2021-12-17 13:55:28
ሰለ ሳተላይት ስልኮች ሊያውቋቸው የሚገቡ እውነታዎች።
የሳተላይት ስልኮች ምንም ኔትወርክ በሌለባቸው አከባቢዎች እንዲውም መሰረት ልማት ያልተሟላባቸው አከባቢዎች ላይ ስልክ መደወል የሚችሉ ስልኮች ናቸው።
የሳተላይት ስልኮች ከ500 ዶላር ጀምሮ ይሸጣሉ በአለም አቀፍ ደረጃ የሳተላይት ስልኮችን የሚያመርቱ እና ወደ ጠፈር ባስወነጨፏቸው ሳተላያት አማካኝነት የደውል አገልግሎት የሚሰጡ ከሶስት በላይ ድርጅቶች ይገኛሉ የሳተላይት ስልኮች በአሁኑ ዘመን የተለያዩ ሰዎች የሚጠቀሟቸው ሲሆን መንግስታቶች እነዚህን ስልኮች በአይን ቁራኝ ይመለከቷቸዋል በዚህም ምክንያት እነዚህን ስልኮች መጠቀመ ከፈለግን በምንኖርበት አገር ውስጥ ላሉ የመንግስት ባለስልጣናት ማሳወቅ ግድ ይለናል።
የሳተላይት ስልኮች ቀጥታ ከሳተላይት ጋር የተገናኙ ሲሆን ኔትወረክ ወጣብኝ ምናምን ብሎ መጨናነቅ የለም ነገረ ግን ይሄንን አገልግሎት የሚያቀርቡት ድርጅቶች በየወሩ የሚያስከፍሉት ገንዘብ የተጋነን እንደሆነ ይነገራል ምን አልባት አንድ ደቂቃ በሳተላይት ስልክ ብታወሩ ብዙ ዶላሮችን ሊያስከፍሏቹ ይችላሉ።
አዘውትረው የሳተላይት ስልኮችን የሚጠቀሙት ቱሪስቶች,የመንግስት ባለስልጣናቶች , አለምአቀፍ ድርጅቶች ,ትላልቅ ሚዲያዎች ወዘተ ናቸው።
በነገራችን ላይ የሳተላይት ስልኮችን ልክ እንደ ጌታቸው እረዳ ወደ ጆሯችን አስጠግተን እንድናወራ አይመከርም
በዩቲውብ በሰፊው እንመለስበታለን እስከዛው "subscribe"
https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1
989 viewsedited 10:55