Get Mystery Box with random crypto!

የኩዋንተም እሳቤ እና የአልበርት አንስታይ ውዝግብ አልበርት አንስታይን በኩዋንተም መካኒክስ ፅ | Ethio cyber

የኩዋንተም እሳቤ እና የአልበርት አንስታይ ውዝግብ

አልበርት አንስታይን በኩዋንተም መካኒክስ ፅንሰሀሳብ ካልተስማሙ ሰዎች መካከለ አንዱ ነው በተለይ የአንድ ክስተት እውንታ የሚወሰነው በእድሎች ነው የሚለው ሀሳብ አልተዋጠለትም። ለዚያም ነበር "God doesn't play dice on the Universe" ብሎ የተናገረው፤ "ፈጣሪ በስነ- ፍጥረት ላይ ቁማር አይጫወትም" እንደማለት ነው። አንስታይን ይህን ይበል እንጂ የኩዋንተም መካኒክስ ሊቃውንቶች በየግዜው እያገኙዋቸው የመጡት ግኝቶች በግዜው የአንስታይን ንድፈሀሳቦች ስህተት እንደነበሩ ለማሳየት የሚቃጡ ነበሩ።

ነገረ ግን የአንስታይን ጀነራል ሪላቲቪቲ ንድፈ-ሀሳብ በሂሳባዊ ቀመር ተረጋግጦ የተነደፈ በመሆኑ እንከን ሊወጣለት አልቻለም። በሌላ በኩል ደግሞ የኩዋንተም መካኒክስ ተመራማሪዎችም ኤሌክትሮመግነጢሳዊ ሀይልንን እና የኒውክሌር ሀይሎች አዋህደው የነደፉት የንድፈሀሳባቸውን ተጨባጭነት በሂሳባዊ ቀመር አስደግፈው ስላስቀመጡ አዎንታዊ ምላሽ አግኝተዋል። ነገር ግን ሀለቱን ንድፈሀሳቦች እንድ ላይ የሚያዋህድ ተመራማሪ በግዜው አልተገኘም ነበር። ሁለቱም ንድፈሀሳቦች ዩኒቨርሳችን ላይ
ይሰራሉ፤ ከሰሩ ደግሞ የግድ መዋሀድ አለባቸው። የአንስታይን ጀነራል ሪላቲቪቲ የሚሰራው ለግዙፍ አካላት ነው ለፕላኔቶች፣ ለከዋክብት እና ሌሎች ትላልቅ ቁስ አካላት። ኩዋንተም መካኒክስ ደግሞ በብዛት የሚሰራው ለጥቃቅን አካላት ነው፤ አተሞች፣ ፓርቲክሎች ወዘተ... በመሆኑም እነዚህን ሁለት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ የሆኑ ንድፈሀሳቦች ማዋሀድ ፈታኝ ስራ ሆነ።

በ 1933 አልበርት አንስታይን ከጨቁዋኙ የ ጀርመን ናዚ ስርአት በመሸሽ አሜሪካ መጥቶ ፕሪንስተን ዩኒቨርሲቲ ያቁዋረጠውን ትምህርቱን ቀጠለ። ከዩኒቨርሲቲው ብዙም ሳይርቅ በሚኖርበት ቤት ብቻውን በመሆን እነዚህን ሁለት ንድፈሀሳቦች ለማዋሀድ ለአመታት ጣረ። በመጨረሻም በ1955 የማዋሀድ ስራውን ከግብ ሳያደርስ ከዚህ አለም በሞት ተለየ።

ሳይንቲስቶች ሁለቱን ንድፈሀሳቦች የማዋሀዱን ስራ 'ግራንድ ዩኒፊኬሽን'[Grand unification] ብለው ጠሩት። በግዜው የነበሩ አብዛኞቹ የፊዚክስ ሊቆች ሌት ተቀን የሚሰሩት ይህን ሆነ፤ ነገር ግን ጠብ የሚል ጠፋ።

