Get Mystery Box with random crypto!

​የስትሪንግ ንድፈሀሳብ (String theory) ይሄ ንድፈሀሳብ የተፈጠረው የአልበርት አንስታይን | Ethio cyber

​የስትሪንግ ንድፈሀሳብ (String theory)

ይሄ ንድፈሀሳብ የተፈጠረው የአልበርት አንስታይንን ንድፈ ሐሳብ እና የኳንተም ንድፈሀሳብን ለማስታረቅ ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ንድፈሀሳብ ከሁለቱም የተለየ አመለካከት ነው ያለው።

ለምሳሌ በእጃቹ የሚገኘውን ስልክ ዝንብላቹ እስከ መጨረሻው ለሁለት እከፈላቹት ብትሄዱ መጨረሻ ላይ አተምን (atom) ታገኛላቹ ከዚህ በዋላ አትምን ለመከፍፈል ብትሞክሩ ፕሮቶን ኒውትሮን እና ኤሌክትሮን ወደ ሚባሉ ነገሮች ትከፍፍላላቹ ከዚህ በዋላ ሶስቱን ነገሮች መከፈል አይቻልም ነገረ ግን ከቅርብ ዓመታት በዋላ እንዚህንም ኒውትሮን እና ፕሮቶን የሚባሉት ነገሮች ኳርክ(quark) ወደ ሚባሉ ነገሮች መክፈል ተቻለ ከዚስ በዋላ ኳርክን መከፈል ይቻል ይሆን የሚለው የብዞች ጥያቄ ሆነ

የስትሪንግ ንድፈሀሳብ መጣ እና ከዚህ በላይ መክፈል ይቻላል አለ በመቀጠልም የሁሉም ቁሶች መነሻ ወይም ሁሉም ነገሮች የተፈጠሩት ከሚርገበገቡ የሀይል ገመዶች(vibrating strands of energy strings) እንደሆነ ገለፀ።

ስለዚህ የበፊት እውቀታችን
የተገደበው ከአተም ውስጥ ከሚገኙት ፕሮቶን እና ኒውትሮን ያነሱ ኩዋርክ(Quark) የተባሉ ቅንጣቶች ላይ ነበር እነሱ ሲሰባበሩ ደግሞ የሚርገበገቡ ሌላ ስትሪንግ/ ገመድ(string) የተባሉ ሌሎች ቅንጣቶች እንዳሉ አሁን አውቀናል ማለት ነው። የእርግብግቦሹ ቅርፅ የሚነግረን የፓርቲክሉን ባህርይ እንደሆነም ይነግረናል።

እዚህ ንድፈ-ሀሳብ ላይ አንድ ችግር ብቻ አለ። የሚርገበገቡት ገመዶች(vibrating strings) በጣም የቅንጣት ቅንጣት ከመሆናቸው የተነሳ የእውነት መኖራቸውን ለማረጋገጥ የሚረዳ መሳሪያም ሆነ ቴክኖሎጂ አሁን ያለንበት ግዜ የለም። በሳይንስ እይታ ደግሞ የአንድ ነገር መኖር በሙከራ ካልተረጋገጥ ሳይንስ ሳይሆን ፍልስፍና ነው። ስለዚህ ስትሪንግ ንድፈሀሳብ ሳይንስ ሳይሆን ፍልስፍና ሁኖ ቀር

የስትሪንግ ንድፈሀሳብም እንደተጠበቀው ሰለ ዩንቨርስ በቂ የሆነ ነገርን ማቀርብ አልቻለም ሁለቱን ንድፈሐሳቦችንም ማስታረቅ አቃተው የኳንተም ንድፈሐሳብ እና የአልበርት አንስታይን ንድፈሐሳብም እስከዛሬ ሳይዋሀዱ አሉ።

እንደ ስትሪንግ ሀሳብ በዚህ ዩንቨርስ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ነገሮች የሚታዩትም የማይታዩትም ሕይወት ያላቸውም የሌላቸውም የተፈጠሩት ከታች እንደምታዩት በሚመስሉ ነገሮች ነው

የዩቲውብ ቻናላችንን subscribe ለማድረግ ወይም የለቀቅናቸውን ቪዲዮዎች ማየት ለምትፈልጉ በዚህ ሊንክ ታገኙታላቹ

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1