Get Mystery Box with random crypto!

​የቀጠለ....... ምን አይነተ ቴክኒክ ነበረ የተጠቀመው ይሄ ሳይንቲሲት? መጀመሪያ መሬት ክብ | Ethio cyber

​የቀጠለ.......

ምን አይነተ ቴክኒክ ነበረ የተጠቀመው ይሄ ሳይንቲሲት?

መጀመሪያ መሬት ክብ ከሆነቸ በመሬት ወገብ አከባቢ ወይም በእንግልዘኛው "Equater" አከባቢ መሬት ከፀሐይ ጋር በቀጥታ ትይዩ ከሆነቸ ፀሐይን በቀጥታ ወደላይ እናያታለን በፀሐይቷ ምክንያት የሚፈጠረ የኛ ጥላ ደግሞ ከኛ አንፃር ዜሮ ድግሪ ነው

ይሄ ሳይንቲስት በሒሳባዊ መንገድ የመሬትን ስፍት የለካው በሁለተ በተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚወጣውን የፀሐይ ጨረረ የ"angle" ልዩነታቸውን በመፈለገ ነው ይሄንን የፈለገው ደግሞ በአውኑ ዘመን አስዋን እና አሌክዛንደር ተብለው በሚጠሩ የግብፅ ከተሞች ላይ ሲሆን በሁለቱ ቦታዎቸ ላይ ያለውን የፀሐይ ጨረረ የሚፈጥረውን ጥላ ተመርኩዞ ነው ይሄ ብቻ ሳይሆን በተመሳሳይ "longitude" ተመሳሳይ ሰሀተ እንዳለ ተርድቷል ወይም ከ"north pole" ወደ "south pole" ቀጥ ባሉት መስመሮች ላይ ተመሳሳይ ሰሀተ እንዳለ ገምቷል ለዚህም ነበረ ሁለቱን ከሞች የተጠቀማቸው

ያገኘውም የ"angle" ልዩነተ 7.2 ነበረ በመቀጠልም በሁለቱ ከተሞች መሀል ያለውን እርቀተ ለክቷል በወቅቱ ነገሮች የሚለኩት "km" ወይም በ"meter" ሳይሆነሰ "stadium" በሚባል ነገረ ነው በሁለቱ ከተሞች መሀል ያለው እርቀት 5000 stadia ነበረ ይሄንን እርቀተ ወደ ኪሎ ሜትር ስንቀይረው 787km ነው

ይሄ እርቀተ ከጎንደር እስከ አዲስ አበባ ይደርሳል ይሄንን የለካው መኪና ወይም ሌላ ነገረ ተጠቅሞ አደለም ግመሎችን ብቻ ተጠቅሞ ነው።

ይሄንን መሰዋትነተ የከፈለው ለ ገንዘብ ወይም ጥቅማጥቅም ለማግኘት አደለም ስንቁ ለማወቀ ያለው ጉጉት ብቻ ነው ወይም ለሳይንሱ ያለው ፍቅር ነው በዚህ ዘመን የምንኖር ሰዎች ለማወቅ ምን ያክል መሰዋትነተ እንከፍላለን ጥንት አባቶች ትምህርት ቤት ሳሄዱ አውቀትን የሚፈልጓት ወይም ለማወቅ የሚጥሩት በእንዲ አይነቱ መንገድ ነበር በዚህ ዘመን ግን ትምህርት ቤቶች በዝተዋል ሌሎች መንገዶቸም አሉ እኛስ እየተጠቀምናቸው ነው ወደ ትምህርት ቤት የምንሄደውስ ከምር ለማወቀ ነው ,እውቀትን ፍለጋ ነው ወይስ.... ሁላችንም እራሳችንን ልንጠይቅ ይገባል

ይሄ ሳይንቲስት የለካው ግመሎችን እየተጠቀመ ሰለነበረ የለካበተ መንግድ ጥራቱን የጠበቀ ወይም በ ሳይንሱ የሚጠበቅበትን "accuracy"ባለሟማላቱ የተነሳ በአውኑ ዘመን ከተለካው ቁጠር ጋር የተወሰነ የቁጥረ ልዩነተ እንዲፈጥር አድርጓል ሳይንቲስቱ በተመሳሳይ ሰሀተ በሁለቱ ቦታዎች ላይ ያለውን የፀሐይ ጥላ ለመለካት እጅግ የሚያስደንቅ ስራ ሰርቷል እንዲውም በእንዲ አይነተ መንገድ የመሬትን ስፍት አገኛለው ብሎ ማሰቡ በዚህ ዘመን ያሉ ሳይንቲስቶችን አስደንቋል እንዲውም ሐሳቡ እራሱ እንዴት መጣለት ብለው የሚጠይቁ ብዙዎች ናቸው

የሆነው ሁኖ ወደ ሒሳቡ ስንመጣ

በሁለቱ ከተሞች ያለውን እርቀተ "d" እንበለው በመቀጠለ ደግሞ በሁለቱ ከተሞች ያለውን የፀሐይ ጨረረ የፈጥረውን ጥላ አንግል በመቀናነስ ያገኘነውን አንግል "s" እንበለው አውን የምንፈልገውን የመሬት ዙሪያ ያለውን ስፍት ወይም "circumference" ነው አስተውሉ ይሄ 787km የመሬት "circumference" አንዱ አካል ነው ማለትም በ7.2 ድግሪ የመሬት አካል 787km ስፍት አለው እንደማለተ ነው አጠቃላይ መሬት ክብ ነች ሰለዚህ አጠቃላይ ድግሪዋ 360 ነው ሰለዚህ ለ7.2 ድግሪ 787km ከሆነ ለ360 ድግሪ ስንት ይሆናል?

የመሬት አጠቃላይ ድግሪ 360 ሲሆን "a" እንወክለው አጠቃላይ የመሬት ዙሪያ አጠቃላይ ስፍት ወይም "circumference" በ"c" እንወክለው።

given req answer

a=360° c=? if s=d
d=787km then c=a
s=7.2° s/a=d/c

c=a*d/s
ቁጥር ስንተካ

c=360*787/7.2

c=39,350km

"Circumference" ወይም መሬት ፍፁም ክብ ብትሆን መሬትን አንድ ዙር ዙሮ ለመጨረስ 39,350km መጓዝ አለብን እንደማለተ ነው።

በመቀጠል የመሬትን "radius" እንፈልግ።

circumference=2*pi*radius


Pi= 3.14

r=c/2*pi
r=39350/2*3.14

r=6,267km

ይሄንን ይመስላል ዘመናዊ የተባለው ልኬት የተደረገው ሰው ሰራሽ የሆኑ ሳተላይቶች መሬትን መዞር ከጀመሩ በዋላ ሲሆን
የመሬት "circumference" 40,070km ሲሆን "radius" ደግሞ 6,378km ነው

ያላቸውን ልዩነተ ማወዳደረ ትችላላቹ

ሌላው ነገረ መሬት ፍፁም ክብ ባለመሆኗ የተነሳ ብዙ አይንተ ልኬት አለ አቭርጄ ልኬቱ ግን ከላይ ያለውን ይመስላል

Share share

@ethiotefer @ethiotefer
@ethiotefer
@erhiotefer @ethiotefer