Get Mystery Box with random crypto!

​ክፍል አራት የብላክኦል ሌላኛው ገፅታ ምን ይመስላል አዲስ አለም ላይ ወይም አፅናፍ አለም ላይ | Ethio cyber

​ክፍል አራት

የብላክኦል ሌላኛው ገፅታ ምን ይመስላል አዲስ አለም ላይ ወይም አፅናፍ አለም ላይ በድንገት ብትከሰቱ ምን ይሰማቹዋል ?

ብላክኦል ውስጥ ምን እተፈጠረ ነው? በሌላኛው ጫፍ ያለው የብላክኦል ክፍል ምንድነው ? የሚሉትን ጥያቄዎች በርግጠኝኘተ መመለስ ባይቻልም ብዙ እሳቤዎች ወይም መላምቶች አሉ።

ለምሳሌ ብላክኦሎች ወደሌላ አፅናፍ አለም(universe) መሄጃ መንገዶች ናቸው የሚለው አንደኛ ነው

ብዙ አፅናፍለ አለሞች ወይም በእንግልዘኛው " multiverse"
የምንለው ነገረስ ይኖር ይሆን?

የኛን አፅናፍ አለም የሚመስል ወይም በእንግልዘኛው "parallel universe" የምንለው ነገረ ይኖር ይሆን?

"muletiverse" እና "parallel universe " ምንድነው ልዩነታቸውስ ?

"parallel universe" የምንለው የኛን አፅናፍ አለም የሚመስል ሲሆን የኛን የሚመስል ፕላኔት የኛን የሚመስል ጋላክሲ,ኮከቦች ወዘተ ያሉበተ ነው ወይም አንቺን, አንተነ ወይም እኔን የሚመስል ሰው ያለበተ አፅናፍ አለም(universe) ነው።

"multiverse" የምንለው ደግሞ አጠቃላይ የአፅናፍአለሞች ስብሰብ ነው ይሄ ማለተ "parallel universe" የምንለውም አዚህ ውሰጥ ይካተታል።

እንደሳይንቲስቶች ግምት ይሄ አፅናፍአለም(universe) በ"bigbang" ወቅት ሲፈጠረ ሌሎች ይሄንን የሚመስሉ አፅናፍ አለሞቸ ተፈጥሮል የሚል ነው አንደ እስቢያቸው ከሆነ ማለቂያ የለሽ አፅናፍአለሞች ወይም በእንግልዘኛው (infinite universe) ተፈጥረዋል የሚል ምልከታ አለ።

የሆነው ሁኖ ብላክኦል ምንድነው ተፅኖው በዚህ "multiverse" ውስጥ።

ብላክኦል ወደተለያዩ አፅናፍአለሞች መሄጃ መንገድ ነው ወይም በተቃራኒ በኩል ያለው የብላክኦል ቀዳዳ ወደሌላ አፅናፍአለም ይወስዳሉ የሚል ምልከታ ነው ያለው ይሄ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ አፅናፍአለሞችን የሚያስተሳስር ብቸኛው ነገረ ሊሆን ይችላል የሚል እሳቤ ነው ያለው ሰለዚህ ወደተለያዩ አፅናፍ አለማት ብላክኦልን ተጠቅመን መሄድ እንችላለን ማለት ነው ወይም ብላክኦል ውስጥ ሰምጠን ሳይሆን የምንቀረው ሌላ አፅናፍ አለም ላይ ነው የምንፈጠረው እንደማለት ነው።

"parallel universe","multiverse" እንዲውም ብላክኦል ወደሌሎች ዩኒቨርስዎች መውሰጃ መንገድ ነው የሚሉት ሐሳቦች በሳይንቲስቶች ይነገር እንጂ ምንም አይነተ ሳይንሳዊ ማስረጃ የላቸውም ወይም ሳይንሳዊ ግምቶች ናቸው።

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13