Get Mystery Box with random crypto!

'James Webb Space' የተሰኘው ቴሌስኮፕ እንዴት 12 ቢልዬን አመት ወደ ዋላ ሊወስደን ይች | Ethio cyber

"James Webb Space" የተሰኘው ቴሌስኮፕ እንዴት 12 ቢልዬን አመት ወደ ዋላ ሊወስደን ይችላል?

ይሄ ቴሌእስኮ በቅርብ ወራት ውስጥ ወደ ጠፈረ የሚላክ ሲሆን አፅናፍ አለም ከ12 ቢልዬን አመተ በፊት ምን አይነተ ገፅታ እደነበረው ያሳያል ተብሎ ይታመናል። ይሄ እንዴት ሊሆን ይችላል?

ሚስጥሩ ብርሃን ነው , የሰው ልጆች ሆኑ ማንኛውም ነገረ የብርሃን ጨረረ ሲኖር ብቻ ነው ማየት የሚችሉት ወይም ሌሎች የብርሃን አይነት ጨረሮች ሲኖሩ ብቻ ነው።

አይኖቻችን ያለ ብርሃን ምንም ናቸው ለምሳሌ አንድ ሰው የቤቱን ብር አየ ስንል ከፀሐይ የመጣው ብርሃን በሩ ላይ ካረፈ በዋላ አንፀባርቆ ወደ አይኑ ሲገባ ብቻ ነው በሩን የሚያየው ከዛ ውጭ ምስል አይምሮ ውስጥ አይቀረፀም ወይም አይታይም በሩ ላይ ተንፀባርቆ የሚሄደው ብርሃን ደግሞ እጅግ ፈጣን ሰለሆን በሩን በቅፅበት ያየነው ይመስላል ነገረ ግን በቅፅበት የሚሆን ነገረ የለም
ማለትም ብርሃን ከበሩ ተነስቶ ወደ አይኑ ሲገባ የሆነ ጊዜ ይወስድበታል

ምንም እንኳን ከኛ ብዙ ያራቀነ ነገረ ስናየው በቅፅበት ልንለውል እንችላለን ከብርሃን ፍጥነተ አንፃር ነገረ ግን በጣም እሩቅ ሲሆን እንደዛ ብሎ መደምደም አይቻልም

ለምሳሌ ጨረቃን መሬት ላይ ሁነን ስናያት የምናየውም የጨረቃ ገፅታ ከአንድ ሰከንድ በፊት የነበረውን እንጂ በቅፅበት ያላትን ገፅታ አደለም ፀሐይን ስንመለከታት ደግሞ ከ8 ደቂቃ በፊተ የነበረውን የፀሐይን ገፅታ እንጂ በቅፅብት አደለም የምናያት

የማታዎቹ ኮከቦችን ስናያቸው ደግሞ በቅፅበት ያላቸውን ገፅታ ሳይሆን ከሽህ ወይም ከሚልዬን አመት በፊት የነበራቸውን ገፅታ ነው ልናይ የምንችለው ማለትም የኮከቦቹ ብርሃን እኛ ምድር ላይ የሚደርሰው ከሽህ ወይም ከሚልዬን አመት ጉዞ በዋላ ነው ይሄ ብቻ አደለም በዚቺ አውን በምናይበት ቅፅበት ኮከቦቹ ጠፍተው ወይም የሆነ ነገረ ሁነው ሊሆን ይችላል ነገረ ግን ይሄንን ለውጥ ለማየት ሌላ ሽህ ወይም ሚልዬን አመት ሊያስፈልገን ይችላል ይሄ ሁሉ የሚሆነው ብርሃን በሰከንድ 300,000km እየተጓዘ ነው

ለምሳሌ "NGC1052-DF2" የተሰኘው ጋላክሲ ከሰው ልጆች 70 ሚልዬን የብርሃን አመት ይርቃል ዳይነሶሮች ከኛ አለም ከጠፉ ደግሞ 65 ሚልዬን አመተ አልፎታል የተለዩ ፍጥሮች በዚህ "NGC1052-DF2" የተባለ ጋላክሲ ውስጥ አሉ ብለን ብናስብ እና ከኛ እጅግ የረቀቀ ቴሌስኮፕ ቢኖራቸው ማለትም የኛ ምደር ላይ ያለውን ነገረ በሙሉ ማየት የሚያስችል ነው ብንል እና አውን በዚች ቅፅበት ወደ ሚልክዌ ጋላክሲ ውስጥ ወደ ሚገኘው ፀሐይ እና ፀሐይን ወደምትዞረዋ መሬት ቢመለከቱ የሚያዩት ከ65 ሚልዬን አመት በፊት የጠፉትን ዳይንሰሮችን(Dinosaurs) ይሆናል

ይሄ በቅርቡ ይላካል ተብሎ የሚጠበቀው ቴሌስኮፕ 12 ቢልዬን አመተ ወደ ዋላ ይወስደናል ማለተ 12 ቢልዬን አመተ ሙሉ ተጉዙ የመጣውን ብርሃን አጉልቶ ያሳየናል እንደማለተ ሲሆን ብርሃኑ አንፀባርቆ የመጣበትን ፕላኔት ወይም የኮከብ ገፅታ ያሳያል ማለተ ነው ብርሃኑ አንፀባርቆ የሚመጣው ውይም ምድር ላይ የሚደርሰው ከ12 ቢልዬን አመተ በዋላ ነው ይሄ ማለተ ደግሞ ብርሃኑ ወደ መሬት ይዞ የሚመጣው ብርሃን የያዘው መረጃ ከ12 ቢልዬን አመት በፊት የነበረውን ነገረ ሁኔታ ወይም ታሪክ ነው።

ይሄ ቴሌስኮፕ እንደ አብል ቴሌስኮፕ ምድርን አደለም የሚዞረው ...ቴሌስኮፑ የሚዞረው መሬትን ሳይሆን ፀሐይን ነው ልክ እንደፕላኔቶች ነገረ ግን በመሬት ትይዩ ነው የሚዞረው ፀሐይን ሰለዚህ መረጃዎችን በቀላሉ ወደ ምድር ይልካል ተብሎ ይጠበቃል

ቴሌስኮፗች ስራቸው የሩቅን ነገረ አቅርቦ ማሳየተ ነው ወይም አግዝፎ ማሳየት ነው ወይም አንፀባርቆ የመጣውን ብርሃን በማግዘፍ የሰው ልጆች እዲያዩት ማመቻቸተ ነው እና ለምን ምድር ላይ እንዳሉ አንጠቀማቸውም ወይም ለምን ወደ ጠፈረ መላክ አስፈለገ ?

እንዚህ እስፔስ ነከ ቴሌስኮፖች ብዙዎቹ እጅግ በጣም ሰንሴቲቪ ናቸው ማለትም በቀላሉ ሊታወኩ ይችላሉ ለምሳሌ ምድር ላይ ብዙ አይነተ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮአዊ ብርሃኖች አሉ ሰለዚህ እንዚህ ብርሃኖች ከረቁ ቦታ የሚመጡትን ብርሃኖች የማጥፍት ወይም የማወከ አቅም አላቸው ሌላው ደግም የመሬት ከባቢ አየረ ወደ መሬት ብርሃን እንዳይመጣ የማገድ አቅም አለው ሰለዚህ መፍትሔው ቴሌስኮፖችን ድቅድቅ ጨለማ ወደሆነው ጠፈረ መላክ ነው

share share

@ethiotefer @ethiotefer

@ethiotefer

@ethiotefer @ethiotefer