2021-05-02 15:59:45
ቻይና ቋሚ የህዋ ጣቢያ ለማዋቀር የሚያስችላትን የመጀመርያ ዙር ቁሳቁሶችን ወደ ህዋ ላከች።
ቻይና የመጀመሪያውን ምዕራፍ ቋሚ የህዋ ጣቢያ ለማዋቀር
የሚያስችላትን መንኮራኩር ወደ ህዋ ያመጠቀችው ባለፈው ሐሙስ ነበር
ቻይና ለዚህ ተግባር የሚውል 'ዘ ቲያንሄ' መንኩራኩር ከዌንቻንግ
የህዋ ማስፈንጠሪያ ማዕከል ሎንግ ማርች 5ቢ ዋይ2 ሮኬትን
አምጥቃለች። ቻይና በአውሮፓውያኑ 2022 የራሷ የህዋ ጣቢያ ግንባታን ማጠናቀቅ ትፈልጋለች። በአሁኑ ጊዜ በህዋ ምህዋር ላይ የሚገኝ ብቸኛው ዓለም አቀፍ የህዋ ምርምር ጣቢያ በእንግዝኛ ምሕጻሩ አይኤስኤስ (ISS)
ነው።
ይሁንና ቻይና በዚህ ጣቢያ ውስጥ አልታቀፈችም። ቻይና ወደ ህዋ ሳይንስ አዲስ ገቢ ስትሆን ነገሩን አጥብቃ መያዝ ከጀመረች ሁለት አስርት ዓመት ዓመታት አይሆናትም።
በ2003 (እአአ) ነበር ለመጀመርያ ጊዜ የህዋ ሳይንቲስቷን ወደ
ጠፈር የላከችው። ይህም ከአሜሪካና ከሶቪየት ኅበረት ቀጥሎ የዓለም ሦተኛዋ አገር አድርጓታል።
እስከ አሁን ቻይና ሁለት የህዋ መንኩራኩሮችን ወደ ምህዋር
ልካለች። የመጀመርያው ቲያንጎንግ-አንድ እና ቲያንጎንግ ሁለት
ሲሆኑ እነዚህም ጉዞዎች ለሙከራ ብቻ ስለነበሩ የሕዋ
ተመራማሪዎቹ ያደረጉት ቆእታ አጭር ነበር።
አሁን አዲስ የምትገነባው የህዋ ጣቢያ ቢያንስ ለሚቀጥሉት 10
ዓመታት አገልግሎት የሚሰጥ ነው። ይህ ቤይጂንግ አዲስ የምትገነባው የህዋ ምርምር ጣቢያ ሙሉ ተግባራዊ እስኪሆን ድረስ ቢያንስ 10 የሙከራ ጉዞዎችን እንደምታደርግ ይጠበቃል። ከዚህ የሕዋ ጣቢያ ጉዞ ሌላ ቤይጂንግ ወደ ጨረቃና ማርስ ጉዞን አልማለች። በዓለም ትልቁ የራዲዮ ቴሌስኮፕን ለመትከልም እየሰራች ነው።
የሐሙሱ ከዌንቻንግ የመጠቀው የህዋ ጉዞ የተደረገው ቻይናና
ሩሲያ በጥምረት በፀሐይ ሥርዓት ውስጥ የህዋ ምርምር ማዕከል
ለመግንባት ስምምነት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው።
Via-Bbc amharic
Share Share
@ethiotefer @ethiotefer
@ethiotefer @ethiotefer
235 views12:59