈፀም 1ሺህ እድሎች ካሉ 1ሺውም ይፈፀማሉ፤ ነገር ግን አንድሺውም የሚፈፀሙት በተለያዩ ዩኒቨርሶች ውስጥ ነው። እዛ ካፌ ውስጥ እያለው ብዙ ላዛቸው የምችላቸው ነገሮች አሉ እንደ ቡና፣ ሻይ፣ ወተት፣ ለስላሳ ወዘተ... ስለዚህ እዚህ ያለው ማንነቴ ቡና ካዘዘ ሌላኛው ማንነቴ ሻይ ሌላኛው ወተት ሌላኛው ለስላሳ ወዘተ...እያዘዙ ካፌው ውስጥ ያሉት አማራጮችን ይጣጣሉ ማለት ነው።

በተለያዩ ዩኒቨርሶች ውስጥ የተለያዩ ቁስ አካሎችን አንድ አይነት ባህርይ የማላበስ ሂደት ኩዋንተም ኢንታንግልመንት(Quant um entanglement) ተብሎ የጠራል። በዚህ ሂደት የተያያዙ ሁለት ቅንጣት አካሎችን (Particles ) በመሀከላቸው ምንም ያህል መራራቅ ቢመጣ ባህርያቸው ሊለያይ አይችልም። ይህ እንደ መንትያ ልጆች አርገን ማሰብ እንችላለን። መንትያዎቹ የተለያየ ቦታ ቢሆኑም ከሁለቱ አንዱ የደስታ ስሜት ሲሰማው ሁለተኛው ባለበት ቦታ ሆኖ በማያውቀው ምክንያት የደስታ ስሜት ይሰማዋል። ኩዋንተም ኢንታንግልመንትም ልክ እንደዚሁ ነው።

source - facebook page

የዩቲውብ ቻናላችንን subscribe ለማድረግ ወይም የለቀቅናቸውን ቪዲዮዎች ማየት ለምትፈልጉ በዚህ ሊንክ ታገኙታላቹ

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1