Get Mystery Box with random crypto!

የአፅናፍ አለም ትንሹ ኮከብ እና ፕላኔት ጁፒተር እንደሚታወቀው የኛ ጋላክሲ በሆነው ሚልክዌጋላክሲ | Ethio cyber

የአፅናፍ አለም ትንሹ ኮከብ እና ፕላኔት ጁፒተር

እንደሚታወቀው የኛ ጋላክሲ በሆነው ሚልክዌጋላክሲ ውስጥ ከ400 ቢልዬን በላይ ኮከቦች አሉ በዚህ ጋላክሲ ውስጥ ከተገኙ ኮከቦች መሀል "EBLM J0555-57Ab" የተባለው "red dwarf" ኮከብ ከኛ ምድር 600 የብርሃን አመት የሚርቅ ሲሆን ስፍቱ ደግሞ 180,000km ብቻ ነው ይሄም "saturn" ከተባለው ፕላኔት ጋር በስፍት ተመሳሳይ ነው።

ይሄ ኮከቡ በስበት መሬትን 300 እጥፍ የሚበልጣት ሲሆነ ይሄ ኮከብ የራሱ ፕላኔት የለውም ይልቁንም "EBLM JO555-57A" የተባለውን ኮከብ ልክ እንደ ፕላኔቶች ይዞራል ይሄ ኮከብ ከኛ ፀሐይ ጋር ተመሳሳይ ነው ኮከቡን ዙሮ ለመጨረስ ደግሞ 8 ቀን ብቻ ነው የሚፈጅበት

ይሄም ኮከብ እስከዛሬ ከተገኙ ኮከቦች ትንሹ ሲሆን "haydrogen" አተምን በጉልበቱ በማጣበቀ ወደ "helium" በመቀየር ብርሃን መፍጠር ይችላል እኛ ሶላር ሲስተም ውስጥ የሚገኙት ፀሐይ እና ጁፒተር ይሄንን ኮከብ በስፍት ይበልጡታል የጁፒተር ስፍት እንደሚታወቀው 140,000km ነው

ይሄ ማለተ ጁፒተር የተባለው ፕላኔት ይሄንን ኮከብ 22,000km ያክል በስፍት ይበልጣል

እና ለምን ጁፒተር የተባለው ፕላኔት ኮከብ አልሆነም

መልሳችን ሊሆን የሚችልው ይሄ ፕላኔት "hydrogen" አተምን በማጣበቅ ወደ "helium" በመቀየረ ብርሃንን ለመፍጠር የሚያስችል በቂ ስበት የለውም ወይም ሐይል የለውም ይሄም የሆነው በክብደቱ ምክንያት ነው "EBLMJO555-57Ab" የተባለው ኮከብ በስፍት ጁፒተር በተባለው ፕላኔት ይብለጥ እንጂ በክብደት 85 ጊዜ ጁፒተርን ያጥፈዋል በዚህ ምክንያት ከፍተኛ ስበተ ስላለው ሁለተ "hydrogen" አተሞችን በጉልበት እያጣበቀ ብርሃንን መፍጠር ይችላል

share share

@ethiotefer