Get Mystery Box with random crypto!

ክፍል አምስት ሰለ ብላክኦል አስገራሚ እውነታዎች እና እሳቤዎች በዚህ አፅናፍ አለም ውስጥ ከተገ | Ethio cyber

ክፍል አምስት

ሰለ ብላክኦል አስገራሚ እውነታዎች እና እሳቤዎች

በዚህ አፅናፍ አለም ውስጥ ከተገኙ ብላክኦሎች መካከለ በክብደቱ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ብላክኦል "NGC 4889"የሚባል ሲሆን በየቀኑ አንድ ኮከብ ይውጣል ወይም ይመገባል ይሄ ብላክኦል በየቀኑ አንድ ኮከበ ይብላ እንጂ በአንድ ሚልዬን አመተ ውስጥ ስፍቱ የሚጨምረው 1% ብቻ ነው
ይሄ ብላክኦል 32 ቢሊዬን እጥፍ ከፀሐይ ይመዝናል

የኛ አፅናፍ አለም(universe) የተፈጠረው ወይም የመጣው ከብላክኦል ነው ምክንያቱም እንደ "bigbang" እሳቤ ይሄ አፅናፍ አለም የተፈጠረው እጅግ ሞቃታማ እና በጣም ከተኮማተረ ወይም ከፍተኛ የሆነ ዴንስቲ(density) ካለው ነገረ ነው ይሄ ማለተ አፅናፍ አለም የተፈጠረው ከ"singularity" ነው ወደሚል ድምዳሜ ይወስዳል
እንደሳይንቲስቶች ግምት በያንዳዱ ብላክኦል ውስጥ ያለው "singularity" ለተለያዩ አፅናፍ አለመ መወለደ ወይም መፈጠሮች ምክንያት ሊሆን ይችላል።

"primordial" የሚባሉት የብላክኦል አይነቶች እጅግ በጣም ትንሽ ሲሆን ምን አልባት አተመን"atom" ሊያክሉ ይችላሉ ወይም ተራራን ሊያክሉ ይችላሉ

አብዛኛው ጋላክሲዎች መሀል ላይ ትላልቅ ብላክኦሎች ወይም አነስ ያሉ ብላክኦሎች አሉ ይሄ ብቻ አደለም ሁሉም ኩዋክብቶች የሚዞሩት በጋላክሲያቸው መሀል ላይ ያለውን ብላክኦል ነው እንደ አንዳድ ሳይንቲስቶች ሀሳብ ብላክኦሎች ከሌሉ ጋላክስ ብሎ ነገረ የለም ወይም ጋላክሲዎች የሚፈጠሩት በብላክኦሎች ምክንያት ነው ይሄም ማለተ ትላልቅ ኮከቦች ሲያረጁ ብላክኦል ይሆናሉ ከዛን ሌሎች ነገሮች ብላክኦሉን ይዞራሉ እንዲውም በዙሪያው የተለያዪ ኳክብቶች፥ ይፈጠራሉ ከዛን ጋላክሲ ይሆናሉ።

ምንም እንኳን ጋላክሲዎች ያለ ብላክኦል አይፈጠሩም ይባል እንጂ "A2261-BCG" የተባለው ጋላክሲ ማሀሉ ላይ ምንም አይነተ ብላክኦል የለውም ለምን እንደሆነ ግን የሚታወቀ ነገረ የለም

እንደ"quantum loop gravity" እሳቤ ብላክኦል ውስጥ ያለው "singularity"ከፍተኛ ዴንሲቲ(density) ስላለው እስፔስታይም እጅጉን በመለጠጡ የተነሳ የዚህ ስፔስታይም መስመሮች እስከወደፊቱ ድረስ ሊለጠጡ ይችላሉ በሌላ አበባል የወደፊቱን ሊያሳዩን ይችላሉ ወይም ወደፊት ሊያስኬዱን ይችላሉ ወይም በእንግልዘኛው "time travel" የምንለው በዚህ ስፍራ ላይ ሊኖር ይችላል ማለትም ለምሳሌ ብላክኦል ውስጥ የገባ ነገረ በገባበተ ቅፅበተ በሌላ ጊዜ ላይ ይከሰታል ወይም ይፈጠራል ምን አልባት አሁን ካለንበተ 1000 ዓመተ በዋላ ወይም በፊት የነበረበት ጊዜ ላይ ሊሆን ይችላል እንዲ አይነቱን ክስተተ በእንግልዘኛው "time travel" ብለን እንጠረዋለነ።

እድሜ ጠገቡ ብላክኦል የተገኘው በአውስትራሪያ ሳይንቲስቶች ሲሆን እድሜ ደግሞ 12.7 ቢልዬን አመተ ነው ይሄ ማለተ አፅናፍ አለም ከተፈጠረ 1 ቢልዬን አመተ በዋላ የተፈጠረ እንደማለተ ነው እንደሚታወቀው ኩዋክብት ወደ ብላክኦል ለመቀየር ቢልዬን አመታት ያስፈልጋቸዋል ሰለዚህ በዚች አጨር ጊዜ ውስጥ እንዴት ኮከብ ወደ ብላክኦል ተቀየረ የሚለውን መልስ መስጠት የተቸገሩት ሳይንቲስቶች አፅናፍ አለም እንደተፈጠረ አብረው የተፈጠሩ ብላክኦሎች አሉ ወደሚል ድምዳሜ እንዲመጡ ያስገደደ ግኝተ ነው ይሄ ብላክ ኦል 8000 እጥፍ በኛ ካላክሲ መሀል ላይ ያለውን ብላክኦል በክብደተ ይበልጣል።

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13