2021-04-22 12:14:43
ናሳ በቅርቡ ወደ ማርስ የላክት "ፐርሰርስረንስ" የተሰኘቹ ሮቨር የማርስን ከባቢ አየር በአስገራሚ ሁኔታ ማፅዳት ጀመረች
የማርስ ከባቢ አየር ከፍተኛ የሆነ የካርቦንዳይኦክሳይድ መጠን እንዳለው ይታወቃል ይሄ ደግሞ ማርስ ህይወት ላላቸው ነገሮች አደገኛ እድትሆን ያደርጋታል በተለየም ለእንስሳት የሰው ልጆች እስከ 2050 ድረስ ማርስን የመቆጣጠረ ወይም ማርስ ላይ የመኖር እቅድ እንዳለ ይታወቃል እናም ማርስን ለመኖር ምቹ ማድረግ የመጀመሪያው ስራችን ይሆናል ናሳ ደግሞ አንድ ብሎ ጀምሮታል
ለመጀመሪያ ጊዜ በማርስ ላይ ኦክስጅንን መፍጠረ የተጀመረው ኤፕሪል 22 ቀን 2021 ሲሆን የናሳ ሮቨርች ደግሞ ትልቅ ድርሻ ይወስዳሉ ናሳም ታሪክ መስራቱን ቀጥሎበታል ፡፡ ባለ ስድስት ጎማ ያላት ሮቨር ከማርስ ከባቢ አየር ውስጥ የተወሰነ ካርቦን ዳይኦክሳይድን ወደ ውስጦ በማስገባት ወደ ኦክስጂን ቀይራዋለች ይሄ ማለተ እቺ ሮቨር ዛፎች በመሬት ላይ የሚሰሩትን ስራ ነው እየሰራች ያለቹው እንደሚታወቀው በኛ ምደር ላይ ካርቦንዳይኦክሳይድን በመሳብ ወደ ኦክስጅን የሚቀዩርት ዛፎች ሲሆን ይሄ ኦክስጅን የተባለው አየር ለእንስሳቶች እንዲውም ለሰው ልጆች አስፈላጊ ወይም መሰረታዊ የሆነ አየረ ነው ይሄንን ስራ በደንብ ከሰራንበት በማርስ ምድር ላይ የሰው ልጆች ያለ መተንፈሻ በነፃነት መተንፈስን ይችላሉ
የናሳ የጠፈር ቴክኖሎጂ ተልእኮ ዳይሬክቶሬት ተባባሪ አስተዳዳሪ ጂም ሬተር በበኩላቸው "ይህ በማርስ ላይ የሚገኘውን ካርቦን ዳይኦክሳይድን ወደ ኦክስጅን መቀየር መቻል ማርስን ህይወት ላላቸው ነገሮች ምቹ የማድረግ ትልቁ እርምጃ ነው" ብለዋል ፡፡
ሂደቱ ለወደፊቱ የጠፈር ተመራማሪዎች እንዲተነፍሱ ለማድረግ ብቻ አደለም ኦክስጅንን የሚመረተው ከማርስ ወደ ምድር ለመመለስም እሮኬቶች የግድ ያስፈልጋቸዋል ይሄ ሮቨር ላይ የተገጠመው ካርቦንዳይኦክሳይድን ወደ ኦክስጅም የሚቀይረው ማሽን " MOXIE " የሚባል ሲሆን የመኪና ባትሪ መጠን ያለው ወርቃማ ሣጥን ነው ይሄ ማሽን በሮቨር ፊት ለፊት በቀኝ በኩል ይገኛል ፡፡
“መካኒካል ዛፍ” ተብሎ የተጠራው በአንድ የካርቦን አቶም እና በሁለት የኦክስጂን አተሞች የተሠሩ የካርቦን ዳይኦክሳይድ ሞለኪውሎችን ለመከፋፈል ኤሌክትሪክ እና ኬሚስትሪ ነው የሚጠቀመው ፡፡ MOXIE በአንደኛው ሩጫ መደበኛ እንቅስቃሴን ለሚያካሂድ ሰው 10 ደቂቃ ያህል ሊተነፍስ የሚችለውን ኦክስጅንን ነው በደቂቃ ውስጥ የሚያመርተው ፡፡ የ MOXIE መሐንዲሶች አሁን ተጨማሪ ሙከራዎችን እያካሄዱ ሲሆን ምርቱን ለማሳደግ እየተሰራ ነው። ነገር ግን አሁን ባለው አሀዝ ማሽኑ በሰዓት እስከ 10 ግራም ኦክስጅንን ማመንጨት እንዲችል ታስቦ ነው የተገጠመ ነው ፡፡
ማርስ 96 % የካርቦን ዳይኦክሳይድ ከባቢ አየር ያላት ሲሆን ኦክስጅንን በኤሌክትሪክ የመፍጠረ ብቻው አማራጭ ነው አሁን ካለን ቴክኖሎጂ አንፃር ፡፡
ይሄ ኦክስጅንን መቀየር የሚችለውን ማሽን የያዘው ሮቨር ትንንሽ ሕይወት ያላቸው ተሕዋስያን በማርስ ምድር ላይ እንዲፈልግ እና ምልክቶችን እንዲያገኝ ተልእኮ ተሰቶት ነበረ በቀይ ፕላኔት ላይ የካቲት 18 ቀን የረፈው፡፡በተመሳሳይ እዚህ ሮቨረ ላይ የተገጠመቹ አነስተኛ ሄሊኮፕተርም በማርስ ምድር ላይ በዚህ ሳምንት ነበረ ለመጀመሪያ ጊዜ በረራ ያደረገቹ ይሄም በሰው ልጆች ታሪክ የመጀመሪው ነው ማለትም በሌላ ፕላኔት ላይ ድሮኖችን ማብረረ መቻል
ሌው ደግሞ ሮቨር ለመጀመሪያ ጊዜ የማርስን ድምፆች በቀጥታ በመቅዳት ወደ ምድራችን በመላክ ማርስ ላይ ያለውን ደምፅ ሰምተናላ ዛሬ ደግሞ ኦክስጅንን መፈጠር ጀምሯል
በማርስ ምድር ላይ ያለውን ካርቦንዳይኦክሳይድ በመቀነስ ወደ ኦክሰሰጅን የመቀየሩ ስራ እና የማርስን ከባቢ አየር የማፅዳት ስራ በትንሹ ስንት አመት ሊፈጅ ይችላል? ግምታቹውን ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን እስኪ
Share Share
@ethiotefer @ethiotefer
@ethiotefer @ethiotefer
320 viewsedited 09:14