Get Mystery Box with random crypto!

​ሮኬቱ የት ሊወድቅ ይችላል? ቻይና በቅርቡ ወደ ሕዋ ያስወነጨፈችው ሮኬት ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ቅዳ | Ethio cyber

​ሮኬቱ የት ሊወድቅ ይችላል?

ቻይና በቅርቡ ወደ ሕዋ ያስወነጨፈችው ሮኬት ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ቅዳሜ እና እሁድ ላይ ስብርባሪው መሬት እንደሚደርስ ተነግሯል።

ይህ ከቁጥጥር ውጪ የሆነ የሮኬት ስብርባሪዎች አካል በትክክል መቼ እና የት እንደሚወድቁ እርግጠኛ መሆን
አልተቻለም።

ማርች 5ቢየሚል ስያሜ የተሰጠው ሮኬት ባሳለፍነው ወር መገባደጃ ላይ ነበር ቻይና በሕዋ ላይ ለመስራት ላሰበችው ማዕከል የሚሆኑ ቁሳቁሶችን ይዞ ነው ወደ ህዋ የተወነጨፈው።

18ሺህ ኪሎ ግራም የሚመዝነው ሮኬት በአስርት ዓመታት ውስጥ ቁጥጥር ሳይደረግበት ወደ ምድር የሚወድቅ ግዙፍ ቁስ ይሆናል ተብሏል።

አሜሪካ ትናንት ባወጣችው መግለጫ የሮኬቱን አቅጣጫ እና አካሄድ በቅርበት እየተከታተለች እንደሆነ በመግለጽ ተኩሳ የመጣል እቅድ ግን እንደሌላት አስታውቃለች።

የአሜሪካ የመከላከያ ሚንስትሩ ሎይድ ኦስቲን "ሮኬቱ ጉዳት
ሳያስከትል እንደሚወድቅ ተስፋ እናደርጋለን" ብለዋል። ምናልባት የባህር አካል ላይ ወይም ሰዎች በማይኖሩበት ቦታ ላይ ይወድቃል ብለው እንደሚገምቱ ተናግረዋል።

የመሬት አካል አብዛኛው ክፍል በውሃ የተሸፈነ እና አብዛኛው
የምድራችን ክፍል ሰዎች የማይኖርበት መሆኑን ከግምት
በማስገባት ሮኬቶ በሰዎች ላይ ሊያደርስ የሚችለው ጉዳት
አነስተኛ ነው ተብሏል።

ባለሙያዎች 75 ሜትር ቁመት ያለው ሮኬት ምድር ሳይደርስ
አብዛኛው ክፍሉ ተቃጥሎ ሊያልቅ እንደሚችል ጠቁመዋል።

ከፍተኛ ሙቀት መቋቋም የሚችሉ እና የማይቀልጡ የሮኬቱ አካላት እንደሚወድቁ ግን ይጠበቃል። ሮኬቱ ወደ ምድር ቢያንስ በሰዓት 60 ኪሎ ሜትር እየምዘገዘገም እንደሚወርድ ይጠበቃል።

ቻይና ከዚህ በኋላም ተጨማሪ 10 ተመሳሳይነት ያላቸው ሮኬቶችን ወደ ሕዋ ለማስወንጨፍ እቅድ ያላት ሲሆን የአውሮፓውያኑ 2022 ከመጠናቀቁ በፊት ደግሞ የራሷን የሕዋ ማዕከል ለመገንባት አቅዳለች።

ሊወድቅ የሚችልበትን አከባቢ ከታች በካርታ ላይ በሚታይ ምስል አካተን አታች አርገነዋል እንደ ካርታው ከሆነ ኢትዮጲያ ውስጥም ሊወድቅ ይችላል

Via bbc

Share Share

@ethiotefer @ethiotefer

@ethiotefer @ethiotefer