2021-05-13 03:06:07
የቻይናው ሮኬት ለምን ወደቀ ?
ቸይና በዚህ ጉዳይ የተብራራ መረጃን ከመስጠት የተቆጠበች ሰለሆነ ለሮኬቱ መውደቅ መንስሄው ይሄ ነው ብሎ መናገር ይከብዳል የሆነው ሁኖ መሬት የደፍው ሓሰብ ወይም የወደቀበትን መክንያትን ግን የዘርፉ ባለሙያዎች በተቻላቸው መጠን ለመገመት ሞክረዋል።
" Escape Velocity " ማለት አንድ ሳተላይት ከምድር ወቶ ወደ ኦርቪት ውስጥ ለመግባት የሚያስፈልገው ፍጥነት ወይም ከምድር ስበት አምልጦ ለመውጣት የመያስፈልግ ፍጥነት ሲሆን ማንኛውም ሮኬት ወደ ሰማይ ሲቶክስ ይሄንን ፍጥነት መጠበቅ ወይም ማሟላት አለበት ይሄም በሰከንድ 11.4km መፍጠነ አለባቸው አለበለዚህ ወደ ምድረ ተመልሰው ይመጣሉ አንደ አንዳዶች ግምት የቻይናው ሮኬት ይሄንን ፈጥነት ጠብቆ እየሄደ ሳለ የተፈለገው ቦታ ላይ ሳይደረስ አንዱ የሮኬቱ ሞተር ስራውን በማቆሙ ምክንያት ከቁጥጥር ውጭ ሳይሆን እንዳልቀር ይገምታሉ
ሁለተኛው እና ከላይ ያልጠቀስነው አንድ ሐይል አለ በርግጥ ሳተላይቶችን ላይ የጎላ ተፀኖ የማያደርግ ቢሆንም ልክ እንደ ISS ላሉ እስቴሽኖች ፈተና ነው ይሄም ሐይል በእንግልዘኛ "drag force" ይባላል ይሄ አይል ምንድነው?
ብዙዎቻችን ሳተላይቶች የሚሽከረከሩበት ቦታ ላይ ምንም አይነት አየር ወይም ጋዝ የለም ብለን እናስባለን ምክንያቱም አይር የሚኖር ከሆነ ሳተላይቶች በጭራሽ በተመሳሳይ ፍጥነት ሊንቀሳቀሱ አይችሉም ምክንያቱም አየር የራሱ አይል አለው ይሄ ሐይል ደግሞ ሳተላይቶች በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ትንሽ የሚባል ተፅኖ ቢያመጣም ከረጅም አመት በዋላ ግን ሳተላይቱን ወደ መሬት ሊጥለው ይችላል ይሄም ምንድነው ከላይ የጠቅሳናቸው ሁለቱ አይሎች እኩል ሰለማይሆን ሳተላይቱ ፍጥነቱት ይቀንሳል ወይም ይጨምራል በዚህ ወቅት "acceleration " ይኖረናል ምክንያቱም " acceleration " ማለት የፍጥነት መቀነስ ወይም በመጨመር የሚገኘ ነገረ ነው ይሄ ማለት ደገሞ "net force " አለ ማለተ ነው ነገረ ግን ይሄ "drag force" ሳተላይቶች ፍጥነታቸው እዲጨምር ሳይሆን እዲቀንሱ ነው የሚያደርገው ምክንያቱም አየር አንድን ነገረ እንዳሄድ የሚከለክል ነገረ ሰለሆነ በርግጥ ጠረፍ ላይ አየር አለ ሲባል ልክ ምድር ላይ እንዳለው አደለም በጣም ትንሽ ነው ነገረ ግን ተፅኖ አላት።
ሳተላይቶች እንዴት ነው ይሄንን
ነገረ ቫላንስ የሚያደርጉት ?
አሁን ሳተላይቶች ቋሚ የሆን ኦርቢት ለምን እንደማይኖራቸው የተረዳቹ ይመስለኛል ለምሳል ኢትዮጵያ የላከቻት ሳተላይት አንዳዴ ወደ ምድር ትቀርባለች አንዳዴ ደግሞ ከፍ ትላለች ምክንያቱ ይሄ "drag force" የተባለው አይል በሚያመጣው ተፅኖ ነው በነገራችን ላይ ፀሐይ እራሱ ተፅኖ አላት ለዚህ ሕይል መፈጠረ።
ሳተላይቶች ፍጥነታቸው የሚቀንስ ከሆነ ደግሞ ወደ መሬት ይወድቃሉ ነገረ ግን ከዛ በፊት ሳተላይቶቹ ይሄንን አይል የሚቃረን ወይም ባሉበት ቦታ እንዲፀኑ ለማድረግ ሌላ ውጫኛ አይል በመጠቀም "net force" ውን መልሰው ወደ ዜሮ ያመጡታል ሰለዚህ የቀነሰውን ፍጥነታቸውን መልሰው ሰለሚያገኙ ይካካሳል ሰለዚህ ፍጥነታቸው ቀንሶ ወደ መሬት የመውደቅ እድላቸውን ይቀንሳሉ ለዚህም ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው ISS ነው ለምሳሌ ናሳ ይሄንን ስቴሽን ባለበት ኦርቢት እንዲቀጥል በአመት እስከ 19,000 ፓዎንድ የለው ክብደት "propellant" ያቃጥላል።
ከዚህ አይል ጋር በተገናኝ የቻይናው ሮኬት ይሄንን አይል ቫላንሳ ማድረግ አቅቶት ነው የወደቀው የሚሉም አልታጡም እደሚክንያት የሚያነሱት ደግሞ ሮኬቱ በአንዴ ወደ መሬት ከባቢ አየር አለመግባቱ እና የተወሰነ ቀን ምድርን መሽከርከሩ ነው።
በነገራችን ላይ አብዛኛው የሮኬቱ ከፍል የተቃጠለው ሮኬቱ ወደ ምድር ከባቢ እደገባ ነው ነገረ ግን የህንድ ዊቂያኖስ ውስጥ ወድቆ ያየነው ጠንካራው ወይም በቀላሉ የማይቃጠለው የሮኬቱ ክፍል ነው በእንግልዘኚው እንደነዚህ አይነቶችን እቃዎች "high melting point" ያላቸው ማቴሪያሎች ብለን እንጠራቸዋለን።
ሳተላይቶችን እንዴት ነው በአይናችን ማየት የምንችለው በርግጥስ ይታያሉ ከታዩስ በምን ሰሀት?
118 viewsedited 00:06