Get Mystery Box with random crypto!

የመጨረሻ ክፍል የብላክኦሎች መጨረሻ ምንድነው? በዚህ አፅናፍ አለም ውስጥ የሚኖር ማንኛውም ነገ | Ethio cyber

የመጨረሻ ክፍል

የብላክኦሎች መጨረሻ ምንድነው?

በዚህ አፅናፍ አለም ውስጥ የሚኖር ማንኛውም ነገረ ጠፊ ነው ብላክኦሎችም ጭምር አንድ ቀን ይሞታሉ ወይም ይጠፍሉ ብላክኦሎች የተለያዩ ነገሮችን ውጠው በማስቀረት እራሳቸውን ያሳድጋሉ ክብደታቸው ደግሞ 100 ቢልዬን እጥፍ የኛን ፀሐይ ሊያክል ይችላል።

እንደ "general relativity " እሳቤ ከሆነ ኮከቦች ወደ ብላክኦል ከተቀየሩ በዋላም መሀል ላይ ያለው ሐይል ወደማል ሁሉን ነገረ መሳብ ወይም ይበልጥ ለማኮማተረ የሚያደርገውን ጥረተ አያቆምም ምንም እንኳን ውጨኛው የብላክኦል ክፍል መጠኑ ባይቀየርም ወይም መኮማተር ባይችልም ነገረ ግን ፕላኔት,ኮከበ ወዘተ እየሳቡ ወደራሳቸው ውስጥ እየከተቱ በሄዱ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ ስፍታቸው እና ክብደታቸው እየጨመረ ይሄዳል።


በ1974 "stephen hawking" የሚባለው ሳይንቲስት አንድ እሳቤን ይፍ አድርጎ ነበረ ይሄም ብላክኦሎች ትናንሽ ጨረሮችን እንደሚያወጡ ብዙዎቹ ጨረሮች ደግሞ "photons" የሚባሉ ነገሮች ናቸው የሚል ነበረ ይሄ ሂደተ "hawking Radiation" በሚል ይታወቃል በዚህም ምክንያት ብላክኦሎች መጠናቸው እየቀነሳል ወይም በእንግልዘኛው "shrink" እያደረጉ ይሄዳሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ መጠናቸው ቀንሶ ቀንሶ አንድ ቀነ እስከመጨረሻው ይጠፍሉ የሚል ሳይንሳዊ ምልከታ ነበረው።

ይሄ ብቻ አደለም ትላልቅ ብላክኦሎች ትንሽ ጨረረ ሲያወጡ ትንንሾቹ ደግሞ በጣም ብዙ ጨረረ ያወጣሉ በዚህም የተነሳ ትናንሽ ብላክኦሎች በፍጥነተ ይጠፍሉ የሚል ሐሳብ ነው።

ይሄንን እሳቤ ሳይንቲስቶች ለማረጋገጠ ብዙ ጥረት አርገው ነበር ይሄ እሳቤ ከተገኘ ከዓመታት በዋል ሳይንቲስቶች ጠፈር ውስጥ "Hawking radiation" መኖሩን አረጋግጠዋል ይሁን እንጂ ይሄንን ጨረረ ከብላክኦል ሲወጣ በቀላሉ አናየውም።

"Hawking radiation" እጅግ ቀርፍፍ ሂደተ ነው በዚህም የተነሳ ብላክኦሎች ሳይጠፉ ለረጅም ዓመታት መኖር ይችላሉ ለምሳሌ የኛን ፀሐይ የሚያክል ብላክኦል 1*10^67( 67 ዜሮ ያለው ቁጥር ) ይሄንን ያክል ዓመተ ሳይጠፍ መኖር ይችላል።

በኛ ጋላክሲ መሀል ያለው ብላክኦል " Sagittarius A*" የሚባል ሲሆን 1*10^84 አመት ይቆያል ሙሉ በሙሉ ሳይጠፍ በጠቃላይ ብላክኦሎች ሳይሞቱ እጅግ በጣም በጣም ብዙ ዓመተ መኖር ይችላሉ።

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13