Get Mystery Box with random crypto!

ክፍል ሁለተ ኦርምኦል እና እስፔስታይም መስመሮች ከዚህ ቀደም ማንኛውም ነገረ በእስፔስታይም መስ | Ethio cyber

ክፍል ሁለተ

ኦርምኦል እና እስፔስታይም መስመሮች

ከዚህ ቀደም ማንኛውም ነገረ በእስፔስታይም መስመሮች ላይ ነው የሚሄደው ወይም ተቀምጦ ያለው ብለነ ነበር እንዲውም ግራቪት የምንለው ነገር ስበት ሳይሆን በእነዚህ መስመሮች ላይ እንድንሄድ የሚያስገድድ አይል እንደሆነ አይተናል

ዛሬ ደግሞ ኦርምኦል ቢኖር እስፔስታይም ምን ይመስላል የሚለውን እናያለን በምስሉ ላይ እንደምናየው እስፔስታይም መስመሮች መሀል ላይ ወይም "2" ቁጥር ላይ በአቋራጭ ተገናኝተዋል

ለምሳሌ የኛ ፕላኔት ያለቹ "1" ቁጠር ላይ ነው ብንል "4" ቁጠር ላይ ደግሞ መሉ በሙሉ በውሃ የተከበበቹ ፕላኔት አለች እንበል ከመሬት ተነስተነ ወደዚህ ፕላኔት ለመሄድ ሁለተ አማራጭ አለነ አንደኛው በ"3"ኛው ቁጠር በኩል ዙረን መሄድ ሲሆን ይሄም በትክክለኛው መንገድ ሄድን እንደማለተ ሲሆን በዚህ መንገድ በብርሃን ፍጥነተ ከተጓዝን 40 አመት ይፈጅብናል ወይም በፈጣኗ እስፔስክራፍት ከሄድን ደግሞ 700,000 አመት ይፈጅብናል ነገረ ግን በ"2"ቁጠር በኩል አቋራጭ መንግድ እንዳለ ይታያል

ይሄም እነ አልበርት አንስታይን "space time" መስመሮች ውስጥ ድልዲ አለ ሁለተ የተለያዩ ቦታዎችን የሚያገናኝ ወይም የሚያስተሳስር ይሄም ደግሞ ከቦታ ቦታ ለመሄድ አቋራጭ መንገድ ነው ወይም ጊዜ ና እርቀትን በእጅጉ ይቀንሳል ያሉት "Einistein-Rosen bridge" ወይም hormhole ብለን የምንጠራው ነው

"2" ቁጥር ባለበተ ቀዳዳ መሄድ ከቻልን ጉዞውን በደቂቃ ውስጥ ልንጨርሰው እንችላለነ ማንኛውም ነገረ እኛን ጨምሮ እስፔስታይም መስመሮች ላይ ነን እስፔስታይም መስመሮች በአይን አይታዩም ግን በነሱ ምክንያት የሚመጣውን ተፅኖ ማየት ይቻላል ጥያቄው ይሄንን አጭር መንገድ እንዴት እናግኘው ወይም እንዴት እንፍጠርው ነው