ይህ ከመሆኑ ጥቂት አመታት በፊት (በ1940ዎቹ ውስጥ) የጀርመን ተወላጅ የሆነ ሾሮዲንገር የተባለ የፊዚክስ ሊቅ እጅግ ግዙፍ አካላትን ክብደታቸውን ሳንቀንስ ወደ በጣም አነስተኛ አካላት ማፈግ ብንችል በዙሪያቸው የሚፈጥሩት የስበት ሀይል እጅግ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ የቦታ-ግዜ ድርን (space time fabric) በእድጉ እንደሚያሰረጉዱ በሳይንሳዊ ቀመር አስደግፎ በማስረዳት የአልበርት አንስታይንን ሀሳብ በፅኑ ደግፎ ነበር።

ለዚህ ማረጋገጫ ያስቀመጠው ፀሊም ጉድጉዋዶችን (Black holes) ነበር። ባለፈው እንዳየነው ፀሊም ጉድጉዋዶች የሚፈጠሩት እጅግ ግዙፍ የሆኑ ከዋክብት ሲፈነዱ እንደሆነ ተረድተናል። ማንኛውም ኮከብ ሳይፈነዳ በፊት 2 አይነት ሀይሎች በላዩ ላይ ይኖራሉ። አንዱ ሀይል ከኮከቡ የውስጠኛ ክፍል ውስጥ በሚኖረው የኒውክሌር መብላላት ከውስጥ ወደውጭ የሚገፋ የግፊት ሀይል(Pressure) ሲሆን ሁለተኛው ሀይል ደግሞ በግዜ-ቦታ ስርጉደት ምክንያት ኮከቡን ከውጭ ወደውስጥ የሚገፋው የስበት ሀይል(Gravity) ነው። ሀለቱ ሀይሎች መጠናቸው እኩል እስከሆነ ድረስ(Equilibrum) ኮከቡ በህይወት ይቆያል። ነገር ግን ኮከቡ ውስጡ ያለው የኒውክሌር ሀይል ሲያልቅ በመለጠጥ ይፈነዳል። በዚህ ግዜ የግፊቱ ሀይል ይጠፋና የስበት ሀይል ብቻ ያይላል። ይህ የስበት ሀይል የኮከቡን መሀለኛ አካል(core) በማፈግ ክብደቱን ሳይቀንስ ወደ በጣም ጥቂት ቅንጣት ይቀይረዋል። ከዚህ በሁዋላ በግዜው ለነበሩት ለሁሉም የፊዚክስ ሊቆች አልመለስ ያለ አንድ ጥያቄ ተፈጠረ። የፀሊም ጉድጉዋዱ ወይም ብላክኦል መሀል ላይ የሚሰራው ንድፈሀሳብ ጀነራል ሪላቲቪቲ ነው?
(ግዙፍ ኮከብ በመሆኑ) ወይንስ ኩዋንተም መካኒክስ ነው?(ወደ ቅንጣት ኮከብ በመቀየሩ)።

ሁለቱን ንድፈሀሳቦች አንድ ላይ ማዋሀድ ደግሞ ትርጉም የሌለው ውጤት አመጣ። ዩኒቨርስ ግን ትርጉም አለው በመሆኑም መዋሀድ የግድ ሆነ። ልክ አንድ ቤት ውስጥ እንደሚኖሩ ሁለት የተለያዩ ቤተሰቦች ነገር ግን አውርተውም የማያውቁ ማን ማን እንደሆነም እንደማይተዋወቁ ቤተሰቦች ማለት ናቸው ሁለቱ ንድፈሀሳቦች።

ይህንን ትልቅ ችግር ለመፍታት ነበር ስትሪንግ ንድፈ ሀሳብ(string theory) የተነደፈው።

facebook page

ሰለ እስትሪግ ቲዎሪ በቃጣይ እንፅፍለን

የዩቲውብ ቻናላችንን subscribe ለማድረግ ወይም የለቀቅናቸውን ቪዲዮዎች ማየት ለምትፈልጉ በዚህ ሊንክ ታገኙታላቹ

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1