2021-11-19 19:57:41
ከፀሐይ እስከ መሬት ያለው እርቀት 150,000,000km ነው ይሄንን እርቀት ሳይንቲስቶቹ እንዴት ለኩት ?
ጥንት የሰው ልጆች ከመሬት እስከ ፀሐይ ያለውን እርቀት ለማወቅ ብዙ ጥረቶችን አድረገዋል ብዙዎቹ በቲዎሪ ደረጃ የሄዱበት መንገድ አሪፍ ቢሆንም መጨረሻ ላያ ያገኙት ውጤት ግን ከአሁን ዘመን ልኬት ጋር ባለመገናኘቱ ውድቅ ተደርጓል
ሳይንቲስቶች ትክከለኛውን ልኬት ያደረጉት በ1962 በቀላል ዘዴ ነበር በዚህም ምክንያት ከመሬት እስከ ፀሐይ ያለውን እርቀት ካልኩሌሽኑን ለመስራት የ8ኛ ክፍል ተማሪ መሆነ በቂ ነው
በምስሉ ላይ እንደምታዩት ጨረቃ መሬት እና ፀሐይ 90° ድግሪ ሰርተዋል ወይም ፐርፐንዲኩላር ናቸው ይሄ የሚሆነው ጨረቃ መሬት ላይ ሁና ስትታይ ግማሽ በምትሆንበት ጊዜ ነው
ይሄንን ካልኩሌሽን ለመስራት የሚከተለውን ቀመር ማስታወስ አስፈላጊ ነው
c^2=a^2+b^2 ወይም c*c=a*a+b*b
በምስሉ ላይ እንደተጠቀምነዉ "A" ማለት ከጨረቃ እስከ ፀሐይ ያለው እርቀት ሲሆን በተመሳሳይ "B" ማለት ከመሬት እስከ ጨረቃ ያለው እርቀት ነው "C" ማለት ደግሞ ከፀሐይ እስከ መሬት ወይም እኛ የምንፈልገው እርቀት ነው
ሌላ አንድ ቀመር አስታውሱ
cos = adj/hyp ወይም በኛ cos= b/c
እንደማለት ነው 89.85° የመጣቹ ድግሪ የፀሐይ እና የጨረቃን ጥላ በማስተያየት የተገኘ ልኬት ነው ልኬቱ ምድር ላይ ሰለሆነ ያን ያክል የሚከብድ ነገረ አደለም ያው ለነሱ ማለቴ ነው
ለማንኛውም cos89.538°=0.0043906132
ይሄም ማለት
0.0043906132=b/c
"b" ማለተ ደግሞ ከፀሐይ እስከ ጨረቃ ያለው እርቀት ሲሆን ይሄም 384,400km ነው
ከፀሐይ እስከ መሬት ወይም C=B/cos
C=384,400/0.007277958730
boom!!!
C=152,948,061.329km
ከመሬት እስከ ፀሐይ ያለው እርቀተ 152,948061km ነው ይሄም ከሚታወቀው ቁጥር ጋር ተቀራራቢ ነው
እቤታቹ እራሳቹ እየሰራቹ በደንብ ቼክ አድርጉት
ሌላኛው አማራጭ ፕላኔት ቬኑስን በጨረቃ ቦታ መጠቀም ነው ቬኑስ ምድራችን ላይ ታየች ማለት ቬኑስ, መሬት እና ፀሐይ ከላይ እንዳለው 90° ሰርተዋል ማለት ነው ሰለዚህ ከመሬት እስከ ቬኑስ ያለውን እርቀት ብቻ በመፈለገ ከመሬት እስከ ፀሐይ ያለውን እርቀት ማወቅ ይቻላል።
በቅርቡ በዩቲውብ በስፍት እንመለሳለን እስከዛው "subscribe" አድርጉ ከጨረቃ እስከመሬት ያለው እርቀት እንዴት ተለካ ለምትሉ ደግም ይሄንን ቪድዮ እዩት
509 views16:57